ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
ምንም ቴክኒካል ሃተታ ሳላበዛ በጥሬ ትርጉሙ ኢዛና ማለት ንጉስ፣ መስፍን ማለት ነው ። የቃሉ ብልት ሁላችሁም የምታውቁት ‘ጃ’ (ዣ) የሚለው ነው ። ኃያል፣ ታላቅ ማለት ሲሆን ዣን፣ ዣን ሆይ፣ ዣን አሞራ የምንለው ነው።
ቃሉ የተወለደው በጥንታዊት ግብጽ ሲሆን እነሱ ካህ ወይም ቻህ ያሉት ይመስለኛ ። ከዚህ ብዙ ሳይርቅ ይዘውት ያሉት ኢራናዊያን ሲሆኑ እነሱ ‘ሻ’ (ሻህ) ይሉታል። ሻ (ሻህ) ንጉስ ማለት ሲሆን ሻሃንሻ ንጉሰ ነገስት ማለት ነው ።
በኢትዮጵያ ያለው አጠቃቀም ከፊቱ ቅጽል ተቀጥሎበት ንጉስ (ንኩሽ)፣ ነካሺ (ነጋስሂ) ማለትም ካህ በሚለው የግብጽ ስሩ ያለ ነው።
ከዚህ በታች እንደ ኤቪደንስ ልዩ ቃላትና አግባቦን አቀባለሁ ።
(1) በአቢይ ጾም ግማሽ የምናከብረው ሆሳዕና (ሆሻና፣ ሆሳና) የንጉሱ መግባት በዓል ነው ። ሆሳን ወይም ሆሻና ንጉስ ማለት ነው ።
(2) በህንዶች ቅዱስ ቋንቋ (የህንዶች ግእዝ) ሳንስክሪት ሆሻን ፣ ሾሻን መስፍን ማለት ነው።
(3) ካልተሳስትኩ በእብራስጥ ሹሻን ልዕልት ፣ ንግስት እንደ ማለት ነው፣ የሴት ስም ነው
(4) ከአረሜይክ ቋንቋ ጀምሮ በሁሉም የሴም ቋንቋዎች ኧዣ፣ እዣ፣ አዚዝ፣ አዣዥ፣ ገዢ፣ ነጋሲ፣ ንግስት፣ ንጉስ፣ ማለት ባለስልጣን ፣ ገዥ። ሩለር ማለት ነው ።
(5) በጉራጌ አንዱ የጉራጌ አገርና ጎሳ እዣ ይባላል
(6) እንዲሁ በጉራጌኛ ሰነ (ሸነ) ኃይል ማለት ሲሆን ስልጣን፣ ስልጤ ለሚሉት ቃላት ስር ነው
(7) እንዲሁ በጉራጌ ሰነቻ የሚዳኙ ሽማግሎች ናቸው
(8) በአረብኛ ሃሳን፣ ሃሰን፣ ሁሴን ማለት ኃያል ፣ ታላቅ ማለት ነው ። መስፍን እንደ ማለት ነው
(9) ሰነ ኃይል ማለት ነው ብዬ ነበር ፤ ጸና፣ ጽኑ፣ ጽናት ኃይል፣ ጥንካሬ ማለት ነው
(10) በጎደር ዘመን የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ዘ ስላሴ የጉራጌ ሕዝብ አስተዳደር አጉራ ጠነ ይባላል ብለዋል ። አጉራ ጠነ ማለት ራስ ገዝ አገር ማለት ነው ። ጠነ (ሰነ) ከላይ እንዳልኩት ገዝ (ገዠ፣ ኧዠ) ማለት ነው።
በአጭሩ ኢዛና ማለት ኧዣኛ፣ ኧዠኛ ... ባለ ኃይል፣ ገዢ፣ ንጉስ ማለት ነው ። ንጉስ ኢዛና ንጉሰ ነገስት የሚል ማረግ መያዙን አላቅም ። አድርጎ ቢሆን ኢዛነዛ ወይም ኢዛነዣ ይባል ነበር ። ንጉሰ ነግስት በሚለው አግባቡ ማለት ነው ።
እነዚህ ለግዜው እማስታውሳቸውን ብቻ ነው ። ሌሎቻችሁ ሻ፣ እሻ፣ እዛ፣ ኢዛ፣ ትዛዝ ቀመስ ቃላት አክሉበት ።

Last edited by Horus on 12 Aug 2023, 18:26, edited 3 times in total.
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
"The best thing a human being can do is to help another human being know more" You are doing it here without fail. Thanks.
-
- Member
- Posts: 950
- Joined: 11 Aug 2013, 07:11
- Contact:
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
ሰላም ወንድሜ Horus: ለዚህ እና ለመሰል አስተማሪ ጽሑፎችህ ብዙ ብዙ ምስጋና ይገባሃል። እናም ከላይ በገለፅከው መሰረት ... ዣን-ጥላ ወይንም ጃን-ጥላ የንጉስ ጥላ ለማለት ነው የሚል ትርጉም ይሰጣልን? ሻ-ሽ የሚለውስ ቃል ሻ ከሚለው የኢራን ቃል ተራብቶ (ውርስ) ሆኖ ... ምናልባት ንጉስ ኣፄ ምንሊክን በመሳል ሂደት የምናየው በጭንቅላት ላይ የሚታሰረው ሻሽ መሰል ጨርቅ ከንግስና (ዙፋን) ጋር የተያያዘ ትርጉም ይኖረው ይሆን የሚል የእራሴን ጥያቄ ይዣለሁ።
መልካም ሰንበት ይሁንልህ, Brother Horus
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
Horus,
ስለ ትግሬ ጥያቄዎችህን በሙሉ professor halafi ብትንትን አድርጎ ያስረዳሀል። አይዞህ። ስንት አመት ሙሉ አስረዳን ሁላችንንም ER ላይ። አንድ ነገር አለ ፣ "ናይ እውቀቲና ናይ ፈሰስዩ" ይባላል በትግራያዋይ አባባል። ትርጓሜውም እውቀት በትግራያዋይ ወደላይ ሄዳ ወደ ታች ፈሰሰች ማለት ነው።
ከፈለክ አክሱም ሀውልት የተገነባው በመለስ ቅድመ አያት ነው ይልሀል፣ ታጋይ ዜናዊ ማለት ነው። አክስም ማለት ሲተነነትን እንዲህ ነው፣ ቀላል እኮ ነው ምንም ማካበድ አያስፈልግም!
አ፣ ማለት አጋዚ ሲሆን፣
ክ፣ ማለት ክፍለጦር ሲሆን፣
ሱ፣ ማለት ደግሞ ሱውሳይድ (እራስን አይኑ እያየ የጥይት እሩምታ ውስጥ መክተት) ሲሆን፣
ም፣ ማለት ምፅራአ፣ ያው ወደ ምፅርኧ አስገብተህ ወርቁን ስትመዘው፣ qinter ማለት ነው በአድዋኛ።
Professor halafi በዚህ በአክሱም ጉዳይ ላይ more ትንታኔ ያቀርባሉ ብለን እንጠብቃለን።

For how long have you been playing him? “without fail” and “not knowing exactly what he wants,” unlike some others, cannot be true at the same time. Can they be?
Last edited by Naga Tuma on 17 Aug 2023, 19:12, edited 1 time in total.
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
Horus - That’s your brilliance. Leave the political propaganda to others.
Horus wrote: ↑12 Aug 2023, 01:43ምንም ቴክኒካል ሃተታ ሳላበዛ በጥሬ ትርጉሙ ማለት ንጉስ፣ መስፍን ማለት ነው ። የቃሉ ብልት ሁላችሁም የምታውቁት ‘ጃ’ (ዣ) የሚለው ነው ። ኃያል፣ ታላቅ ማለት ሲሆን ዣን፣ ዣን ሆይ፣ ዣን አሞራ የምንለው ነው።
ቃሉ የተወለደው በጥንታዊት ግብጽ ሲሆን እነሱ ካህ ወይም ቻህ ያሉት ይመስለኛ ። ከዚህ ብዙ ሳይርቅ ይዘውት ያሉት ኢራናዊያን ሲሆኑ እነሱ ‘ሻ’ (ሻህ) ይሉታል። ሻ (ሻህ) ንጉስ ማለት ሲሆን ሻሃንሻ ንጉሰ ነገስት ማለት ነው ።
በኢትዮጵያ ያለው አጠቃቀም ከፊቱ ቅጽል ተቀጥሎበት ንጉስ (ንኩሽ)፣ ነካሺ (ነጋስሂ) ማለትም ካህ በሚለው የግብጽ ስሩ ያለ ነው።
ከዚህ በታች እንደ ኤቪደንስ ልዩ ቃላትና አግባቦን አቀባለሁ ።
(1) በአቢይ ጾም ግማሽ የምናከብረው ሆሳዕና (ሆሻና፣ ሆሳና) የንጉሱ መግባት በዓል ነው ። ሆሳን ወይም ሆሻና ንጉስ ማለት ነው ።
(2) በህንዶች ቅዱስ ቋንቋ (የህንዶች ግእዝ) ሳንስክሪት ሆሻን ፣ ሾሻን መስፍን ማለት ነው።
(3) ካልተሳስትኩ በእብራስጥ ሹሻን ልዕልት ፣ ንግስት እንደ ማለት ነው፣ የሴት ስም ነው
(4) ከአረሜይክ ቋንቋ ጀምሮ በሁሉም የሴም ቋንቋዎች ኧዣ፣ እዣ፣ አዚዝ፣ አዣዥ፣ ገዢ፣ ነጋሲ፣ ንግስት፣ ንጉስ፣ ማለት ባለስልጣን ፣ ገዥ። ሩለር ማለት ነው ።
(5) በጉራጌ አንዱ የጉራጌ አገርና ጎሳ እዣ ይባላል
(6) እንዲሁ በጉራጌኛ ሰነ (ሸነ) ኃይል ማለት ሲሆን ስልጣን፣ ስልጤ ለሚሉት ቃላት ስር ነው
(7) እንዲሁ በጉራጌ ሰነቻ የሚዳኙ ሽማግሎች ናቸው
(8) በአረብኛ ሃሳን፣ ሃሰን፣ ሁሴን ማለት ኃያል ፣ ታላቅ ማለት ነው ። መስፍን እንደ ማለት ነው
(9) ሰነ ኃይል ማለት ነው ብዬ ነበር ፤ ጸና፣ ጽኑ፣ ጽናት ኃይል፣ ጥንካሬ ማለት ነው
(10) በጎደር ዘመን የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ዘ ስላሴ የጉራጌ ሕዝብ አስተዳደር አጉራ ጠነ ይባላል ብለዋል ። አጉራ ጠነ ማለት ራስ ገዝ አገር ማለት ነው ። ጠነ (ሰነ) ከላይ እንዳልኩት ገዝ (ገዠ፣ ኧዠ) ማለት ነው።
በአጭሩ ኢዛና ማለት ኧዣኛ፣ ኧዠኛ ... ባለ ኃይል፣ ገዢ፣ ንጉስ ማለት ነው ። ንጉስ ኢዛና ንጉሰ ነገስት የሚል ማረግ መያዙን አላቅም ። አድርጎ ቢሆን ኢዛነዛ ወይም ኢዛነዣ ይባል ነበር ። ንጉሰ ነግስት በሚለው አግባቡ ማለት ነው ።
እነዚህ ለግዜው እማስታውሳቸውን ብቻ ነው ። ሌሎቻችሁ ሻ፣ እሻ፣ እዛ፣ ኢዛ፣ ትዛዝ ቀመስ ቃላት አክሉበት ።
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
አሰግድ፣Assegid S. wrote: ↑12 Aug 2023, 05:22ሰላም ወንድሜ Horus: ለዚህ እና ለመሰል አስተማሪ ጽሑፎችህ ብዙ ብዙ ምስጋና ይገባሃል። እናም ከላይ በገለፅከው መሰረት ... ዣን-ጥላ ወይንም ጃን-ጥላ የንጉስ ጥላ ለማለት ነው የሚል ትርጉም ይሰጣልን? ሻ-ሽ የሚለውስ ቃል ሻ ከሚለው የኢራን ቃል ተራብቶ (ውርስ) ሆኖ ... ምናልባት ንጉስ ኣፄ ምንሊክን በመሳል ሂደት የምናየው በጭንቅላት ላይ የሚታሰረው ሻሽ መሰል ጨርቅ ከንግስና (ዙፋን) ጋር የተያያዘ ትርጉም ይኖረው ይሆን የሚል የእራሴን ጥያቄ ይዣለሁ።
መልካም ሰንበት ይሁንልህ, Brother Horus
እኔም በጣም አመሰግናለሁ! ከባድ ጥያቄ ነው ያነሳሃው? ትንሽ ላስብበት ። እንደ ምታቀው ጃንጥላ በግዕዝ ድባብ ነው የሚባለው ። ደቡብ፣ ደበብ ያለ ከሚለው ይያያዛል ። ጥላ፣ ጥላል (ሻዶው) ነው ። ጥላ፣ ጥላል/ጉራጌኛ መጠለያ፣ ከለላ፣ ሼልተር፣ መከላከያ እያለ ከድባብና ከ ሻዶው የላቀ የከረረ አግባብ አለው ። ስለዚህ ጃንጥላ ከድባብ ርቆ እንዴት ጥቅም ላይ እንደ መጣ ትንሽ ልተኛበት የተሳሳተ ነገር እንዳላሰራጭ ማለትም ጃንትላ ከኃይል ጋር መያያዙ ገርሞኛል ። ምናልባት አንተ እንዳልከው ድሮ ጃንጥላ ለነገስታት የሚያዘው ሊሆን ይችላል ። ለታቦት የሚያዘው የታቦት ጥላ ድባብ ሲሆን ጥላ ያዡ ጸዋሬ ድባብ ይባላል ። ጥላ ያዥ ወይም ጥላ ተሸካሚ ማለት ነው ።
Last edited by Horus on 12 Aug 2023, 21:49, edited 1 time in total.
-
- Senior Member+
- Posts: 34272
- Joined: 06 Jan 2007, 15:44
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
Horus
Why is there a Greek version of Ezana?
"Ézana, (Greek: Aezanas), Emperor (fl. mid-4th century A.D.)"

በእኔ እምነት የኢዛና ታሪክ የጻፉት ያሳሳቱት ይመሰለኛል ። 'ኢ' በግዕዝ አፍራሽ አሉታዊ ፕሪፊክ ወይም ቅጽል ነው ። ለምሳሌ መደበኛ ኢመደበኛ ወዘተ። ስለዚህ ድሮ ኢዝና (ኃይል አልባ ማለት ስለሆነ) አልነበረም፣ ኧዛና ወይም ኧዠኛ ይባል የነበር ይመሰላል ። ኧዠኛ ማለት ባለ ኃይል፣ ኃያል ማለት ነው ። እኛ በጉራጌ ኧዣ ነው የምንለው እንጂ ኢዣ አንለውም ። አማርኛና አረብኛ አዚዝ፣ አዣዥ ይላሉ እንጂ ኢዚዝ፣ ኢዛዥ አይሉም ። የሆነ ፈረንጅ ነው ታሪክ ሲዘግብ ያበላሸው ። የግሪኩን ስላስታወቅከን እናመሰግናለን ። አትርሳ ለተወሰነ ግዜ ግሪክ በአክሱም የቤተ መንግስት ቋንቋ እንደ ነበር ታውቃለህ ። ስለዚህ ኤዛና ትክክለኛ አባባል ነው ። ኢዛና ግን ስህተት ነው ያውም ግዕዝ በተነገረበት ቤተ መንግስት ። ኣኤዛና ወይም አዬዛና የሚለው የግሪኮች ፕሪፊክስ ነው! አይገባኝ ልክ ኣኤቶፒያ፣ ኣኤዞፕ እንደ ሚሉት ያ የግሪክ አክሰንት ነው ።Revelations wrote: ↑12 Aug 2023, 20:33Horus
Why is there a Greek version of Ezana?
"Ézana, (Greek: Aezanas), Emperor (fl. mid-4th century A.D.)"
Last edited by Horus on 12 Aug 2023, 21:59, edited 1 time in total.
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
ሰላም፣
በፖለቲካል ማህበረሰብ ውስጥ እየኖርክ ፖሊቲካል እንሰሳ አትሁን ማለት የዜግነት ሃላፊነቴን መርሳት ማለት ነው ። የፖለቲካ አመለካከትና አቋሜ ካልተመቸህ እዚያ እንደ ሁለት በሃሳብ የሚለያዩ ዜጎች መከራከር እንችላለን ። ለምሳሌ እስቲ ከማራምዳቸው አቋሞች የማይስማማህን ንገረኝ ፤ ራሴን የመግለጻ ግዴታ ሃላፊነት ስላለብኝ! ኬር!

ወዳጄ
እኔ የፖለቲካ አቋምህ አይስማማኝም አላልኩኝም። በወንድማዊ ምክር ፣ ተራ ፕሮፓጋንዳ በአንተ በትልቁ ሰው ላይ አያምርብህም ነው ያልኩት። ይኸንንም ያልኩት በራስህ ፅሁፍ ፣ ‘ስነልቦና የጦርነት አካል’ እንደሆነና ፣ ጠላትን ለማሸነፍ መቅጠፍ (fabrication) ተገቢ እንደሆነና አንተም ይህንኑ እንደምታደርግ ስለነገርከኝ ነው። Don’t get me wrong, ፕሮፓጋንዳ የጦርነት አካል እንደሆነ አምናለሁ። ትክክልም ነው!
በእኔ አስተሳሰብ ግን ፣ በተጠና ትንታኔ የሚያምን ሰው ፣ ፕሮፓጋንዳውን ለባለ ሙያዎቹ ቢተወው የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም ሁለቱ በፍፁም ሊታረቁ የማይችሉ የድምዳሜ ፍለጋ አሰራሮች ናቸው። ኢምፒሪካል አስተሳሰብ (empirical thinking) አየር ላይ በተበተነ ፅንሰ ሃሳብ ሳይሆን ፣ በዕውነት በታዩና በተደረጉ ምክንያቶችና መረጃዎች ላይ የተመሰረተ ትንታኔ ነው። በተቃራኒው ፕሮፓጋንዳ የሚጀምረው መልሱን በስሜታዊነት አስቀድሞ በማስቀመጥና ከዚያም በኋላ ቀድሞ የቀረበውን ድምዳሜ ለመደገፍ የሚያስችሉ የውሸት ቁጥሮችን፣ ቦታዎችን፣ ምክንያቶችንና ወዘተ በመደርደር ነው። በዚህም አሰራር ሳይንሳዊ አስተሳሰብ በምርምርና በክርክር እየታነፀና እየተከረከመ ወደ ቋሚ ዕውነታነት ሲያድግና ሲሸጋገር ፣ ፕሮፓጋንዳ ውይይትንና ክርክርን በፍፁም ስለማያስተናግድ ሳያድግ ቀጭጮ ይሞታል።
በእኔ አመለካከት ሁለቱን አሰራሮች የሚያሳክር ሰው ምንም ትልቅ ነገር ቢሰራ ተአማኝነት አይኖረውም። በተለይ ከእነ ታዲዮስ ታንቱ ፣ ከእነ ኃይሌ ላሬቦ፣ ከእነ ፀጋዬ ገብረመድህን ፣ ከእነ መንግስቱ ለማ ፣ ከእነ ብርሃኑ ዘርይሁን እና ከእነ ደበበ ሰይፉ ደረጃ የሚመደብ ተመራማሪ ፣ ብዕረኛና ፈላስፋ ከነ ዲዲቲ ፣ ቶማስና ሃላፊ ፋንድያና ካድሬያዊ ፕሮፓጋንዳ ጋር ለመወዳደር ሲጋጋጥ አዝናለሁ።
“የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ” ማርቆስ 12:17

Last edited by Selam/ on 13 Aug 2023, 12:18, edited 4 times in total.
-
- Member+
- Posts: 9729
- Joined: 30 Apr 2007, 17:38
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
OPFIST Shabian/Tplf was so pissed about what Horus posted on Ezana and the Amharic. He is pissed demanding Oromiffa should be the National language kkkkkk
-
- Member+
- Posts: 9729
- Joined: 30 Apr 2007, 17:38
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
Advice: Selam is right, today the so called Ethiopian intellectuals, no pun intended to Horus, but they have lost the compass, they have gone so low, getting in issues that is useless instead of creating some kind of project that will empower ethiopians within and outside. do you know why? Most are remenants of Ehapa who are still programmed and brainwashed. they have killed with Shabia, Tplf and OLf mercinaries the real Ethiopian intellectuals since the 60s that could have taken Ethiopia beyond.
-
- Member+
- Posts: 9729
- Joined: 30 Apr 2007, 17:38
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
Advice: Selam is right, today the so called Ethiopian intellectuals, no pun intended to Horus, but they have lost the compass, they have gone so low, getting in issues that is useless instead of creating some kind of project that will empower ethiopians within and outside. do you know why? Most are remenants of Ehapa who are still programmed and brainwashed. they have killed with Shabia, Tplf and OLf mercinaries the real Ethiopian intellectuals since the 60s that could have taken Ethiopia beyond. Ethiopia till today is only surviving because of of Orthodox. They are now trying to kill Orthodox the last battle.
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
Horus wrote: ↑12 Aug 2023, 01:43ምንም ቴክኒካል ሃተታ ሳላበዛ በጥሬ ትርጉሙ ኢዛና ማለት ንጉስ፣ መስፍን ማለት ነው ። የቃሉ ብልት ሁላችሁም የምታውቁት ‘ጃ’ (ዣ) የሚለው ነው ። ኃያል፣ ታላቅ ማለት ሲሆን ዣን፣ ዣን ሆይ፣ ዣን አሞራ የምንለው ነው።
ቃሉ የተወለደው በጥንታዊት ግብጽ ሲሆን እነሱ ካህ ወይም ቻህ ያሉት ይመስለኛ ። ከዚህ ብዙ ሳይርቅ ይዘውት ያሉት ኢራናዊያን ሲሆኑ እነሱ ‘ሻ’ (ሻህ) ይሉታል። ሻ (ሻህ) ንጉስ ማለት ሲሆን ሻሃንሻ ንጉሰ ነገስት ማለት ነው ።
በኢትዮጵያ ያለው አጠቃቀም ከፊቱ ቅጽል ተቀጥሎበት ንጉስ (ንኩሽ)፣ ነካሺ (ነጋስሂ) ማለትም ካህ በሚለው የግብጽ ስሩ ያለ ነው።
ከዚህ በታች እንደ ኤቪደንስ ልዩ ቃላትና አግባቦን አቀባለሁ ።
(1) በአቢይ ጾም ግማሽ የምናከብረው ሆሳዕና (ሆሻና፣ ሆሳና) የንጉሱ መግባት በዓል ነው ። ሆሳን ወይም ሆሻና ንጉስ ማለት ነው ።
(2) በህንዶች ቅዱስ ቋንቋ (የህንዶች ግእዝ) ሳንስክሪት ሆሻን ፣ ሾሻን መስፍን ማለት ነው።
(3) ካልተሳስትኩ በእብራስጥ ሹሻን ልዕልት ፣ ንግስት እንደ ማለት ነው፣ የሴት ስም ነው
(4) ከአረሜይክ ቋንቋ ጀምሮ በሁሉም የሴም ቋንቋዎች ኧዣ፣ እዣ፣ አዚዝ፣ አዣዥ፣ ገዢ፣ ነጋሲ፣ ንግስት፣ ንጉስ፣ ማለት ባለስልጣን ፣ ገዥ። ሩለር ማለት ነው ።
(5) በጉራጌ አንዱ የጉራጌ አገርና ጎሳ እዣ ይባላል
(6) እንዲሁ በጉራጌኛ ሰነ (ሸነ) ኃይል ማለት ሲሆን ስልጣን፣ ስልጤ ለሚሉት ቃላት ስር ነው
(7) እንዲሁ በጉራጌ ሰነቻ የሚዳኙ ሽማግሎች ናቸው
(8) በአረብኛ ሃሳን፣ ሃሰን፣ ሁሴን ማለት ኃያል ፣ ታላቅ ማለት ነው ። መስፍን እንደ ማለት ነው
(9) ሰነ ኃይል ማለት ነው ብዬ ነበር ፤ ጸና፣ ጽኑ፣ ጽናት ኃይል፣ ጥንካሬ ማለት ነው
(10) በጎደር ዘመን የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ዘ ስላሴ የጉራጌ ሕዝብ አስተዳደር አጉራ ጠነ ይባላል ብለዋል ። አጉራ ጠነ ማለት ራስ ገዝ አገር ማለት ነው ። ጠነ (ሰነ) ከላይ እንዳልኩት ገዝ (ገዠ፣ ኧዠ) ማለት ነው።
በአጭሩ ኢዛና ማለት ኧዣኛ፣ ኧዠኛ ... ባለ ኃይል፣ ገዢ፣ ንጉስ ማለት ነው ። ንጉስ ኢዛና ንጉሰ ነገስት የሚል ማረግ መያዙን አላቅም ። አድርጎ ቢሆን ኢዛነዛ ወይም ኢዛነዣ ይባል ነበር ። ንጉሰ ነግስት በሚለው አግባቡ ማለት ነው ።
እነዚህ ለግዜው እማስታውሳቸውን ብቻ ነው ። ሌሎቻችሁ ሻ፣ እሻ፣ እዛ፣ ኢዛ፣ ትዛዝ ቀመስ ቃላት አክሉበት ።
ግሩም ፍልስፍና ነው ወንድም Horus ምርምሩን ቀጥልበት፡ ግፋበት!
ኤርትራችን ውስጥ እንግዲህ ከኤዛና ሆነ ኢዛና ጋር የሚመሳሰሉ አንዳንድ ቃላትን እንጨምርልህ። ዓዜን፡ ኳዜን፡ ቢዘን፣ ላህዜን፡ ምድሪ ዜን፡ የሚባሉ የቀዬ ስሞች ኣሉ። በተጨማሪም መስፍንቶ የተባለች እጅግ ታሪካዊ ቀዬም ኣለችን . . . መረብን ስትሻገር ደግሞ ሓውዜን የሚለው ቃል ይጠብቅሃል ማለት ነው።
ሽመዛና (ሽመጃና) የሚባል ታሪካዊ ስፍራም ኣለን።
እስቲ በነዚህ ቃላትም ተፈላሰፍባቸው የሴም ይሁኑ የኩሽ ቃላቶቹ ኤርትራ ውስጥ ቁልጭ ብለው እስከዛሬ ድረስ ኣሉ። የምርምር ውጤትህን እዚህ ለብዙሃን ማጋርትህንም እጅግ አድንቀንልሃል፡ በርታ ብለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
መለከት፣
አው ሃውዜን የሚለው ቃል ስር ዘብ የሚለው ነው ፤ ግ ን መነሻው ኧዣ(እዝ) የሚለው ሳይሆን ሌላ ነው። የእጅ መዳፍ ወይም መያዝ የሚል ስረቃል ነው ያለው ። ሸኔ በኦሮሞፋ ምን ማለት እንደ ሆነ ስለማላውቅ ስረቃሉ ምን እንደ ሆነ መናገር ዝም ብሎ ግምት ይሆንብኛል ።
ይልቅስ ይችን ልመርቅልህ (ልጨምርልህ)። ኢሳያስ ማለት ኢዛና መሆኑን ገምተህ ነበር ወይ? ኢዛ(ና/ያ)ስ (ኢዛንያስ) ማለት ነው ። ያስ የሚለው የግሪክ ኢንፍሉወንስ ነው ። ልክ ኤርሚያስ፣ እዝክያስ፣ ሚልኪያስ እንደ ሚባለው ። ኢሳያስ ማለት እኛ ንጉሴ፣ መኮንን፣ መስፍን እያልን እንደ ምንጠራው ማለት ነው ።

ግሩም መላ ምት ነው። ወንድም Horus ምርቃትህ ደግሞ ታዝናናለች።Horus wrote: ↑14 Aug 2023, 13:05መለከት፣
አው ሃውዜን የሚለው ቃል ስር ዘብ የሚለው ነው ፤ ግ ን መነሻው ኧዣ(እዝ) የሚለው ሳይሆን ሌላ ነው። የእጅ መዳፍ ወይም መያዝ የሚል ስረቃል ነው ያለው ። ሸኔ በኦሮሞፋ ምን ማለት እንደ ሆነ ስለማላውቅ ስረቃሉ ምን እንደ ሆነ መናገር ዝም ብሎ ግምት ይሆንብኛል ።
ይልቅስ ይችን ልመርቅልህ (ልጨምርልህ)። ኢሳያስ ማለት ኢዛና መሆኑን ገምተህ ነበር ወይ? ኢዛ(ና/ያ)ስ (ኢዛንያስ) ማለት ነው ። ያስ የሚለው የግሪክ ኢንፍሉወንስ ነው ። ልክ ኤርሚያስ፣ እዝክያስ፣ ሚልኪያስ እንደ ሚባለው ። ኢሳያስ ማለት እኛ ንጉሴ፣ መኮንን፣ መስፍን እያልን እንደ ምንጠራው ማለት ነው ።
ኢዛና ማለት ንጉሥ መስፍን መኮንን ወዘተ ማለት ነው የሚል ‘መፍቻ ቁልፍ’ ካመጣህ በኋላ ኢሳያስ ማለትም ኢዛንያስ ማለት ነው ብለህናል። ትርጉሙም እንደ ኢዛና ነው ካልከን ዘንዳ፤ “ይ” የተቀላቀለበትና “ይ” ያማከለው ኢሳያስ ማለትም 'ኢሳይያስ' ማለት ምን ማለት ነው በነካ እጅህ እስቲ ተርጉምልን።
ኢሳያስ = ኢዛንያስ = ንጉሴ መኮንን መስፍን ብለህናል፤ ኢዛና ንጉሠነገሥት አልነበረምም ብለህናል።
ኢሳይያስ = _ _ _ _ _ መኮንነ መኳንንት ብለህ ተርጉምልንና አስቀን እንጂ። የቅዱስ መጸሓፉ ኢሳይያስ ትርጉሙ እንዳንተው የኢዛና ትርጉም ነውን?
ኢዛናና ሳይዛናም ሲባል እንሰማለን ሳይዛና ማለትስ ምንድነው ትርጉሙ?
ኢዛና የሚለውን ቃል ከ1600 ዓመታት በኋላ ዲኮድ እንዳደረግከው ገልጸህልናል፡ ቃሉ ግን ከዚያ በፊት በጭራሽ ኣልነበረም ማለት ነውን? ታዲያ ክየት ፈለቀ? ከ1600 ዓመታት በፊትስ ንጉስ መስፍን መኮንን ወዘተ የሚሉት ቃላቶች በ"ኢዛና" ኣይጠቀሱም ነበር ማለትህ ነውን? እስቲ አብራራልን።
ጥንታዊው ቃል "ኢዛና" ነው ወይስ "ኢሳይያስ"፡ "ኢዛና" የሚለውን ቃል ከ1600 ዓመታት በኋላ ዲኮድ እንዳደረግከው ነው የገለጽክልን፡ "ነብዩ ኢሳይያስ" ደግሞ ከ2000 ዓመታት በፊት ስለተወለደው ስለክርስቶስና ስለ እናቱ ስለድንግል ማርያም አስቀድሞ በኦሪት የነገረን ተጽፎ እኛጋም ደርሷል። ጥንታዊው ቃል ግን ዬትኛው ነው!
እላይ የሃውዜንን መላ ምትህን ሰምተነዋል፤ የነ ዓዜን ዃዜን፡ ምድሪዜን፡ ቢዘን፡ ባዜን፡ ሽመዛና(ሽመጃና)፡ ዛና ወዘተ ትርጉምስ ከኢዛና ጋር ግንኙነት አለውን? እስቲ መላ ምቶችህን ኣካፍለን። ዲኮድ ካደረግህ ኣይቀር በደንብ አድርገህ ዲኮድ አድርግልንና እዬተዝናናን እንማማርባቸው ብለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Re: ኢዛና ምን ማለት ነው? ይህው ከ1600 አመት በኋላ ሆረስ ዲኮድ አድርጎታል!
ዒዛና የሚለው ቃልስ ዖዚያን ከሚባለው ቅን የይሁዳ ንጉሥ ስም ጋራ ይያያዝ ይሆን እንዴ? ዖዚያን የነገሰው ከዒዛና 1000 ዓመት ገደማ በፊት ሲሆን በጣም የተሳካለትና ስመ ጥሩ ንጉስ ነበር። ሆኖም የካህናትን ሥራ ለመሥራት መቅደስን በመድፈሩ ምክንያት በነገሰ በ52 ዓመቱ በስጋ ደዌ ተመቶ ሞተ።
Meleket wrote: ↑16 Aug 2023, 03:38ግሩም መላ ምት ነው። ወንድም Horus ምርቃትህ ደግሞ ታዝናናለች።Horus wrote: ↑14 Aug 2023, 13:05መለከት፣
አው ሃውዜን የሚለው ቃል ስር ዘብ የሚለው ነው ፤ ግ ን መነሻው ኧዣ(እዝ) የሚለው ሳይሆን ሌላ ነው። የእጅ መዳፍ ወይም መያዝ የሚል ስረቃል ነው ያለው ። ሸኔ በኦሮሞፋ ምን ማለት እንደ ሆነ ስለማላውቅ ስረቃሉ ምን እንደ ሆነ መናገር ዝም ብሎ ግምት ይሆንብኛል ።
ይልቅስ ይችን ልመርቅልህ (ልጨምርልህ)። ኢሳያስ ማለት ኢዛና መሆኑን ገምተህ ነበር ወይ? ኢዛ(ና/ያ)ስ (ኢዛንያስ) ማለት ነው ። ያስ የሚለው የግሪክ ኢንፍሉወንስ ነው ። ልክ ኤርሚያስ፣ እዝክያስ፣ ሚልኪያስ እንደ ሚባለው ። ኢሳያስ ማለት እኛ ንጉሴ፣ መኮንን፣ መስፍን እያልን እንደ ምንጠራው ማለት ነው ።
ኢዛና ማለት ንጉሥ መስፍን መኮንን ወዘተ ማለት ነው የሚል ‘መፍቻ ቁልፍ’ ካመጣህ በኋላ ኢሳያስ ማለትም ኢዛንያስ ማለት ነው ብለህናል። ትርጉሙም እንደ ኢዛና ነው ካልከን ዘንዳ፤ “ይ” የተቀላቀለበትና “ይ” ያማከለው ኢሳያስ ማለትም 'ኢሳይያስ' ማለት ምን ማለት ነው በነካ እጅህ እስቲ ተርጉምልን።
ኢሳያስ = ኢዛንያስ = ንጉሴ መኮንን መስፍን ብለህናል፤ ኢዛና ንጉሠነገሥት አልነበረምም ብለህናል።
ኢሳይያስ = _ _ _ _ _ መኮንነ መኳንንት ብለህ ተርጉምልንና አስቀን እንጂ። የቅዱስ መጸሓፉ ኢሳይያስ ትርጉሙ እንዳንተው የኢዛና ትርጉም ነውን?
ኢዛናና ሳይዛናም ሲባል እንሰማለን ሳይዛና ማለትስ ምንድነው ትርጉሙ?
ኢዛና የሚለውን ቃል ከ1600 ዓመታት በኋላ ዲኮድ እንዳደረግከው ገልጸህልናል፡ ቃሉ ግን ከዚያ በፊት በጭራሽ ኣልነበረም ማለት ነውን? ታዲያ ክየት ፈለቀ? ከ1600 ዓመታት በፊትስ ንጉስ መስፍን መኮንን ወዘተ የሚሉት ቃላቶች በ"ኢዛና" ኣይጠቀሱም ነበር ማለትህ ነውን? እስቲ አብራራልን።
ጥንታዊው ቃል "ኢዛና" ነው ወይስ "ኢሳይያስ"፡ "ኢዛና" የሚለውን ቃል ከ1600 ዓመታት በኋላ ዲኮድ እንዳደረግከው ነው የገለጽክልን፡ "ነብዩ ኢሳይያስ" ደግሞ ከ2000 ዓመታት በፊት ስለተወለደው ስለክርስቶስና ስለ እናቱ ስለድንግል ማርያም አስቀድሞ በኦሪት የነገረን ተጽፎ እኛጋም ደርሷል። ጥንታዊው ቃል ግን ዬትኛው ነው!
እላይ የሃውዜንን መላ ምትህን ሰምተነዋል፤ የነ ዓዜን ዃዜን፡ ምድሪዜን፡ ቢዘን፡ ባዜን፡ ሽመዛና(ሽመጃና)፡ ዛና ወዘተ ትርጉምስ ከኢዛና ጋር ግንኙነት አለውን? እስቲ መላ ምቶችህን ኣካፍለን። ዲኮድ ካደረግህ ኣይቀር በደንብ አድርገህ ዲኮድ አድርግልንና እዬተዝናናን እንማማርባቸው ብለናል እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።![]()