በግብጽ የሚቀነባበረው የጽምዶ አባላት ግብጽ ፣ ኤርትራ ፣ ወያኔ ፋኖና ሸኔ የራሳቸውን ትርጉም ሊሰጡ ይችላሉ ። የኢትዮጵያ ጦር አዛዦች ለምን እስካሁን ዝም እንዳሉ የራሳቸው እስትራተጂ ሊኖራቸው ይችላል ።
ነገሩን ውጭ ሆነን ለምናየው ግን መከላከያ እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለመስጠቱ እጅግ ትክክለኛ ትክክለኛ እስትራተጂ ነው ።
ይህም ቦታ ሰጥቶ ግዜን መግዛት ይባላል።
በጦርነት ውስጥ የተለቀቀ ቦታ በማንኛው ግዜ መልሶ መያዝ ይቻላል ። ከአንድ የጦር መሪ የተወሰደን ግዜ ግን በፍጹም መልሶ መያዝ አይቻልም ።
አንድ ትክክለኛ የጦር መሪ መዋጋት ካልፈለገ አልዋጋም ብሎ ከጠላት ይርቃል። ሲጠቃ መመለስ ካልፈለገ ወደ ኋላ በማፈግፈግ የጠላትን ፕላን ያበላሻል ። ዞሮ ዞሮ ማንኛውም ዉጊያ በራሱ ፕላን እና እቅድ እንጂ ጠላት ባዘጋጀለት ወጥመድ ውስጥ አይገባል ።
ለምሳሌ ፋኖ ደጋግሞ ይህን ከተማ ያዘ ፣ያን ከተማ ተቆጠጠረ ምንትሴ ይባላል ። ይህ ማለት ምንም ማለት አይደለም።
ፋኖ የረባ ከተማ ይዞ ቢከላከል የራሱ የጦርነት አይነትና ድርጅታዊ ባህሪውን ለውጦ ችግር ውስጥ ከመግባት ያለፈ ፋይዳ አያመጣም ። የከተማ አስተዳዳሪ መሆንና ተወርዋሪ ጎሬላ መሆን እንደ ሰማይ ምድር የተለያዩ ስለሆነ ።
ለምሳሌ ፋኖ ተቆጣጥሮ ባንክ የሚዘርፍባቸውን ከተሞ መመልከት በቂ ነው። ይህን መሰል የሽፍታና የሌባ ድርጅታዊ ባህሪ በራሱ ለፋኖ ውድቀት እንጂ የድል ምልክት አይደለም። ይህ ሊሆን የቻለው ፋኖ ቦታ እንዲቆጣጠር በመተዉ ነው ፣ ይህ በራሱ ረቂቅ የዉጊያ እስትራተጊ ነው።
ስለዚህ የኢትዮጵያ መከላከያ ፈታ ዘና ብሎ ለቦታ መያዝ ሳይጨነቅ ግዜን ገዝቶ ሙሉ የጦር ፕላን ማድረጉ በራሱ የጦር አመራር ጥበብ ነው !
የስትራተጂ ሊቃውንት እንደ ሚሉት ጠላትህ ሲሳሳት አታርመው ፣ይልቅስ የበልጥ ስህተተ የሚሰራበትን ወጥመድ ዘርጋለት ነውና