Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4052
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!

Post by Meleket » 16 Aug 2023, 12:25

Selam/ግሩም ጭዋነትን የተላበሰ መላ ምት ነው!

ከዜና መዋእሉ ዖዚያን በፊትም ኦሪት ዘኁልቍ 26፡16 ላይም እኮ ከጋድ ልጆች መካከል ኦዝኒ ተጠቅሷል ኦዝናውያንም ይላቸዋል ልጆቹን መሆኑ ነው መሰል። ትርጓሜውንም ከዚህ በፊት እንደገመትነው "እዝኒ" ማለትም ከመስማትና ከጀሮ ጋር ኣያይዘውታል።https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=325878&

https://www.biblestudytools.com/dictionary/ozni/

Ozni

(hearing ), one of the sons of Gad ( Numbers 26:16 ) and founder of the family of the Oznites. ( Numbers 26:16 )

Selam/ wrote:
16 Aug 2023, 05:30
ዒዛና የሚለው ቃልስ ዖዚያን ከሚባለው ቅን የይሁዳ ንጉሥ ስም ጋራ ይያያዝ ይሆን እንዴ? ዖዚያን የነገሰው ከዒዛና 1000 ዓመት ገደማ በፊት ሲሆን በጣም የተሳካለትና ስመ ጥሩ ንጉስ ነበር። ሆኖም የካህናትን ሥራ ለመሥራት መቅደስን በመድፈሩ ምክንያት በነገሰ በ52 ዓመቱ በስጋ ደዌ ተመቶ ሞተ።

Meleket wrote:
16 Aug 2023, 03:38
Horus wrote:
14 Aug 2023, 13:05
Meleket wrote:
14 Aug 2023, 11:47
Horus wrote:
12 Aug 2023, 01:43
. . .
(6) እንዲሁ በጉራጌኛ ሰነ (ሸነ) ኃይል ማለት ሲሆን
. . .
ለፈገግታ ያህል ነው "ሸኔ" ማለትስ ምን ማለት ነው? እየተዝናናን መመራመር ነው እንጂ!
መለከት፣
አው ሃውዜን የሚለው ቃል ስር ዘብ የሚለው ነው ፤ ግ ን መነሻው ኧዣ(እዝ) የሚለው ሳይሆን ሌላ ነው። የእጅ መዳፍ ወይም መያዝ የሚል ስረቃል ነው ያለው ። ሸኔ በኦሮሞፋ ምን ማለት እንደ ሆነ ስለማላውቅ ስረቃሉ ምን እንደ ሆነ መናገር ዝም ብሎ ግምት ይሆንብኛል ።

ይልቅስ ይችን ልመርቅልህ (ልጨምርልህ)። ኢሳያስ ማለት ኢዛና መሆኑን ገምተህ ነበር ወይ? ኢዛ(ና/ያ)ስ (ኢዛንያስ) ማለት ነው ። ያስ የሚለው የግሪክ ኢንፍሉወንስ ነው ። ልክ ኤርሚያስ፣ እዝክያስ፣ ሚልኪያስ እንደ ሚባለው ። ኢሳያስ ማለት እኛ ንጉሴ፣ መኮንን፣ መስፍን እያልን እንደ ምንጠራው ማለት ነው ።
ግሩም መላ ምት ነው። ወንድም Horus ምርቃትህ ደግሞ ታዝናናለች።

ኢዛና ማለት ንጉሥ መስፍን መኮንን ወዘተ ማለት ነው የሚል ‘መፍቻ ቁልፍ’ ካመጣህ በኋላ ኢሳያስ ማለትም ኢዛንያስ ማለት ነው ብለህናል። ትርጉሙም እንደ ኢዛና ነው ካልከን ዘንዳ፤ “ይ” የተቀላቀለበትና “ይ” ያማከለው ኢሳያስ ማለትም 'ኢሳያስ' ማለት ምን ማለት ነው በነካ እጅህ እስቲ ተርጉምልን።

ኢሳያስ = ኢዛንያስ = ንጉሴ መኮንን መስፍን ብለህናል፤ ኢዛና ንጉሠነገሥት አልነበረምም ብለህናል።

ኢሳይያስ = _ _ _ _ _ መኮንነ መኳንንት ብለህ ተርጉምልንና አስቀን እንጂ። የቅዱስ መጸሓፉ ኢሳይያስ ትርጉሙ እንዳንተው የኢዛና ትርጉም ነውን?

ኢዛናና ሳይዛናም ሲባል እንሰማለን ሳይዛና ማለትስ ምንድነው ትርጉሙ?

ኢዛና የሚለውን ቃል ከ1600 ዓመታት በኋላ ዲኮድ እንዳደረግከው ገልጸህልናል፡ ቃሉ ግን ከዚያ በፊት በጭራሽ ኣልነበረም ማለት ነውን? ታዲያ ክየት ፈለቀ? ከ1600 ዓመታት በፊትስ ንጉስ መስፍን መኮንን ወዘተ የሚሉት ቃላቶች በ"ኢዛና" ኣይጠቀሱም ነበር ማለትህ ነውን? እስቲ አብራራልን።

ጥንታዊው ቃል "ኢዛና" ነው ወይስ "ኢሳይያስ"፡ "ኢዛና" የሚለውን ቃል ከ1600 ዓመታት በኋላ ዲኮድ እንዳደረግከው ነው የገለጽክልን፡ "ነብዩ ኢሳይያስ" ደግሞ ከ2000 ዓመታት በፊት ስለተወለደው ስለክርስቶስና ስለ እናቱ ስለድንግል ማርያም አስቀድሞ በኦሪት የነገረን ተጽፎ እኛጋም ደርሷል። ጥንታዊው ቃል ግን ዬትኛው ነው!

እላይ የሃውዜንን መላ ምትህን ሰምተነዋል፤ የነ ዓዜን ዃዜን፡ ምድሪዜን፡ ቢዘን፡ ባዜን፡ ሽመዛና(ሽመጃና)፡ ዛና ወዘተ ትርጉምስ ከኢዛና ጋር ግንኙነት አለውን? እስቲ መላ ምቶችህን ኣካፍለን። ዲኮድ ካደረግህ ኣይቀር በደንብ አድርገህ ዲኮድ አድርግልንና እዬተዝናናን እንማማርባቸው ብለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
:mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 34739
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!

Post by Horus » 16 Aug 2023, 14:25

ሰላም፣
ኦዚያን ከኢዛና ጋር ተመሳሳይ አጠቃቀም ይመስለኛ፣ በእብራይስጥ ። ከላይ እንደ ኤቪደንስ ሊስት ካደረኳቸው ውስጥ ቁ 1 ላይ ያለው ሆሳዕና ሆሻና የሚለው ነው ። ኢራኖች ሻህ እና ሁሻን እንደ ሚሉት ነው ። የሳንስክሪቱም ከዚያ ይቀርባል ። ቋንቋዎች ግንዳቸው አንድ ሆኖ በዲያሌክት የሚለያዩት በዚህ መንገድ ነው ፤ ከቃሉ ፊትና ጭራ ላይ አዲስ ድምጽ በመጨመር፣ አንዳንዴ በዘልማድ አዲስ ድምጽ መሃል ላይ በመሸንቆር ። እብራይስጥ በጣም የተጠና ቋንቋ ስለሆነ የሚያውቁ ሰዎን ኦዚያን ዛሬ ላይ ያለውን ትርጉም ጀባ ቢሉን እናመሰግናቸዋለን ።

መለከት፣
እኔ ኢሳያስ ማለት መስፍን መኮንን ማለት አላልኩም። ያልኩት ዛሬ ላይ መስፍን፣ መኮንን፣ ንጉሴ፣ ወዘተ እንደ ተራ ስም እንደ ምንጠቀመው አሳያሳም በዚያ መልክ ነው ጥቅሙ ለማለት እንደ ምሳሌ ነው የጠቅስኳቸው ። አቶ አፈወርቂ ኢሳያስ የሚለውን ስም ከመጻፍ ቅዱስ አኝግተውት ይሆናል። ኢዛና (ሂሻና) ወደ ኢሳያስ የሚለውጠው ግሪክ ነው ። መጻፍ ቅዱስ ከሴም ቋንቋዎች ወደ ግሪክ ለተተረጎመ። ኧዣ ፣ ሻህ ፣ወይም ኢዛና የሚለው ቃል የተወለደው ጥንታዊ ግብጽ ነው ብዬ ነበር። እዚህ ፎረም ላይ ከግብጽ ወደ ሴም እንዴት ኢቮልቭ አደረገ የሚለው ቴክኒካል ገለጻ እዚህ አልሰጥም። ስለማያስፈልግ።

በቀሩት ቃላት ላይ እኔ የትግርኛ ተናጋሪ ስላልሆንኩኝ በማላውቀው ቋንቋ ላይ ኢቲሞሎጂካልም ሆነ ፊሎሎጂካል ግምት አልሰጥም ። ማለት አንተ እንደ ምትለው መላ ምት አላደርግም ። የኢዛና ዲኮዲንግ መላምት አይደለም ። ስለዚህ እየዚያ ሊስት ያደረካቸው ትግርኛ ቃላት እስከነ ትርጉማቸው ከነገርከን ከምናውቃቸው የኧዣ እርባታ ቃላት ጋራ በማነጻጸር መወያየት እንችላለን።

Meleket
Member
Posts: 4052
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!

Post by Meleket » 18 Aug 2023, 09:25

ወዳጃችን Horus መፈላሰፍህ መልካም ሆኖ ሳለ፡ ስለምታውቀው ቋንቋ ስለ ጉራጌኛ እንዳሻህ መፈላሰፍ ስትችል፡ "ትግርኛ ውስጥ ዬሌሉ ቃላት" በማለት በርካታ ታሪካዊ ቃላትን ኢዛና፡ ኣግኣዝያን፡ ኣዅሱም፡ ነጋሲ ግድር፡ ገጀረት፡ ዘግዱር፡ እንዲሁም ጋዝ እና ኣበጋዝ (ኣቦ ጋዝ) ዘርዝረህ ነበር። እኛ ደግሞ በርካቶቹ ትግርኛ ውስጥ እንዳሉ ገልጸንልሃል።

የኋላ ኋላ ትግርኛ ቋንቋንም እንደማታውቀው ራስህ ገልጸህልን እያለ፡ በምን ሂሳብና ፍልስፍና ነው "ትግርኛ ውስጥ ዬሌሉ ቃላት" ለማለት የደፈርከው? የጉራግኛን ርቀት ለመግለጽ እኮ ዓይንህን በጨው ታጥበህ ትግርኛን ማንቋሸሽና ማኮሰስ ኣይጠበቅብህም።

እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ያቀረብናቸው በኤርትራና በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ ስፍራዎች ስማቸው ቁልጭ አድርጎ የሚገልጸው "ትግርኛ ውስጥ የሉም ያልካቸው"ቃላቶች ትግርኛ ውስጥ እንዳሉ ነው። ትርጉማቸውን ደግሞ የቀጠናችን ተመራማሪዎች ከጥላቻ ቦተሊካ ጸድተው ትክክለኛ ምርምር በሚያደርጉበት ወቅት ግልጽ አድርገው ይነግሩናል ብለን እናስባለን፡ እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Horus wrote:
25 Jul 2023, 22:53
በትግርኛ ውስጥ የሌሉ ግን በጉራጌኛ ውስጥ ያሉ 4 ቃላት!
https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=325878&
https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=325878&
Horus wrote:
16 Aug 2023, 14:25
ሰላም፣
ኦዚያን ከኢዛና ጋር ተመሳሳይ አጠቃቀም ይመስለኛ፣ በእብራይስጥ ። ከላይ እንደ ኤቪደንስ ሊስት ካደረኳቸው ውስጥ ቁ 1 ላይ ያለው ሆሳዕና ሆሻና የሚለው ነው ። ኢራኖች ሻህ እና ሁሻን እንደ ሚሉት ነው ። የሳንስክሪቱም ከዚያ ይቀርባል ። ቋንቋዎች ግንዳቸው አንድ ሆኖ በዲያሌክት የሚለያዩት በዚህ መንገድ ነው ፤ ከቃሉ ፊትና ጭራ ላይ አዲስ ድምጽ በመጨመር፣ አንዳንዴ በዘልማድ አዲስ ድምጽ መሃል ላይ በመሸንቆር ። እብራይስጥ በጣም የተጠና ቋንቋ ስለሆነ የሚያውቁ ሰዎን ኦዚያን ዛሬ ላይ ያለውን ትርጉም ጀባ ቢሉን እናመሰግናቸዋለን ።

መለከት፣
እኔ ኢሳያስ ማለት መስፍን መኮንን ማለት አላልኩም። ያልኩት ዛሬ ላይ መስፍን፣ መኮንን፣ ንጉሴ፣ ወዘተ እንደ ተራ ስም እንደ ምንጠቀመው አሳያሳም በዚያ መልክ ነው ጥቅሙ ለማለት እንደ ምሳሌ ነው የጠቅስኳቸው ። አቶ አፈወርቂ ኢሳያስ የሚለውን ስም ከመጻፍ ቅዱስ አኝግተውት ይሆናል። ኢዛና (ሂሻና) ወደ ኢሳያስ የሚለውጠው ግሪክ ነው ። መጻፍ ቅዱስ ከሴም ቋንቋዎች ወደ ግሪክ ለተተረጎመ። ኧዣ ፣ ሻህ ፣ወይም ኢዛና የሚለው ቃል የተወለደው ጥንታዊ ግብጽ ነው ብዬ ነበር። እዚህ ፎረም ላይ ከግብጽ ወደ ሴም እንዴት ኢቮልቭ አደረገ የሚለው ቴክኒካል ገለጻ እዚህ አልሰጥም። ስለማያስፈልግ።

በቀሩት ቃላት ላይ እኔ የትግርኛ ተናጋሪ ስላልሆንኩኝ በማላውቀው ቋንቋ ላይ ኢቲሞሎጂካልም ሆነ ፊሎሎጂካል ግምት አልሰጥም ። ማለት አንተ እንደ ምትለው መላ ምት አላደርግም ። የኢዛና ዲኮዲንግ መላምት አይደለም ። ስለዚህ እየዚያ ሊስት ያደረካቸው ትግርኛ ቃላት እስከነ ትርጉማቸው ከነገርከን ከምናውቃቸው የኧዣ እርባታ ቃላት ጋራ በማነጻጸር መወያየት እንችላለን።

Horus
Senior Member+
Posts: 34739
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!

Post by Horus » 18 Aug 2023, 13:00

መለከት፣
እኔ ዚዚዚ ጭቅጭቅ አልወድም። ኢዛና ምን ማለት እንደ ሆነ ዛሬ አውቀሃል ።ያ ነው የኔ አላማ ። አጋዚ ነጻ አውጪ ማለት ነው ብለህ ኖረሃል። አይደለም ። አጋዚ ጦረኛ እንጂ ነጻ አውጪ ማለት አይደለም ። ዛሬ ጋዝ ማለት ጦር ማለት ነው የሚል ጉራጌ ብቻ ነው። ግድር ዛሬ ትርጉሙን ነግሬሃሉ ግድር ዛረ ተራጉራጌኛ ቃል ነው ትግርኛ አይደልም ። አበቃሁ !! ይህን ምልልስ እዚህ አናብቃው! ሰላም

Meleket
Member
Posts: 4052
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!

Post by Meleket » 23 Aug 2023, 09:19

ወዳጃችን Horus
አግዐዘ የሚለው የግዕዝ ቃል አንዱ ትርጉሙ ነጻ አወጣ፡ ነጻ አደረገ፡ ነጻነትን አጐናጸፈ፡ ነጻነትን አመጣ፡ ሐርነትን ሰጠ፡ ነጻ ለቀቀ ወዘተ ተብሎ መተርጐሙን አንብበናል። ታዋቂው ጀርመናዊ የግዕዝ ሊቀሊቃዉንት ዲልማንም እንዲህ ብሎ አብነቶችን አስቀምጧል፦

ያግዕዛ ውስተ ገዳም። መኑ አግዐዞ ለሐለስትዮ። ትፌንዎ ኣግዒዘከ። አግዐዘታ ለእንታክቲ ወለታ። ያግዕዝ። ከመ ያግዕዝዎሙ እምቅኔሆሙ። ኢታህጕሎ ዕሴቶ ከመ ታግዕዞ። ያግዕዝ ቅኑያነ። በእንተ አግእዞ ገብር።
. . .
አግዐዘነ እምኅጢኣት ወሞት። አግዐዘነ እምተቀንዮ ለኅጢኣት፡ እምአርዑተ ኅጢኣት።

ለዚህም ነው ከዚህ በፊት እንዲህ በማለት ለመግለጽ የሞከርነው
Meleket wrote:
29 Jul 2023, 02:17
ግሩም ትንታኔና ምርምር ነው ወንድም Horus ቀጥልበት፦
. . .
ኣግኣዚ የሚለውን ቃል እግዚእ፡ ጎይታ፡ ገዛኢ ከሚለው ጋር ያዛምዳሉ ኣንዳንድ ተመራማሪዎቻችን፡ ትክክለኛው ጌታችን ደግሞ ከኃጢኣትና ከባርነት ቀንበር ነጻ እውጪ መሆኑን መቼም ሁላችንም ኣንስተውም፡ እንስማማበታለን።
Horus wrote:
18 Aug 2023, 13:00
መለከት፣
እኔ ዚዚዚ ጭቅጭቅ አልወድም። ኢዛና ምን ማለት እንደ ሆነ ዛሬ አውቀሃል ።ያ ነው የኔ አላማ ። አጋዚ ነጻ አውጪ ማለት ነው ብለህ ኖረሃል። አይደለም ። አጋዚ ጦረኛ እንጂ ነጻ አውጪ ማለት አይደለም ። ዛሬ ጋዝ ማለት ጦር ማለት ነው የሚል ጉራጌ ብቻ ነው። ግድር ዛሬ ትርጉሙን ነግሬሃሉ ግድር ዛረ ተራጉራጌኛ ቃል ነው ትግርኛ አይደልም ። አበቃሁ !! ይህን ምልልስ እዚህ አናብቃው! ሰላም
እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች አግዐዚ ማለት ነጻ አውጪ ማለት ነው ስንል በምክንያት ነው!

ኬር!
:mrgreen:

Post Reply