Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member+
Posts: 5066
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Meleket » 25 Mar 2026, 11:23

የህዝብ መዝሙሮች ሱዳን - ኤርትራ - ትግራይ - አማራ [ፋኖ] - ኦሮሞ - ለጨዋታ ያህል

በቅርቡ ከሰላ ላይ በጽምዶ ዙርያ በተደረገው የህዝቦች ግንኙነት ወቅት ሶስት የህዝብ መዝሙሮችን አድምጠን ነበር።

የሱዳን ህዝብ መዝሙር - ሱዳን የሚል ቃል ሰምተንበታል።

የኤርትራ ህዝብ መዝሙር - ኤርትራ የሚል ቃል በተደጋጋሚ ሰምተንበታል።

የትግራይ ህዝብ መዝሙር - “መስመር ኢዩ ኃይልና!” የሚል ቃል በተደጋጋሚ የሰማንበት ሲሆን በውስጡ ግን ትግራይ ወይ ተጋሩ የሚል ቃል አልሰማንበትም።

እንግዲህ በጨዋ ደንብ ለትግራይ ወገኖቻችን “ብሮቦስ” እናደርጋለን። ብሄራዊ የህዝብ መዝሙራቸው ማንነታቸውን በአጭር ቃል የሚገልጽ ቃል ሳያስፈልገው አይቀርም።

እንደሰማነው
“መስመር ኢዩ ኃይልና ሕዝቢ ኢዩ ክባታት ጸላእቲ ክንፍጽሖ ኢና!

መስመር ኢዩ ኃይልና ሕዝቢ ኢዩ ኃይልና ተዓወቲ ኢና!

መስመር ኢዩ ኃይልና ሕዝቢ ኢዩ ኃይልና ወይከ ኣይንሰዓርን! ወዘተ”
የሚሉ ቃላት በተደጋጋሚ አሉት።

ታዲያ አንዱን ስንኝ
“መስመር ኢዩ ኃይልና ሕዝቢ ኢዩ ኃይልና ንሕና ተጋሩ ኢና!” ወይም

መስመር ኢዩ ኃይልና ሕዝቢ ኢዩ ኃይልና ደቂ ትግራይ ኢና!” ብለው ቢደመድሙት ሳይሻል ኣይቀርምን ይበልጥ ማንነታቸውን ገላጭ አይሆንምን?

Axumezana wrote:
22 Mar 2026, 18:34
...
sarcasm wrote:
22 Mar 2026, 09:50
...
Tigray People wrote:
22 Mar 2026, 12:58
...

ለማንኛውም የተሳሳተ ግንዛቤ ካለን ለመታረም ዝግጁ ነን። የመረጃ ወዳጆቻችን እነ ስታሊንና ሃይለ ደደቢት ጭምር ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? ጽምዶ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ሰላማዊ የሃሳብ ልውውጥን መቼም አይቃወምም።

በነገራችን ላይ የፋኖ ወይም የአማራ ህዝብ መዝሙርስ ምን ይመስላል? የምታውቁት ካላችሁ ወዲህ በሉት እስቲ። የትግራዮቹም ሙሉውን ግጥሙን እስቲ አካፍሉን።

የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርስ ግጥሙ ይዘቱ ምን ይመስላል!

Mesob
Member
Posts: 3019
Joined: 23 Dec 2013, 21:03

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Mesob » 25 Mar 2026, 14:09

From all the national or regional songs, the Tigrayan song has the best lyrics and melody, while the Eritrean song has a very good melody but it has the worst and disappointing lyrics that is nailed in the past full of lamentation - melqes or liqso.
The Eritreans song that does not look into the bright future.

Meleket
Member+
Posts: 5066
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Meleket » 26 Mar 2026, 03:37

በኛ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ አተያይ፡ ሁሉም ብሄራዊ መዝሙሮች ውብ ዜማ አላቸው፡ ይዘታቸውም ከሞላ ጎደል መልካም እንደሆነ እናምናለን።

የኤርትራን የህዝብ መዝሙር በተመለከተ ብርቁ ታጋይ ሰለሞን ጸሃዬ በራኺ ገና ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት የቋጨውን ውብ ግጥም ከነጻነት በኋላ አሻሽሎ ምርጥ የሆነ ይዘት ያለው ግጥም እንዳደረገው ኤርትራዉያን እናውቃለን። ዜማውም በነጻነት ታጋዮቹ በኢሳቕ ኣብርሃም መሃረዝጊና በአሮን ተኪኣ ተስፋጽዮን ኣቀናባሪነት እንደተሰራ እናውቃለን።

ይዘቱ በአጠቃላይ፡
ኤርትራ ደመኛ ጠላቶቿን አስለቅሳ፡ ነጻ እንደወጣች፡ መስዋእቷ ከንቱ ሆኖ እንዳልቀረ፡ ለዘመናት በፍትሓዊ ዓላማዋ ጸንታ ስለታገለች፡ የጽናት ምልክት ሆና፡ ለጭቁኖችም ኩራት ሆና፡ እውነት ሁሌም አሸናፊ መሆኗን ያረጋገጠች፡ በዓለም መድረክም ተገቢዉን የክብር ቦታዋን በመስዋእቷ እንዳረጋገጠች፡ ለነጻነት እንደተደረገው ጥረት ሁሉ ለልማትና ለሃገር ግንባታም ጥረት በማድረግ፡ ስልጣኔን በማቀላጠፍ ኤርትራን ግምጃ ለመሸለም አደራ እንዳለብን በመግለጽ በድጋሜ ኤርትራ በዓለም መድረኽ ተገቢውን የክብር ቦታዋን በመስዋእቷ እንዳረጋገጠችና እንደተጎናጸፈች
በመግለጽ ይቋጫል።

ይዘቱ እንደወረደ ይህን ይመስላል።

Eritrea, Eritrea, Eritrea,
Her Nemesis destroyed while wailing,
her sacrifices vindicated by freedom.

Forever firm in her principles,
her name became a synonym of tenacity,
Eritrea, the pride of the oppressed,
is a testament that truth prevails.

Eritrea, Eritrea,
has taken her rightful place in the world.

[So that] The supreme dedication that brought us freedom,
will serve to rebuild her and develop her,
We shall honor her with progress,
It is our legacy to crown her.

Eritrea, Eritrea,
has taken her rightful place in the world.
https://en.wikipedia.org/wiki/Eritrea,_Eritrea,_Eritrea
Mesob wrote:
25 Mar 2026, 14:09
From all the national or regional songs, the Tigrayan song has the best lyrics and melody, while the Eritrean song has a very good melody but it has the worst and disappointing lyrics that is nailed in the past full of lamentation - melqes or liqso.
The Eritreans song that does not look into the bright future.

Meleket
Member+
Posts: 5066
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Meleket » 26 Mar 2026, 03:58

የኤርትራ ህዝብ ብሄራዊ ወይም ሃገራዊ መዝሙር የኣማርኛ ግርድፍ ትርጉም ነው! እስቲ አጣጥሙት!

ኤርትራ ኤርትራ ኤርትራ፡
ደመኛዋ እያለቀሰ ተደመሰሰ፡
መስዋእቷም በሓርነት ተመለሰ።

በዓላማዋ ጸንታ ለዘመናት፡
ስሟ ሆነ ምልክት የጽናት።
ኤርትራ ይቺ የጭቁኖች መኩሪያ፡
ምስክር ነች ለሓቅ አሸናፊነት መታያ።

ኤርትራ ኤርትራ ኤርትራ፡
በዓለም መድረኽ ተገለጸ ክብሯ።

ነጻነትን ያስገኘው ግዙፍ ወኔ፡
አሁንም ሊተጋ እንዳረገው ያኔ፡
የስልጣኔ ግርማ ልናለብሳት፡
ብርቱ አደራ አለን ግምጃ ልንሸልማት። [ብርቱ አደራ አለን ከሰማእታት።]

ኤርትራ ኤርትራ ኤርትራ፡
በዓለም መድረኽ ተገለጸ ክብሯ።

ግርድፍ ትርጉሙ ተጣፈ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Mesob wrote:
25 Mar 2026, 14:09
From all the national or regional songs, the Tigrayan song has the best lyrics and melody, while the Eritrean song has a very good melody but it has the worst and disappointing lyrics that is nailed in the past full of lamentation - melqes or liqso.
The Eritreans song that does not look into the bright future.
ወዳጃችን Mesob ከሞላ ጎደል የግጥሙ ይዘት እላይ የተጠቀሰው እንደሆነ እየታወቀ፡ ልቅሶውና መልቀስ የተባለው በምን ሂሳብ ነው። ታሪክ መጥቀሱ እንዴት ከለቅሶና ከመልቀስ ጋር ይታሰባል። ልቅሶና ቁዘማ ያስተጋባል የተባለው የግጥሙ ክፍል ለመሆኑ ዬትኛው ነው? በእርግጥ እያለቀሱ ያሉት የኤርትራ ጠላቶች መሆናቸውን ነው ግጥሙ በመጀመርያው ስንኞቹ ላይ ቍልጭ አድርጎ ያሰፈረው።

ወዳጃችን Mesob እስቲ የትግራይ ህዝብ ወይም የአማራ ህዝብ ብሄራዊ መዝሙርን ግጥም ይዘት አጋራን፡ ካልሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ 'ብሄር ብሄረሰቦች' መዝሙርን ግጥም ይዘት አጋራን።

Selam/
Senior Member
Posts: 17793
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Selam/ » 26 Mar 2026, 08:16

የክፍለ ሃገርን ልዩ ውበትና ለሃገሪቱ ያለውን አስተዋፅዖ የሚገልጥ የህዝብ መዝሙርን መደገፍና ማበረታታት ይገባል። ስለ ጦረኝነትና ጀብደኝነት በብሄራዊ መዝሙር ብቻ መጠቃለል ይኖርበታል።

በተረፈ ስለኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙሮች ፈንዳዳውን ጠይቀው፤ በእኔ ትዕዛዝ እጥብ አድርጎ አጥንቷቸዋል።

Meleket
Member+
Posts: 5066
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Meleket » 26 Mar 2026, 09:42

ይህ የትግራይ ክልል ህዝብ “ብሄራዊ” መዝሙር ነው። እንደተባለው ከግጥሙ ይዘት እንደተገነዘብነው “ጀብደኝነትና ጦረኝነት” ቢመስልም እንኳ፡ የትግራይ ህዝብ የትግል ጽናትንና የምከታ ታሪክን ያንጸባረቀ ሆኖ አግኝተነዋል። “ተዓወቲ ኢና!” የሚለውን የመዝሙሩን የመጨረሻ ስንኝ ክፍል ሲደጋግሙት ስላስተዋልን፡ ከመደጋገም ይልቅ “ብሄራዊም ሃገራዊም” መዝሙር ይሆን ዘንድ “ንሕና ተጋሩ ኢና!” ወይ ደግሞ “ደቂ ትግራይ ኢና! ብለው ቢደመድሙት ደግሞ ይዘቱን ይበልጥ ኃያል ያደርጉታል የሚል ግምት አለን።
ናይ ትግራይ መዝሙር (Tigray Region)

ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ
ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና
ወይከ ኣይንስዓርን!
ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ
ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና
ወይከ ኣይንስዓርን!
ሃሩር ፀሓይ ንዳድ ህቦብላ ማይ በረድ
ማይማይ ትበል ነብሲ ኣብ ጀቕጀቕ ትረግረግ
ደንጎላ ንተርኣስ በዓቲ ይኹን ቤትና
ለይትን ቀትርን ጉዕዞ ንድከም ይጥመየና
መስመር እዩ ሓይሊና ህዘቢ እዩ ሓይሊና
ወይከ ኣንስዓርን
ንከበብ በዛብእ መሬት ትፅበበና
ኣብ ስጋና ይቀርቀር ኣስናን ፀላእትና
ስጋና ንኣሞራ ደምና ውሑጅ ይኹን
ኣዕፅምትና ይድቀቕ ሕሩጭ ኮይኑ ይበተን
መስመር እዩ ሓይሊና ህዘቢ እዩ ሓይሊና
ናፓልም ምስ መርዛም ጋዝ ፋሽሽታዊ ነዳድ
ሚሊዮን ቁምቡላታት ኣብ ቅድሜና ይንጎድ
መስዋእትን መቑሰልትን ክሳራታት ንክፈል
ዝኸፍአ መከራ ውዲታት ይፍተልተል
መስመር እዩ ሓይሊና ህዝቢ እዩ ሓይሊና ተዓወቲ ኢና!

የትግራይ ልጆች ካላችሁ እስኪ፡ የዚህ ግጥም ገጣሚ ማን ነው፡ ዜማውንስ ማን ነው ያቀናበረው፡ ለታሪክ መዝግቡት እስቲ! ግጥሙ ዚገጠም የድሮን የሚሳይል ወዘተ ሚና በቀጠናችን ብዙም ይታወቅ ስላልነበረ እንጂ፡ ገጣሚው አሁን ግጠመው ቢባል ድሮንና ሚሳይልንም አካቶ ለማቅረብ ወደኋላ እንደማይል ከግጥሙ መረዳት ችለናል። ቢሆንም ግን ሚሊዮኖችን ለአንድ ዓላማ ያነቃቃ ግጥምና ዜማ በመሆኑ ለገጣሚውም ለዜማው አቀናባሪም ከፍ ያለ አክብሮት አለን፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Meleket
Member+
Posts: 5066
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Meleket » 26 Mar 2026, 09:59

ወዳጃችን Mesob የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ መዝሙርን የአማርኛ ትርጉም ይህን ይመስላል። እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች የግጥሙን ይዘት ታጣጥመው ዘንድ እዚህ አካፍለንሃል ወዳጃችን። https://lyricstranslate.com/en/naaye-te ... zemur.html
የትግራይ መዝሙር

የማንወጣው ተራራ የማንሻገረው ወንዝ
ፍፁም የለም
መስመር (አቋም) ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም
የማንወጣው ተራራ የማንሻገረው ወንዝ
ፍፁም የለም
መስመር (አቋም) ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም
በፀሐይ ሃሩርና በቁር
ነፍሳችን ውሃ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን:ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም
መስመር (አቋም) ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም
በጅቦች እንከበብ ፣ መሬት ይጥበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር
ስጋችን ላሞራ ፣ ደማች እንደጎርፍ ይፍሰስ
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን
መስመር ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
የጦር መሳሪያ መርዝ ፣ ፋሺስታዊ ንዳድ
ሚሊዮን ጠላቶቻችን ፊታች ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት ፣ መቁሰልና ኪሳራም እንከፍላለን
ከዚህም የከፋ የጠላቶቻችን ሴራ ቢጎነጎን፣
መስመር ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን አሸናፊዎች ነን!

Mesob wrote:
25 Mar 2026, 14:09
From all the national or regional songs, the Tigrayan song has the best lyrics and melody, while the Eritrean song has a very good melody but it has the worst and disappointing lyrics that is nailed in the past full of lamentation - melqes or liqso.
The Eritreans song that does not look into the bright future.

Mesob
Member
Posts: 3019
Joined: 23 Dec 2013, 21:03

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Mesob » 26 Mar 2026, 23:48

Thank you Wendim Meleket for translating, posting and elaborating on your responses. I am still disappointed by some of the lines that are clear lamentation or Liqso in the Eritrean anthem. I agree ato Solomon Tsehaye, who attended General Wingate in Addis Ababa, is one of the finest poets in Eritrea, with a lot of respect for his classic book on collected traditional Tigrinya poems/Masse. I believe the anthem needs some work or fine tuning by focusing on the bright future of the land and the sea. There is no doubt its melody is remarkable.
It is true the Tigrayan's should adopt your recommendation and do some fine tuning to represent the current and future generations. They should definitely remove the lines that focus on their adversaries. The melody of their anthem is very catchy and nostalgic that reminds me the melodic notes of the old Protestant songs.
(I am very slow and clumsy in my Amharic responses)
Meleket wrote:
26 Mar 2026, 09:59
ወዳጃችን Mesob የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ መዝሙርን የአማርኛ ትርጉም ይህን ይመስላል። እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች የግጥሙን ይዘት ታጣጥመው ዘንድ እዚህ አካፍለንሃል ወዳጃችን። https://lyricstranslate.com/en/naaye-te ... zemur.html
የትግራይ መዝሙር

የማንወጣው ተራራ የማንሻገረው ወንዝ
ፍፁም የለም
መስመር (አቋም) ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም
የማንወጣው ተራራ የማንሻገረው ወንዝ
ፍፁም የለም
መስመር (አቋም) ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም
በፀሐይ ሃሩርና በቁር
ነፍሳችን ውሃ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን:ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም
መስመር (አቋም) ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም
በጅቦች እንከበብ ፣ መሬት ይጥበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር
ስጋችን ላሞራ ፣ ደማች እንደጎርፍ ይፍሰስ
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን
መስመር ነው ኃይላችን ፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን
የጦር መሳሪያ መርዝ ፣ ፋሺስታዊ ንዳድ
ሚሊዮን ጠላቶቻችን ፊታች ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት ፣ መቁሰልና ኪሳራም እንከፍላለን
ከዚህም የከፋ የጠላቶቻችን ሴራ ቢጎነጎን፣
መስመር ነው ኃይላችን ህዝብ ነው ኃይላችን አሸናፊዎች ነን!

Mesob wrote:
25 Mar 2026, 14:09
From all the national or regional songs, the Tigrayan song has the best lyrics and melody, while the Eritrean song has a very good melody but it has the worst and disappointing lyrics that is nailed in the past full of lamentation - melqes or liqso.
The Eritreans song that does not look into the bright future.

Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10173
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Digital Weyane » 27 Mar 2026, 00:53

በሞቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወገኖቻችን ወደ የመን ለመሻገር በጀልባ ባህር ሲያቋርጡ ፣ ወይም በሊቢያ በኩል አቋርጠው አውሮፓ ለመድረስ ሲሞክሩ፣ በጉዞአቸው ሁሉ የትግራይ ብሔራዊ መዝሙርን መዘመር ብርታት እንደሚሰጣቸው ይናገራሉ።
<<የማንወጣው ተራራ፣ የማንሻገረው ወንዝ፣ ፍፁም የለም።>> አምየን። አምየን። አምየን። :roll: :roll:

የብልፅግና ፓርቲን የተቀላቀለው ትግራዋይ ወንድማችን Mesob የትግራይ ብሔራዊ መዝሙርን ወደ አረብኛ ቋንቋ እየተረጎመው ይገኛል። የሩቁ ግባችን የአረብ ህዝብ በሙሉ መዝሙሩን እንዲማር ነው። አምየን። አምየን። አምየን። :roll: :roll:

almaze
Member+
Posts: 8814
Joined: 15 Dec 2013, 03:38

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by almaze » 08 Apr 2026, 15:28

ትማሊ ናይ ተደምረናል መዝሙር ዘሚሮም ሎሚ ከኣ ናይ ጽምዶ
Please wait, video is loading...

Meleket
Member+
Posts: 5066
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የህዝብ መዝሙሮች ትዝብታችን - በተለይም የትግራይ ህዝብ መዝሙርን በተመለከተ

Post by Meleket » 09 Apr 2026, 02:47

Meleket wrote:
25 Mar 2026, 11:23

Post Reply