DefendTheTruth: ጉራጌኦሮሞች እነዚህ ናቸው!
ደሞ ዱላ አይሸከሙም!
Re: DefendTheTruth: ጉራጌኦሮሞች እነዚህ ናቸው!
ሶዶ? ማረቆ ነው ክስታኔ?
Re: DefendTheTruth: ጉራጌኦሮሞች እነዚህ ናቸው!
ሶዶ የአገር ስም ነው (ክፍለ አገር እንደ ማለት ነው)፣ እነዚህ የክስታኔ ጉራጌና ኦሮሞ ቅይጦች ናቸው እኛ ላሌጌ እንላቸዋለን ከክስታኔ ሰሜን ስለሆኑ! ላለጌ ማለት ሰሜን ማለት ነው ። እስከ አለምገና ገጃ ያሉት ናቸው ። ማረቆ የኦሮሞ ሳይሆን የሃዲያና መስቃን ጉራጌ ቅይጦች ናቸው ።
ክስታኔኛ ይህ ነው ፤
መስቃንና ክስታኔ ኦልሞስት አንድ ናቸው ፣ እኔ ሙሉ በሙሉ መስቃንኛ እሰማለሁ ፣ ይህ ነው መስቃን ጭፈራው በትንሹ ዝግ ይላል ።
Last edited by Horus on 17 Jan 2024, 04:09, edited 2 times in total.
Re: DefendTheTruth: ጉራጌኦሮሞች እነዚህ ናቸው!
ሰምተህ ከሆነ ጭፈራው ብቻ ሳይሆን ሊሪክሱ ላሌ ዬቦላሌ ይላል! ያ የክስታኔኛ ዘፈን አዝማች ነው ። የኤርምያስ ለገሰ ዘመዶች ገጃ አለም ገና ልክ እንደዚህ ነው የሚጨፍሩት ፣ ያንን ነው በመጻፉ የጻፈው ባላገር ዘመዶቼ ጋ ሄጄ ንግግራቸው ኦሮሞኛ ጭፈራቸው ጉራጌኛ ነው ብሏሎ!
አሁን ፈጽሞ ረስተውት ነው እንጂ ገላኖች፣ ያያዎች (የበቾ የማሞ ወልዴ ዘሮች) ሁሉ ሁሉ ግንዳቸው ጉራጌ ነው ። ከዚያም ጨቦን ይዘህ ወንጪን ደንዲ ብለህ ወሊሶ ትገባለህ !!! ብዙዎቹ አሁንም ባህላቸው እንሰትና ቆጮ ነው !!