Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12878
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by DefendTheTruth » 28 Jul 2025, 18:09

ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

ደበላ ና ደባል አንድ አይመስሉኝም፣ ዱባላም እንደዚያዉ።

Odie
Member+
Posts: 6024
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Odie » 28 Jul 2025, 19:17

DefendTheTruth wrote:
28 Jul 2025, 18:09
ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

ደበላ ና ደባል አንድ አይመስሉኝም፣ ዱባላም እንደዚያዉ።

Why do you have inferiority complex and jump to Amhara?
Your brother, Huresa/horus, DDT II last time told you ደበላ is a Gurage name. In Gurage there is a name "ደበልየ" from words ደበለ/ደፐረ:: In Amharic there is ደባል which sounds similar. Means these words are of semitic root. ኬኛ ከሆነ ምን እናደርጋለን:: ካልሆነ ወረሞ ሲዳቀል የስረቀው ቃል እንጂ የራሱ ቃል አይደለም

Dama
Member+
Posts: 6255
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Dama » 28 Jul 2025, 20:39

Odie wrote:
28 Jul 2025, 19:17
DefendTheTruth wrote:
28 Jul 2025, 18:09
ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

ደበላ ና ደባል አንድ አይመስሉኝም፣ ዱባላም እንደዚያዉ።

ካልሆነ ወረሞ ሲዳቀል የስረቀው ቃል እንጂ የራሱ ቃል አይደለም

Awesome!
Be mindful that Oromos are our closest neighbor and deserve to lead Ethiopia

Horus
Senior Member+
Posts: 39844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Horus » 28 Jul 2025, 20:43

DefendTheTruth wrote:
28 Jul 2025, 18:09
ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

ደበላ ና ደባል አንድ አይመስሉኝም፣ ዱባላም እንደዚያዉ።

ዲዲቲ/ናጋቱማ፣

ደበል ተራራ በፍጹም ከደበላ ጋር አይገናኝም ። ደባል የሚለው አማርኛና ጉራጌኛ ቃል እንደ ወረደ ደበላ ማለት ነው ። አብረው የተደበሉ ሰዎች ናቸው ደባሉች ። ለነገሩ አንተ የበቾ (የቸቦ) ወይም እዚያው የሰፈራችን ኦሮሞኛ ተናጋሪ ጉራጌ ነህ!!! ድበል ጨምር ፣ ድገም የሚሉት ክስታኔዎች ብቻ ናቸው ። ድበልሊ ጨምርልኝ ማለት ነው። መድብል አማርኛ ሲሆን ወድብል ክስታኔኛ ነው ።

ደበል ተራራ ከአረብኛው ጀበል የወረደ እንጂ ኦሮሞኛ ቃል አይደለም ። ጀበል ( ገበል፣ ደበል) ተራራ ማለት ነው ። ማለትም ከዳገትና ቅበት የላቀ ተራራ (ገገራ) ነው ። ቅበት ወይም ዳገት (ሂል) ማለት ነው ። ስለዚህ ደበል የሚለው ቃል እንደ ወረደ ተራራ ማለት ነው ። የሴም ቃል ነው ።

በነገራችን ላይ ላንጋኖ ፣ ነጌሌ ፣ ገናሌ፣ ሸበሌ፣ ሻላ የሚባሉት ስሞች በሙሉ የሴም ቃላት ናቸው !!!!

Odie
Member+
Posts: 6024
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Odie » 28 Jul 2025, 21:03

Dama wrote:
28 Jul 2025, 20:39
Odie wrote:
28 Jul 2025, 19:17
DefendTheTruth wrote:
28 Jul 2025, 18:09
ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

ደበላ ና ደባል አንድ አይመስሉኝም፣ ዱባላም እንደዚያዉ።

ካልሆነ ወረሞ ሲዳቀል የስረቀው ቃል እንጂ የራሱ ቃል አይደለም

Awesome!
Be mindful that Oromos are our closest neighbor and deserve to lead Ethiopia

I have no problem with civilized Oromos who respect others and demand respect. I, studied, lived and worked with them. My problem is with the savages, Kenga sayers, gudifecha lovers, ethnofascists who want to own everything because their count number is bigger. To be respected they have to stop the savagery, killing monks, babies, mothers, pregnant ladies the old, burning villages, massacring and attacking the weak. They should make their politic inclusive and cut their "me..me" cry. If not, they will be the losers.

Misraq
Senior Member
Posts: 16537
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Misraq » 28 Jul 2025, 22:34

መድበለ ቃላት በአማርኛ ምን ማለት ነው ወንድማችን በቀለ ሁሬሳ።

መድበለ ካድሬስ?

Odie
Member+
Posts: 6024
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Odie » 28 Jul 2025, 22:38

Misraq wrote:
28 Jul 2025, 22:34
መድበለ ቃላት በአማርኛ ምን ማለት ነው ወንድማችን በቀለ ሁሬሳ።

መድበለ ካድሬስ?
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Misraq
Senior Member
Posts: 16537
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Misraq » 28 Jul 2025, 22:51

Brother Odie, I was hoping Bekele Huressa to answer my question but I guess he won't :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 39844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Horus » 28 Jul 2025, 23:11

ሆረስ ዘ ኢትዮጵያ መች ሰውና እንሰሳ፣ አብርሆተ አይምሮና እብነ ጉነን ፣ ያገር አቢና ተላላኪ፣ አርበኛና ባንዳን መች መድበል ያቅበትና!!! ያገሬ ሰው ፍሬፈርስ ፈረንጁ ደሞ ሆርስሺት እንዲሉህ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 39844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Horus » 28 Jul 2025, 23:56

ድበላ የሚባለው ቃልና ጽንሰ ሃሳብ በዚህ ዘመን ብዙ የተሳሳቱ አጠቃቀም ላይ ውሏል ። ለምሳሌ የግጥም ወይም የመጣጥፎች ስብስብ ለማለት የእከሌ ግጥሞች መድብል ይባላል። ይህ ለመግባቢያ ሆነ እንጂ በመሰረቱ ስሁት ነው ። አንድን ነገር መድበል ያንን ወይም ተመሳሳይ ነገር እንደ ገና ማድረግ ነው ። መልከ ማሪያም ስንደግም ድርሳኑ አይለወጥም ፣ ተግባሩ (ንባቡ) ነው እንደ ገና የሚደገም። ስለዚህ የተለያዩ ነገሮች አብረው ሲሰበሰቡ መድብል አይደሉም ።

መድብለ ቃላት የተሳሳተ አጠቃቀም ነው ። የልዩ ልዩ ቃላት ስብስብ መዝገበ ቃላት እንጂ መድብለ ቃላት አይደሉም፤ አንዱን ቃል ደጋግመን ደጋግመን መዘገብ ስላልሆነ ። ዲክሽነሪ ወይም ዲክሽን አንድን ቃል ከሌላ ቃል መለየት እንጂ አንዱን ቃል መደጋገም ወይም ሁለት ቃላት አብሮ ማዳበል ስለአልሆነ ። ፣

እንኳንስ መድብለ ቃላት ድብልቅ ፣ ማደባለቅ፣ ድብልቅልቅ፣ ደባልቄ ወዘተ ወዘተ የሚባሉት ቃላት ሁሉ ባጠቃቀማቸው ተለመዱ እንጂ በስዋስዋቸው የተሳሳቱ ናቸው ። የተለያዩ ነገሮችን ማደባለቅ አንድ ነገር ደጋግሞ ፣ መጨመር ፣ ማከል ፣ አይደለም ። ለምሳሌ መደመር ማለትም በአንድ ነገር ላይ ሌላ መጨመር በድበል ነው ፣ ግን ማደባለቅ አይደለም

የሆነው ሆኖ ደበላ ግዕዝ አይደለም ለሚለው ዲዲቲ ስለ መድበልና ማደባለቅ ልዩነት ብዙም ግድ የሚሰጠው አይመስለኝም!

Meleket
Member
Posts: 4773
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Meleket » 29 Jul 2025, 06:55

ደበለ የሚለው ቃል ደብል መለኪያ አረቂ ወይ ዊስኪ የሚቀመቅሙ ጣጤዎች ሌላ ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ! የግዕዝ መዝገበ ቃላቶቻችን ግን ወደ ትግርኛችን እንዲህ ይተረጉሙታል።

ደበለ = አከበ፡ ኣኻኸበ፡ ጸንበረ፡ ሰብሰበ፡ ተብሎ ተተርጉሟል

መድብል = ኣኼባ፡ ጉባኤ፡ ባይቶ፡ ጥርናፈ፡ ስብሰባ፡ ማኅበር፡ ጕጅለ ተብሎም ተተርጉሟል።

ደብር = እምባ ፡ ከረን፡ ጎቦ፡ ጠረር፡ ኵርባ ወዘተ ተብሎ አንዱ ትርጉሙ ተራራንና ኮረብታንም እንደሚያጠቃልል ይገለጻል። ይመቻችሁ!

Horus wrote:
28 Jul 2025, 20:43
.....
ድበል ጨምር ፣ ድገም የሚሉት ክስታኔዎች ብቻ ናቸው ። ድበልሊ ጨምርልኝ ማለት ነው። መድብል አማርኛ ሲሆን ወድብል ክስታኔኛ ነው ።

ደበል ተራራ ከአረብኛው ጀበል የወረደ እንጂ ኦሮሞኛ ቃል አይደለም ። ጀበል ( ገበል፣ ደበል) ተራራ ማለት ነው ። ማለትም ከዳገትና ቅበት የላቀ ተራራ (ገገራ) ነው ። ቅበት ወይም ዳገት (ሂል) ማለት ነው ። ስለዚህ ደበል የሚለው ቃል እንደ ወረደ ተራራ ማለት ነው ። የሴም ቃል ነው ።

በነገራችን ላይ ላንጋኖ ፣ ነጌሌ ፣ ገናሌ፣ ሸበሌ፣ ሻላ የሚባሉት ስሞች በሙሉ የሴም ቃላት ናቸው !!!!

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12878
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by DefendTheTruth » 29 Jul 2025, 10:24

በርግጥ ደበለ ና ደብል የምለዉ የእንግሊዚኛዉ ቃል ተመሳሳ ትርጉም አላቸዉ፣ ሁለቱም የነጠላ ተቃራኒ ነዉ፣ ነጠላ መላት አንድ ማለት ነዉ፣ ደብል ማለት ደግም ሁለት ማለት ነዉ፣ እንደምናዉቃዉ። ደበላ ም በአፋን ኦሮሞ ልክ እንደዚሁ ከነጠላ የወጣ ማለት ነዉ፣ ዳግሞሽ እንደምባለዉ የአማርኛ ቃል።
Meleket wrote:
29 Jul 2025, 06:55
ደበለ የሚለው ቃል ደብል መለኪያ አረቂ ወይ ዊስኪ የሚቀመቅሙ ጣጤዎች ሌላ ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ! የግዕዝ መዝገበ ቃላቶቻችን ግን ወደ ትግርኛችን እንዲህ ይተረጉሙታል።

ደበለ = አከበ፡ ኣኻኸበ፡ ጸንበረ፡ ሰብሰበ፡ ተብሎ ተተርጉሟል

መድብል = ኣኼባ፡ ጉባኤ፡ ባይቶ፡ ጥርናፈ፡ ስብሰባ፡ ማኅበር፡ ጕጅለ ተብሎም ተተርጉሟል።

ደብር = እምባ ፡ ከረን፡ ጎቦ፡ ጠረር፡ ኵርባ ወዘተ ተብሎ አንዱ ትርጉሙ ተራራንና ኮረብታንም እንደሚያጠቃልል ይገለጻል። ይመቻችሁ!

Horus wrote:
28 Jul 2025, 20:43
.....
ድበል ጨምር ፣ ድገም የሚሉት ክስታኔዎች ብቻ ናቸው ። ድበልሊ ጨምርልኝ ማለት ነው። መድብል አማርኛ ሲሆን ወድብል ክስታኔኛ ነው ።

ደበል ተራራ ከአረብኛው ጀበል የወረደ እንጂ ኦሮሞኛ ቃል አይደለም ። ጀበል ( ገበል፣ ደበል) ተራራ ማለት ነው ። ማለትም ከዳገትና ቅበት የላቀ ተራራ (ገገራ) ነው ። ቅበት ወይም ዳገት (ሂል) ማለት ነው ። ስለዚህ ደበል የሚለው ቃል እንደ ወረደ ተራራ ማለት ነው ። የሴም ቃል ነው ።

በነገራችን ላይ ላንጋኖ ፣ ነጌሌ ፣ ገናሌ፣ ሸበሌ፣ ሻላ የሚባሉት ስሞች በሙሉ የሴም ቃላት ናቸው !!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 39844
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ደበላ የኦሮሚኛ ቃል አይደልም፣ የአማረ እንጂ ተብለንም ነበር፤ ደበል ስ? ድገም ለማለት ነዉ በአፋን ኦሮሞ።

Post by Horus » 29 Jul 2025, 12:37

መለከት፣
አው የቡና ቤት አሳላፊዎች ዊስኪ ወይም ኮኛክ ስታዝ 'ነጠላ ነው ወይስ ዱብል' ብለው ይጠይቁ ነበር ። ዱብል ካልክ የጠርሙሷ ጡጦ ሁለት ግዜ ትሸናለች!!

እንደ እኔ እምነት 'ደብር' ስረ ቃሉ ድበል (ድገም) የሚለው ሳይሆን ሌላ ነው ። ደብር ስረ ትርጉሙ 'መቀመጫ' መንበር፣ መደብር፣ መኖሪያ፣ ሰፈር፣ መደበሪያ ፣ ልክ እንደ ገዳምና ዳሞት በአጠቃቀምና በልማድ ተራራ ላይ በተደበሩት ሰፈሮችና ገዳሞች ሳቢያ ደብር መኖሪያ ሰፈርና ደብር ጀበል ተራራ የተያያዙ ነው የሚመስለው እንጂ መድበል ትርጉሙ ፍጹም ከተራራ የራቀ ነው። እርግጥ መድብል መሰብሰብ የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል በዘልማድ።

ደብል ፣ ደበል ወይም ድበል በትክክልም ከላቲኑ double ጋር አንድ ነው ። ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ግዜ እዚህ ፎረም ላይ ጽፌበታለሁ ። ይህም የሆነው ከ1500 ጀምሮ የላቲንና ግዕዝ መዝገበ ቃላት ተሰርቶ እጅግ ብዙ ፕሮቶ ኢንዶ አውሮፓ ስረ ቃላት እና የኛ ግዕዝ ተመሳይ ኢቲሞሎጂ ይጋራሉ። እኩል ማለትና ኢኳል አንድ ናቸው። ወረብ ማለትና ኦርቢት አንድ ናቸው ። በኔ ግምት ስከ 20% ይደርሳል። አንድ ቀን ሰው ሰራሽ ክህሎት AI በትክክል ይመልሰዋል።

ለምሳሌ ጉብታ ፣ጎባ ፣ ጉብ ያለ ቦታ ማለት ነው ። እኛ ቅበት የምንለው ማለት ነው ። ባሌ ጎባ እንደ ሚባለው ። በኔ ግምት ጥንት የሰፈርና ያገር ስብሰባዎች እዚያ ጉብታ ላይ ይደረግ ስለነበር ነው ጉባኤ የሚለው የስብሰባ ቃል የመጣው እንጂ ጉብታ ከመድብል ጋር በኢቴማ ስለተያያዙ አይደለም።

Post Reply