Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10173
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

ሰባተኛው ንጉሳችን ሆይ

Post by Digital Weyane » 23 Oct 2023, 01:50

<<ንጉስ አይከሰስም፣ ሰማይ አይታረስም>> የሚለዉ አባባል አይመቸኝም ይቅርታ። :roll: :roll:

አብይነትዎ ሆይ፣

ፈጣሪ ባርኮ የሰጠን ለም የኢትዮጵያ መሬት እያለን የምግብ እርዳታ በመለመን በአለም አንደኛ ነን። የባህር ባለቤት ብንሆን ኖሮ ባህሩ ከፈረንጆች አገር የምግብ እርዳታ ዎደ ኢትዮጵያ ከማስገባት ውጪ ሌላ የሚሰጠን ጥቅም የለውም። ለኢትዮጵያ ሕዝብም የሚፈይደው ነገር የለም። ለልመና እጅን መዘርጋት እንጂ የባህር በር ባለቤትን መሆን አይስፈልግም እና የሰሞኑ ንግግርዎ ትክክልም ጤነኛም አይደለም። :roll: :roll:

Axumezana
Senior Member
Posts: 19122
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ሰባተኛው ንጉሳችን ሆይ

Post by Axumezana » 23 Oct 2023, 01:51

Ascari boys,

Rest in peace!

Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10173
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ሰባተኛው ንጉሳችን ሆይ

Post by Digital Weyane » 23 Oct 2023, 02:42

አብይነትዎ ሆይ፣

በትግራይ አንድ ነጥብ አምሥት ሚሊየን ህፃናት እና ወጣቶች በውክልና ጦርነት ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ተለይተውናል። ትግራይ ህፃናት እና ወጣቶች የሌሉባት ክልል ሆናለች። ሃዘናችንን ሳንጨርስ ለሌላ ዙር መተላለቅ ግፋ በለው ውረድ በለውን እያሉ ሲያንጎራጉሩ መስማት ሃዘናችንን ከባድ ያደርገዋል።

Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10173
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ሰባተኛው ንጉሳችን ሆይ

Post by Digital Weyane » 23 Oct 2023, 03:54

አብይነትዎ፣

ከባለፈው የወያኔ ስህተት መማር ብልህነት ነው። ወያኔ ዎገኖቼ ታላቋ ትግራይን እንመሰርታለን በሚል እቅድ አንድ ነጥብ አምሥት ሚሊየን የትግራይ ወጣቶችን እሳት ውስጥ ማግደው ጨርሰው ትጥቃቸውን ለመፍታት ዎደ ደቡብ አፍሪካ ነጎዱ። የእርሶ እጣ ፈንታም ተመሳሳይ እንደሚሆን ጥርጣሬ የለንም። ፈጣሪን በመካድ የማይክ ሀመር አገልጋይ መሆን በመምረጥዎ እጅግ ትልቅ ኃጢአት ነው የሰሩት። ይቅርታ የማይደረግለት ኃጢአት ነው። በኢትዮጵያ ባንዳነት እስከ 7 ትውልድ ድረስ ያስረግማል። :roll: :roll:

Post Reply