Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4052
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!

Post by Meleket » 23 Aug 2023, 09:25

ወዳጃችን Horus
አግዐዘ የሚለው የግዕዝ ቃል አንዱ ትርጉሙ ነጻ አወጣ፡ ነጻ አደረገ፡ ነጻነትን አጐናጸፈ፡ ነጻነትን አመጣ፡ ሐርነትን ሰጠ፡ ነጻ ለቀቀ ወዘተ ተብሎ መተርጐሙን አንብበናል። ታዋቂው ጀርመናዊ የግዕዝ ሊቀሊቃዉንት ዲልማንም እንዲህ ብሎ አብነቶችን አስቀምጧል፦

ያግዕዛ ውስተ ገዳም። መኑ አግዐዞ ለሐለስትዮ። ትፌንዎ ኣግዒዘከ። አግዐዘታ ለእንታክቲ ወለታ። ያግዕዝ። ከመ ያግዕዝዎሙ እምቅኔሆሙ። ኢታህጕሎ ዕሴቶ ከመ ታግዕዞ። ያግዕዝ ቅኑያነ። በእንተ አግእዞ ገብር።
. . .
አግዐዘነ እምኅጢኣት ወሞት። አግዐዘነ እምተቀንዮ ለኅጢኣት፡ እምአርዑተ ኅጢኣት።

ለዚህም ነው ከዚህ በፊት እንዲህ በማለት ለመግለጽ የሞከርነው
Meleket wrote:
29 Jul 2023, 02:17
ግሩም ትንታኔና ምርምር ነው ወንድም Horus ቀጥልበት፦
. . .
ኣግኣዚ የሚለውን ቃል እግዚእ፡ ጎይታ፡ ገዛኢ ከሚለው ጋር ያዛምዳሉ ኣንዳንድ ተመራማሪዎቻችን፡ ትክክለኛው ጌታችን ደግሞ ከኃጢኣትና ከባርነት ቀንበር ነጻ እውጪ መሆኑን መቼም ሁላችንም ኣንስተውም፡ እንስማማበታለን።
Horus wrote:
18 Aug 2023, 13:00
መለከት፣
እኔ ዚዚዚ ጭቅጭቅ አልወድም። ኢዛና ምን ማለት እንደ ሆነ ዛሬ አውቀሃል ።ያ ነው የኔ አላማ ። አጋዚ ነጻ አውጪ ማለት ነው ብለህ ኖረሃል። አይደለም ። አጋዚ ጦረኛ እንጂ ነጻ አውጪ ማለት አይደለም ። ዛሬ ጋዝ ማለት ጦር ማለት ነው የሚል ጉራጌ ብቻ ነው። ግድር ዛሬ ትርጉሙን ነግሬሃሉ ግድር ዛረ ተራጉራጌኛ ቃል ነው ትግርኛ አይደልም ። አበቃሁ !! ይህን ምልልስ እዚህ አናብቃው! ሰላም
እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች አግዐዚ ማለት ነጻ አውጪ ማለት ነው ስንል በምክንያት ነው!

ኬር!
:mrgreen:

Post Reply