Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6753
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኢትዮጵያን ኣጥንቶ አቅጣጫ ያሳያዉ ብቸኛዉ የኢትዮጵያ ዕንቁ

Post by Naga Tuma » 10 Oct 2025, 14:59

የኢትዮጵያ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን ስም ደጋግሜ የማነሳዉ የጎሳ ዝምድና ስላለን ኣይዴለም። ለዛ ቢሆን ኣያምርብኝም።

በስም ማወቅ እንጂ በአካል ተገናኝተን ኣናዉቅም። ስለ ታሪክ ስራዎቹ ኣላዉቅም ነበር።

የገዳ ስርዓትን የማክበር ግዜዉ ደርሶ ትዉልድ ሃገሩ ከዘመዶቹ ጋር ለማክበር እየተዘጋጀ ነበር የሚል ወሬ በልጅነቴ ሰምቼ ኣስተዋይ ቢሆን ነዉ ኣስብሎኝ ነበር። በምን ምክንያት እንደሆነ ባላዉቅም ተወርቶ የተጠበቀዉ ሳይፈጸም ቀረ።

እኔ የታሪክ ተመራማሪ ባልሆንም በርካታ ነገሮችን ኣንብቤ ስለ ኢትዮጵያ የጥንት ታሪክ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ ብዬ ኣስባለሁ።

እጅግ የደነቀኝ ስለ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህ ስራዎች ሳላዉቅ ተመሳሳይ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ላይ መድረሳችን ነዉ።

በእኔ አስተያየት የእሱ ግንዛቤዎች እና ድምዳሜዎች በስድስት ቃላት ለዘላለማዊ ታሪክ ተቀምጠዋል።

እ ኢ አ በ1964 ቦረና ድሬ ሊበን ሄዶ ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ለካ ኣንተ ነህ ብሎ ለታሪክ ኣስቀምጧል። ለዘለለሙ።

እኔ ለመጀመርያ ግዜ የሰማሁት ከጥቂት ዓመታት በፊት ነዉ። ከሰማሁት ግዜ ጀምሮ ልረሳዉ ኣልቻልኩም። ለፍቼ የደመደምኩት የእኔ ዕድሜ ልክ ያህል በፊት የተደመደመ መሆኑን መርሳት ኣይቻልም።

እርግጠኛ ባልሆንም ቃሉ ያለዉ ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን ሊሆን ይችላል። የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉ አስርቱ ትዕዛዛቱን ሊሆን ይችላል። ግምቶቼ ስህተት ከሆኑ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።

የጻፈዉ ዉስጥ ጅገ ሎጋ ሲል ስለ ሌላ ሰዉም የተናገረ ይመስለኛል። የሎጋ መዉደቅ ማለቱ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ይህም ግምቴ ስህተት ከሆነ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።

ቦረና ድሬ ሊበን ሄዶ የጻፈዉ ዉስጥ የቦረና ቋንቋ ጭምር ስለሆነ ቋንቋዉን ከበሪሳ በፊት፣ ኣፄ ሀይለ ሥላሴ ስልጣን ላይ እያሉ፣ በፊደል የጻፈዉ መሆኑን ያመለክታል።

ለዚህ ብሎ ድሬ ሊበን ቦረና መሄድ ለምን እንደፈለገ ባላዉቅም ኣፄ ሀይለ ሥላሴ የይሁዳ አንበሳ ብለዉ በነገሡበት ዘመን ሎሬት ጸጋዬ ስለ ተሰደደዉ የኣፍርካ ፈረኦን ድሬ ሊበን ቦረና ሄዶ ማወደስ ፖለትካዊ ይዘት ያለዉ ይመስላል።

ይህ የኢትዮጵያ ሎሬት ኣፄ ሀይለ ሥላሴ የለፉለት የኣፍርካ ኣንድነት መዝሙርን የጻፈ ነዉ።

ሌላ የሚደነቅ ጥናቱ ቃልቻ የሚሉ እና ቃሉ የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ከብዙዎች ቀድሞ መሠረታቸዉ ኣንድ የሆነ ሕዝብ ነዉ የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ ነዉ።

የእሱን ስራዎች ልዩ እና ድንቅ የምያደርገዉ የእየሱስ እና የመሓመድ ሃይማኖቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ተስፋፍተዉ የማይደፈሩበት ዘመን ከሁለቱም ዉጪ ሆኖ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰነበተን ቃሉ ማለቱ ነዉ።

ይህ ትክክለኛ የሬይነሳንስ ሰዉ ያደርገዋል። ትክክለኛ የሬይነሳንስ ሰዎች የክርስትና ሃይማኖት ዉስጥ ተዘፍዝፈዉ የኖሩ ወይም ስለ ክርስትና ሃይማኖት ክርክር ዉስጥ ኣልገባም የሚሉ ሳይሆን ከክርስትና ሃይማኖት ወጣ ብለዉ ባህል ኣጥንተዉ የክርስትና ሃይማኖት ዉስጥ ያሉ ስህተቶችን ለማረም የበቁ ቆራጥ ወንዶች ናቸዉ።

የኢትዮጵያዉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን ልዩ የምያደርገዉ ቃሉ ያለዉ ፋራኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን፣ መሆኑ ከተረጋገጠ የሙሴን ግብጣዊ ማንነት የመፋቅ ጥረትን ለካ ኣንተ ነህ በሚል ቃላቱ ያረመ መሆኑ ነዉ።

ብቸኛ የኢትዮጵያ ዕንቁ ያልኩኝ ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን፣ የቃልቻ እና ቃሉ የሚሉ ወንድማማች ሕዝብ ቃሉ ያለ ሌላ ሰዉ መኖሩን ስለማላዉቅ ነዉ።

ይህ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን ከሬይነሳንስ ሰዎች ዉስጥ ሃያሉን ያደርገዋል።

የእሱን ስራዎችን ሳላዉቅ ተመሳሳይ ግንዛቤ እና ድምዳሜ ላይ ስለደረስኩ የእኔ ምስክርነት የሚናቅ ሊሆን ኣይችልም። ምናልባት ቦረና ድሬ ሊበን ሄዶ ቃሉ ያለዉ ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለን ኣለመሆኑ ከተረጋገጠ የእኔ ምስክርነት የሚታረም ይሆናል።


Naga Tuma
Member+
Posts: 6753
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኢትዮጵያን ኣጥንቶ አቅጣጫ ያሳያዉ ብቸኛዉ የኢትዮጵያ ዕንቁ

Post by Naga Tuma » 05 Nov 2025, 19:46

ይህ የኢትዮጵያ ሎሬት፥

ኦሪት ዘፍጥረትን
ቃሉን
ፈረኦንን
አስርቱ ትዕዛዛትን
ሃይግሮፍሊክን
ፊደልን
ከለቸን
ካን
እግዝኣብሔርን
ገዳን
ገዳምን
አባ ብሌን
አቴቴን
አደይን
አብዳሪ ወይም አድባርን
የኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ እና እንግሊዘኛ ቃል ዉልን
በጀርመንኛ ፕፈርድ የሚባል ፈርደ ወይም ፈረስን
የአክሱም ዉድቀትን
እየሱስ ክርስቶስን
ነብዩ መሓመድን
ማርክሲዝምን
ታሪክም፣ ትንቢትም የሆነዉን ድሬ ሊበንን
እንደ ማንዴላን
እንደ ኣፄ ቴዎድሮስን
ምናልባትም የኣፄ ምኒልክ ቤተመንግስትን

በአስር ደቂቃዎች ዉስጥ እንደዚህ ወጥ ሆኖ የሚነበብ ማድረግ የሚችል የኢትዮጵያ ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ የሚባል ይሆን?

ለመሆኑ ሎሬቱ የሚኮላተፍ ነበረ በኣጋጣሚ ማለት ተስኖት በኣጋጫሚ ያለዉ ወይስ በኣጋጫሚ በማለት እንደ ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ በኮድ ነዉ የተናገረዉ?

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ እንደ ማንዴላ ያለዉስ ማንን ይሆን?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6753
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኢትዮጵያን ኣጥንቶ አቅጣጫ ያሳያዉ ብቸኛዉ የኢትዮጵያ ዕንቁ

Post by Naga Tuma » 22 Nov 2025, 14:48

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ ኣንተ ነህ
ተነባቢ የአስር ምስጥር

ያለዉ ማንን እንደሆነ መልሼ መላልሼ እራሴን እጠይቃለሁ።

ይህን ቪድዮ ሳላይ በፊት፣ ወደ ሃያ ዓመታት በፊት፣ መነቡና የተባለ መድረክ ላይ ዋቀ ቶክቸ ኤንደ ሞኖቴይዝም የሚል ረዘም ያለ የዉይይት ርዕስ ጽፌ ነበረ።

ሙሴ ከስደት በፊት ፈረኦ አክናተን የተባለ በጥንት ግብጥ እና አለም ላይ የመጀመርያዉ ሞኖቴይዝም ወይም ኣንድ ኣምላክ የሰበከ መሆኑን ኣንብቤ ታሪኩ ከገባኝ በኋላ ነበር።

ምናልባት ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንም ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ፣ ተነባቢ የአስር ምስጥር፣ ያለዉ ስለ ሙሴ አስርቱ ትዕዛዛት እና ከስደት በፊት ታላቅ ፈረኦ የነበረዉ አክናተን የነበረ ከሆነ ሎሬቱ እኔን ሳያዉቅ፣ እኔ የእሱን ጥናት ሳላዉቅ ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ ደርሰናል ማለት ነዉ።

ይህ ድምዳሜ የሰፊዉ የአለም ሕዝብ ሰፊ ታሪክ ድምዳሜ ይሆናል። የሕንድ እና የቻይና ክፍለ ዓለማትን ታሪክ ኣላጠናሁም።

ከዛ በተረፈ የጥንት ግሪክ ስልጣኔ የጥንት ግብጥ ስልጣኔ ተዋረድ ነዉ ተብሏል።

የእስራኤል ፕሮፌት የሆነዉ ሙሴም የጥንት ግብጥ ታላቅ ፈረኦ አክናተን ተዋረድ መሆኑ ተዘግቧል።

አዉሮፓ ዉስጥ የተጀመረዉ የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ የጥንት ግሪክ ስልጣኔ ተዋረድ ነዉ።

ይህ ማለት የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ በተዘዋዋሪ የጥንት ግብጥ ስልጣኔ ተዋረድ ነዉ ማለት ነዉ።

የአሜሪካ ዲሞክራሲ የጥንት ግሪክ ስልጣኔ እና አዉሮፓ ዉስጥ የተጀመረዉ የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ በተዘዋዋሪ የጥንት ግብጥ ስልጣኔ ተዋረድ ነዉ ማለት ነዉ።

የመካከለኛዉ ምስራቅ ሶስት ሃይማኖቶች ፈረኦ አክናተን ጥንት ግብጥ ዉስጥ የጀመረዉ ሞኖቴይዝም ተዋረድ ነዉ ማለት ነዉ።

የአስርቱ ትዕዛዛት ተሸካሚ እና ጠባቂ የሆነዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የፈረኦ አክናተን ሞኖቴይዝም ተዋረድ ነዉ ማለት ነዉ።

እኔ ዋቀ ቶክቸ ኤንደ ሞኖቴይዝም የልኩትን ርዕስ ሳልጀምር በፊት ጀምሮ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ስል የኖርኩኝ ኣንድም ከፈረኦ አክናተን ስለሚጀምር ነገር ነዉ።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ገዳ በኣዲስ ኪዳን ሆነ በቅዱስ ቁራን ኣያምንም ይላል።

የሬይነሳንስ ሰዎች ኣዲስ ኪዳን እና ቁራን ከምያስተምሩት ወጣ ብለዉ ሌላ ለማስተማር የሚጥሩት ያለ ምክንያት ኣይዴለም።

ለዚህ ደግሞ ፀረ ክርስትያን፣ ኣንቲ ሴሜትክ ተብለዉ ይወቀሳሉ።

እንደዚህ እየተባለ ፈረኦ አክናተን የሰፊዉ የአለም ሕዝብ ታሪክ መሠረት መሆኑ ሳይስተዋል ይኖራል።

ክርስትና እራሱ የፈረኦ አክናተን ሞኖቴይዝም ማለት ተዋረድ ከሆነ ክርስትያኖች የክርስትናን መሠረት ሳያዉቁ ይሰብኩታል ማለት ይሆናል።

ተንጠልጥሎ ያለ ጥያቄ ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ፣ ተነባቢ የአስር ምስጥር የተባለዉ ማነዉ ይሆናል።

ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ የተባለዉ ታላቁ ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለዉ፣ ከሆነ ያ ታላቅ ፈረኦ የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ እና የሁለተኛዉ ሬይነሳንስ መገናኛ ሆነ ማለት ነዉ።

Post Reply