(ድንች በራስህ እጅ ተክለህ፣ ቦኋላ ላይ መደቅደቂያህን ይሰብርብሃል፣)
የራሴን እድል በራሴ አወስናለሁ ማለት፣ ማንንም አልለማመጥም፣ ራሴን እችላለሁ ማለት ነዉ፣ ሌላዉ መጥቶ ስላራሴ እንደልወስን አለፍቅድም ማለት ነዉ።
ታዲያ የሰላሌ ሕዝብ እንዴት ነዉ ዛሬ የራሱን እድል በራሱ መወሰን አቅቶት መንገድ ላይ ወጥቶ ሰላም ስጡን ብሎ የምለምነዉ? የምማፀነዉ? ማን መጥቶ ሰላሙን ያድለዉ እንግዲህ? መንግስት? መንግስት ይድረስልን የምባለዉ ወራሪ ሀይል ስመጣ ብቻ ነዉ፣ የአከባቢዉ ሕብረተሰብ የራሱን አከባቢ ሰላም ማስጠበቅ እንዴት ተሰናዉ? ሚሊሻ የለዉም፣ ከለዉ የሚሊሻ ተልዕኮ ምንድ ነዉ? ሚሊሻ ከአቀተዉ ፖሊስ ምን ይሰራ ነበር? የራሱን ሰፈር እንዴት ነዉ መጠበቅ ያቃተዉ? ይህ ጉዳይ በደንምብ ልጤን ይገባል።
የራሱ ጥፋት የለበትም? ከራሱ የወጣን ጉጠት ወደ መስመር መመልስ አቅቶት፣ መምከር ተስኖት፣ ዛሬ ከአቅም በላይ ስሆንበት አረ ድረሱልን ማለት እንዴት ያዋጣል? የራስህ ጥፋት አይደልምን?
ራሴን በራሴ ለስተዳድር አላልክም? ታዲያ አሁን ደግሞ ማን መጥቶ የአንተን ፀጥታ እንዲያስጠብቅልህ ትፈልጋለህ? ለሕዝብ ክብር አለኝ፣ ሕዝብ አዋቂ ነዉ፣ ሕዝብ የምሆነዉን ና የማይሆነዉን ራሱ ላይቶ ያዉቃል፣ ነገሩ መንገዱን ሥስት ለምን ይህ ነገር ወዴት ልወስደን ይችላል ብሎ አይጠይቅም አንድ ሕዝብ?
ከራስህ መሓል የወጣን ጠማማ በጊዜ መስመር ሥስት፣ ይህ ሕዝብ እንዴት ነዉ ቁጭ ብሎ ስያይ የነበረዉ? የምሆነዉን አያዉቅም ማለት ነዉ? የአገር ሽማግሌዎች የት ሔዶ ነበር? የአገር ሽማግሌን አልሰማም ብሎ ይሁን ራሱ ሕዝቡ? እንደሱ ከሆነ ደግሞ ነገሩ መስመሩን የሳተዉ እዚያ ላይ እኮ ነዉ።
እንደሱ ከሆነ ደግሞ ይህ ሕዝብ ከሁሉ ነገር በላይ አሁን የራሱን የአገር ሽማግሌ እግር ላይ ወድቆ ይቅርታ መጠየቅ አለባት፣ መካስ አለበት።
መንገድ ላይ እየሄዱ እግዚዮ ማለት ለሽማግሌዎች ይቅርታና ካሳ ከተከፈላቸዉ ቦኋላ መሆን አለበት፣ ከሆነም።
መጀመሪያ ላይ ሆይ ሆይ ብለህ አብረህ ወጥተህ አሁን ነገሩ ከአቅም በላይ ስሆንብህ እግዚዮ ብሎ መንገድ ላይ መማፀን ብልህነት ወይም እዉቀት አይመስለኝም። የራስህ ልጅ ነዉ እያደማህ የለዉ፣ ይህን መረዳት ያስፈልጋል፣ የተከበርከዉ የአገሬ ሰዉ!
ነገሮችን በቅጡ መረዳት ለመፍትሔዉ የቅድሚያ እርምጃ ነዉ፣ እግዚዮ ሳይሆን ስህተትህን አስቀድመህ ተረዳ፣ የተከበርከዉ የአገሬ ሰዉ! እግዚያብሔርም የምደርስልህ፣ የራስህን በር ራስህ ዘግተህ ወደ መኝታ ስትሄድ ነዉ፣ በርህን ከፍተህ ማንም እንድገባበት ከአደርግክ ቦኋላ እንዴት ነዉ እግዚያብሔር አልደረሰልኝም ብለህ መንገድ ላይ ወጥተህ የምትማፀነዉ?
የአገሬ ሕዝብ ከዚህ በላይ ያዉቃል ብዬ እጠብቃለሁ!