ውሃ የማይቋጥረው ያንተ ባዶ ፉከራና የጎረቤት ሃገሮችን የመስደብ አባዜ ነው።
<> የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጀግንነት ከበሰበሰው የኦሮሙማ ሰራዊት ጋር ማወዳደር ውስልትና ነው። ኦነግ-ሸኔ ህዝብ ሲያርድ፣ ወንዝ ውስጥ ፈንጅ በድሮን እየጣሉ፣ ጃልመሮን አንዴ ለጥቂት ሳትነው ሌላ ጊዜ ደግሞ ገደልነው የሚሉ ቀጣፊ ጉዶች፣ ድንበር ማስከበር አይደለም የአዋሽ ወንዝን መሻገር አይችሉም።
<> ፋኖን ትደግፋላችሁ እየተባሉ በካድሬ ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው ባለሀብቶች አንድ በአንድ ቀስ እያሉ ወደ ጎረቤት ሃገሮች ቤተሰቦቻቸውን እያስወጡ ነው። ሆዳም ካድሬ ወይንም የዪቱብ አራጋቢ ካልሆነ በስተቀረ፣ የኦሮሙማን ስህተት ለማረም ጦር ሜዳ የሚዘምት አማራ እንደማይኖሮ በጣም እርግጠኛ ነኝ።
<> ሃገራችን ዛሬ ህዝብ በጠኔ የሚያልቅባትና በእርዳታ ተደጋግፋ የቆመች መሆኗን ለመናገር አትፍራ።
<> ኦሮሙማ የጦር መሳሪያ መግዛት አይደለም፣ የዕቃ መለዋወጫ ማቅረብ አልቻሉም በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት።
Abere wrote: ↑22 Feb 2024, 10:33ሆረስ፤
እኔ ከዚህ ሰሞነኛው የፈረንጆቹ ምሥራቅ አፍሪካ ንዑሳን የባህር ማዶ ግዛቶች (HoAs" ግርግር የወሰድኩት ትልቅ ነጥብ ቢኖር ኢትዮጵያ ኃይሏ የቱን ያህል ዓለምን እንደሚያሸብር እና ታላቅ የፓለቲካ እና የሚሊታሪ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገር አሁንም እንደ ጥንቱ መሆኗን ነው።
---አሁን እነኝህ "HoAs" የተባሉ ትናንሽ ፈላ (new born) የቅኝ ግዞች ቱርካ ከጣልያኗ ግዛት ሶማሊያ ጋር ግንኙነት አደረገች ሲባል የድሃ ሰርግ ጡሩምባ የበዛዋል አይነት ልብ ውልቅ ድልቂያ አበዙ። የድሃ ሰርግ ድግሱ ባዶ ነው ግን ሰንጋ እና ጠጅ የተጣለ፤ ጠላ የተዘለለ ለማስመሰል የጡሩምባው ግርግር ጆሮ ይበጥሳል። ቱርካ ይህን ያህል ዕብድ አገር አይደለች አይኗ እየዬ ከማትወጣው አረንቋ (quagmire) አትገባም። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ግዙፍ ሀይል እና ተጽኖ ፈጣሪ (regional super power) ከመሆኗ አኳያ ቱርክ ተሰሚነቷን አልሻባብ እንደ አረም አንቆ ከያዛት ሶማልያ ንዑስ ጥቅም አታጣፋም። Turkey will never ever put herself on a direct collision course against Regional Super Power, Ethiopia - it is a no brainer.
---ይህ ማለት ግን አንዳንድ ጥቅማጥቅም ድጎማዎች ለሶማሊያ አታደርግም ማለት አይደለም። እነኝህ ድጎማዎች ግን በእራሱ አልሻባብ ይጣፋሉ ( cancels out, zero net gain) - ሶማልያ ከዚያው የቀውስ አዙሪት ትቀጥላለች። የቱርኮች የአጭር ጊዜ መዋዕለ ንዋይ አዋጭነቱ እንድሁ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባው ይችላል።
---ሶማልያ በአለም የፓለቲካ ውድቀት ( failed state) አስተምሮ ተምሳሌት ብቻ ሳትሆን የአካባቢ ውድቀት ( ecological failure) ተምሳሌት ልትሆንም ትችላለች። ቱርካ በአጭር ጊዜ ትርፍ እና ምርት ለማገኘት ስትል የአካባቢውን ከፍተኛ ብክለት አድርሳ የበለጠውን ደረቃማ አድርጋው ትሄዳለች። የአፍሪካ ቀይ ባህር እና ሚድትራንያን ዳርቻዎች የበለጸጉት አገራት የአደባባይ ቆሻሻ መድፊያ ( open defecation site) መሆኑ ግልጽ ነው። ቆሻሻ ተጭኖ መጥቶ የሚደፋበት ከሆነ ቆሻሻው ከዚያ ከባህር ዳርቻው የሚወጣ ከሆነ ወደ ቱርክ ሳይሆን ሞቋድሾ ላይ ይሰጣል ማለት ነው፡:
---በመጨረሻ ግን የሶማሊላንድ ህዝብ በመስዋዕትነቱ ከ33 አመታት በላይ ያረጋገጠውን ነጻነት እና የግዛት ልኡላዊነት ማንም በሃይል ሊቀይረው አይችልም። ቱርክ የዚህን አስቸጋሪነት ለዘመናት ከኩርዲስታን (Kurdistan -PKK) ጋር እያደረገች ያለው እና አሁንም አሸንፋ መቋጫ ያጣችለት ጉዳይ ነው። ዘላ የአለም አሸባሪ አልሸባብ ከሚርመሰመስበት ሲዖል ሶማሊያ እንድሁ አትገባም - ትንሽ ሞጭልፋ ትሾልካለች።
---ውሃ የማይቋጥረው የበርካታ ጸረ-ኢትዮጵያዊያን አስተያየት ግን ይገርመኛል። ጨለምተኝነትን ለመፍጠር ሰማይ ተደረመሰ ዋ ይላሉ። ቂቂቂ
የተደረመሰው በኢትዮጵያ ላይ ሳይሆን ከእነርሱ እግር ስር ነው። ኢትዮጵያ ታላቅ አገር እና አሸናፊ መሆኗን ስለሚያውቁ እርሷን ለመጣል ፕሮፓጋንዳ ለመስራት እንጅ ከዚህ የሚመጡት ደካማ አገር ብትሆንማ ከዚህ ፎረም ዝር አይሉም። 50 አመታት ታገሏት፤አጭበረበሩ፤ አሁንም ይሞክራሉ የበግ ለምድ ለብሰው ግን እንደ ከሰሩት ሁሉ ደግመው ይከስራሉ።