(1) ግብጽ ሱዳን ኤርትራናንና ሌሎችን በመደገፍ
(2) ሳውዲ አረቢያ ኤርትራና ግብጽን በመደገ
(3) ቱርክ ሱማሌንና ግብጽን በመደገፍ
(4) ቃታር ጂቡቲን በመደገፍ
(5) አሜሪካ ምን ግዜም ደካማ ኢትዮጵያን መጫንና መቆጣተር ማዘዝ ይፈልጋል
ስለሆነም ኢትዮጵያ ከእስራኤልና ኢሚራቲ ሌላ የሚደርስላት ወዳጅ የላትም
ከዚህ አንጻር ከታየና አሜሪካ ሳይሆን እስራኤል ከጠየቀችን ለእስራኤል ስንል ሰላም አስጠባቂ ጦር ወደ ጋዛ መላክ ትርፍ አለው።
ሰላም አስጠባቂ ጦር ወደ ጋዛ የምንልክ ከሆነ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ሁለት ቅድመ ነገሮችን መጠየቅ ይገባታል!
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የምታገኘው ጂኦፖለቲካዊ ጥቅም ምንድን ነው?
(1) አሜሪካ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በግልጽ መደገፍ አለባት
(2) አሜሪካ ግብጽ በህዳሴ ግድብ ላይ የያዘችውን የጠላትነት ፖሊሲ እንድታቆም ማድረግ አለባት
ከግብጽና ከቀጠናው ጂኦፖለቲካ አንጻር ኢትዮጵያ ሰላም አስጠባቂ ጦር ወደ ጋዛ ብትልክ በግብጽ ድምበር ላይ ሰራዊት እንዲኖራት ስለሚያደርግ ግብጽ ለምታደርገው ጣልቃ ገብነት ትልቅ መልስ ይሆናል!!!
ኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወደ ጋዛ ብትልክ ውስብስብ የሆነው የፍልስጤምና እስራኤል ግጭት ውስጥ ያስገባታል ። ከብዙ የእስላምና አረብ ኃይሎች ጋርም ያጋጫታል፤ ለምሳሌ ቱርክ ፣ ኢራን ፣ ሳውዲና ሌሎችም።
ስለዚህ በእኔ እምነት አንድ ነገር ከተሟላ ብቻ ነው ኢትዮጵያ ይህ የሚያክል ሪስክ መውሰድ ያለባት ያም የባህር በርና የባህር ኃይላችን ቤዝ ቀይ ባህር ወይም ሕንድ ውቂያኖስ ላይ የሚከሰቱ ከሆነ ብቻ ነው
ከዚህ በመለስ የትራምፕ ጊዜያዊና ወረተኛ ፍላጎትና ግፊት ተከትሎ ኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ እስትራተጂያዊ ቅርቃር ውስጥ መግባት በፍጹም የለባትም ።