በስም ማወቅ እንጂ በአካል ተገናኝተን ኣናዉቅም። ስለ ታሪክ ስራዎቹ ኣላዉቅም ነበር።
የገዳ ስርዓትን የማክበር ግዜዉ ደርሶ ትዉልድ ሃገሩ ከዘመዶቹ ጋር ለማክበር እየተዘጋጀ ነበር የሚል ወሬ በልጅነቴ ሰምቼ ኣስተዋይ ቢሆን ነዉ ኣስብሎኝ ነበር። በምን ምክንያት እንደሆነ ባላዉቅም ተወርቶ የተጠበቀዉ ሳይፈጸም ቀረ።
እኔ የታሪክ ተመራማሪ ባልሆንም በርካታ ነገሮችን ኣንብቤ ስለ ኢትዮጵያ የጥንት ታሪክ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ ብዬ ኣስባለሁ።
እጅግ የደነቀኝ ስለ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህ ስራዎች ሳላዉቅ ተመሳሳይ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ላይ መድረሳችን ነዉ።
በእኔ አስተያየት የእሱ ግንዛቤዎች እና ድምዳሜዎች በስድስት ቃላት ለዘላለማዊ ታሪክ ተቀምጠዋል።
እ ኢ አ በ1964 ቦረና ድሬ ሊበን ሄዶ ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ለካ ኣንተ ነህ ብሎ ለታሪክ ኣስቀምጧል። ለዘለለሙ።
እኔ ለመጀመርያ ግዜ የሰማሁት ከጥቂት ዓመታት በፊት ነዉ። ከሰማሁት ግዜ ጀምሮ ልረሳዉ ኣልቻልኩም። ለፍቼ የደመደምኩት የእኔ ዕድሜ ልክ ያህል በፊት የተደመደመ መሆኑን መርሳት ኣይቻልም።
እርግጠኛ ባልሆንም ቃሉ ያለዉ ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን ሊሆን ይችላል። የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉ አስርቱ ትዕዛዛቱን ሊሆን ይችላል። ግምቶቼ ስህተት ከሆኑ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።
የጻፈዉ ዉስጥ ጅገ ሎጋ ሲል ስለ ሌላ ሰዉም የተናገረ ይመስለኛል። የሎጋ መዉደቅ ማለቱ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ይህም ግምቴ ስህተት ከሆነ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።
ቦረና ድሬ ሊበን ሄዶ የጻፈዉ ዉስጥ የቦረና ቋንቋ ጭምር ስለሆነ ቋንቋዉን ከበሪሳ በፊት፣ ኣፄ ሀይለ ሥላሴ ስልጣን ላይ እያሉ፣ በፊደል የጻፈዉ መሆኑን ያመለክታል።
ለዚህ ብሎ ድሬ ሊበን ቦረና መሄድ ለምን እንደፈለገ ባላዉቅም ኣፄ ሀይለ ሥላሴ የይሁዳ አንበሳ ብለዉ በነገሡበት ዘመን ሎሬት ጸጋዬ ስለ ተሰደደዉ የኣፍርካ ፈረኦን ድሬ ሊበን ቦረና ሄዶ ማወደስ ፖለትካዊ ይዘት ያለዉ ይመስላል።
ይህ የኢትዮጵያ ሎሬት ኣፄ ሀይለ ሥላሴ የለፉለት የኣፍርካ ኣንድነት መዝሙርን የጻፈ ነዉ።
ሌላ የሚደነቅ ጥናቱ ቃልቻ የሚሉ እና ቃሉ የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ከብዙዎች ቀድሞ መሠረታቸዉ ኣንድ የሆነ ሕዝብ ነዉ የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ነዉ።
የእሱን ስራዎች ልዩ እና ድንቅ የምያደርገዉ የእየሱስ እና የመሓመድ ሃይማኖቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ተስፋፍተዉ የማይደፈሩበት ዘመን ከሁለቱም ዉጪ ሆኖ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰነበተን ቃሉ ማለቱ ነዉ።
ይህ ትክክለኛ የሬይነሳንስ ሰዉ ያደርገዋል። ትክክለኛ የሬይነሳንስ ሰዎች የክርስትና ሃይማኖት ዉስጥ ተዘፍዝፈዉ የኖሩ ወይም ስለ ክርስትና ሃይማኖት ክርክር ዉስጥ ኣልገባም የሚሉ ሳይሆን ከክርስትና ሃይማኖት ወጣ ብለዉ ባህል ኣጥንተዉ የክርስትና ሃይማኖት ዉስጥ ያሉ ስህተቶችን ለማረም የበቁ ቆራጥ ወንዶች ናቸዉ።
የኢትዮጵያዉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን ልዩ የምያደርገዉ ቃሉ ያለዉ ፋራኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን፣ መሆኑ ከተረጋገጠ የሙሴን ግብጣዊ ማንነት የመፋቅ ጥረትን ለካ ኣንተ ነህ በሚል ቃላቱ ያረመ መሆኑ ነዉ።
ብቸኛ የኢትዮጵያ ዕንቁ ያልኩኝ ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን፣ የቃልቻ እና ቃሉ የሚሉ ወንድማማች ሕዝብ ቃሉ ያለ ሌላ ሰዉ መኖሩን ስለማላዉቅ ነዉ።
ይህ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን ከሬይነሳንስ ሰዎች ዉስጥ ሃያሉን ያደርገዋል።
የእሱን ስራዎችን ሳላዉቅ ተመሳሳይ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ላይ ስለደረስኩ የእኔ ምስክርነት የሚናቅ ሊሆን ኣይችልም። ምናልባት ቦረና ድሬ ሊበን ሄዶ ቃሉ ያለዉ ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን ኣለመሆኑ ከተረጋገጠ የእኔ ምስክርነት የሚታረም ይሆናል።