#አብይ ኢትዮጵያን ቀይ ባህር ለማስገባት ፣ ተፅዕኖ እንዲኖራት ለማድረግ ሲሞክር ነው በአለም ሀገራት ጫና የተደረገበት ይላሉ ... ፉከራ ፣ ሽለላ ፣ እዚህም እዛም መርገጥ ፣ ውረረው በ*ለ*ው እያለ ማጓራቱ አብይ ስራ እየሰራ ነው እንዲባል አስችሏል
ባሻ ፈርሴቡላ ሆይ .. በአብይ የህፃን ስራ ምክንያት ኢትዮጵያ ከበባ ውስጥ ወድቃለች። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ሲወጥኑ የአለም ሀያሃን ሀገር አሰላለፍ አይተው ትንሿ ጅቡቲ ድረስ የዲፕሎማሲያዊ ስራ ሰርተው ነው ግንባታውን የጀመሩት።
መለስ ዜናዊ ፓርላማ ላይ ማይክ ሲጨብጡ አልፎከሩም። ኢትዮጵያ አባይን ትገድባለች ብለው አልተወራጩም። ባገኙት አጋጣሚ የሚያደርጉትን አለፈለፉም። የዲፕሎማሲ ስራቸውን በሚስጥር ጨረሱ። የፕሮጀክቱን ሂደት ካጠናቀቁና ስራው እንደተጀመረ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።
የዛኔ ከግብፅ ጀምሮ ማንም ምንም ማድረግ የማይችልበት ጊዜ ነበር። የዲፕሎማሲ ሆነ ጂኦፖለቲካዊ ፣ ውስጣዊ ጫናዎችን ማድረግ ፈፅሞ የማይችሉ ሆነባቸው። መሪ አድርጎ ያሳያል እንጂ ፎክሮ ሀገርን በጠላት አያስከብብም።
#የአቡሽ የህፃን ልጅ ጩኸት ምክንያት ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የጂኦፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች። አራት ሀገራትን ያሳተፈ የቀይ ባህር ልምምድ በግብፅ መሪነትም እየተደረገ ነው።
ባልተሰራ ፣ እንደሌለ በተቆጠረው የዲፕሎማሲ ስራ ምክንያት ሁሉም ጎረቤት ሀገር ጀርባ ሰጥተውናል። ጫናዎች በሁሉም አቅጣጫ እየተደረገ ነው። #አብይ ስንዝር ሳይራመድ ይፎክራል ... ከጎረቤት ሀገራት እስከ አለም ሀገራት ድረስ ደግሞ በተግባር ስራቸውን ይሰራሉ።
የኢሳያስን ያህል አንድ ሀገር ሄዶ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ማሳመን ሳይችል .. ስራውን እየሰራ ስለሆነ ነው ተብሎ በፈርሴቡላው ይጨበጨብለታል። አውርቶ በማደሩ ብቻ በጠላት ሀገራት እያስከበበን ተፅዕኖ ስለፈጠረ ነው ይላሉ። ውስጣዊ ሰላም ማስከበር አቅቶት .. ቀጠናው ላይ እጁን ስላስገባ ያመጣው ነው ይባልለታል ...
ኢትዮጵያ በአውርቶ አደሩ አብይ ምክንያት አንድ ስንዝር ሳትራመድ በሰንሰለት ተጠፍንጋ ታስራለች። ፈርሴቡላው ደግሞ ተፅዕኖ ፈጠርን ብሎ ይጨፍራል
.
.
.
Please wait, video is loading...