Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member
- Posts: 4549
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 03 Mar 2023, 05:02
ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ለጀግናው ደጃዝማች ባህታ ዬተቀኘንለትን እዚህ ለታሪክ መዘከር ይሆን ዘንድ ኣምጥተነዋል፡ ያበሻ ፈረንጆች እንደማይደሰቱበት ብናውቅም፡ እነሱ ኣይደሰቱበትምና ብለን ጀግኖቻችንን ከማወደስ ወደኋላ እንደማንል ስንገለጥ፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር ነው።
-
Meleket
- Member
- Posts: 4549
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 04 Mar 2023, 03:34
Meleket wrote: ↑02 Mar 2022, 08:06
ከዚህ በፊት እዚሁ መረጃ ውስጥ Open Forum ላይ ዱለነው የነበረውን የደጃዝማቹን ታሪክ፡ ተልባ ባንድ ሙቀጫ እየወቀጥን፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ትኮመኩሙ ዘንድ ጋብዘናል።
Meleket wrote: ↑08 Sep 2018, 00:57
እንደሚታወቀው ለማወራረጃነት እነዚህን ሓቆች እየተጎነጨን የደጃዝማቹን ታሪክ በስምዖን እይታ እንቀጥል፦
1) ባህታ ቆቅ ከመሆኑ የተነሳ “አሽንዃይ ንጉሥ ተምቤን ንፋስ ተምቤን አይልኸኻ” የሚል ብሂል ያዘወትር እንደነበረ፣ ትርጓሜውም “ከተንቤን የመጣ ንጉሥ ይቅርና ከተንቤን አቅጣጫ የነፈሰ ንፋስ አይንፈስብን” የሚል አባባል በማዘውተር ከመረብ ማዶ ይመጣበት የነበረን ተጽዕኖ በአባባሉ ይገልጽ እንደነበረ።
2) ባህታ ሆነ ሌሎች የምድሪ ባሕሪ አርበኞች በሓባብ ምድር መመሸግ የጥንት የጥዋቱ ስትራቴጂ እንደነበረ፣ አሁንም በዘመናችንም ኤርትራውያን ታጋዮች ይህን ሓቅ እንደደገሙ።
3) ባህታ ሆነ ሌሎች የምድሪባሕሪ አርበኞች ሲሻቸው ከጣልያን ጋር ይቀላቀሉ የነበሩት ስልታዊ በሆነ መንገድ መሳርያ ሆነ ሞራላዊ ድጋፍን ለማግኘት እንደ ነበረ። (ልኽ እንኳን ጠቅላይ አብይ ግቡ ከማለቱ በፊት እዚ ኤርትራ ውስጥ እንደነበሩት የጦቢያ ተቃዋሚዎች ማለት ነው፣ ነጭ ነጩን እናውጋ ከተባለ። አሁን የስምዖንን እይታ እንቀጥል፦
በዚህ ወቅትም እንደነ ባላምባራስ ካፍል ጎፋር፣ ደጃዝማች ሓድገምበስ ጉልወት፣ ተድላ አባ ፈርጃ የተባሉና ሌሎችም ኤርትራዉያን የምድረባሕሪ ጀግኖች ከራስ አሉላ ሸሽተው በሓባብ ምድር እንደነበሩ ይታወቅ ነበር። አንድ ቀንም በጋራ ሆነው ሲጫወቱ አንዳንዶቹ “አጼ ወይም አሉላ አሸነፈ ብለው ከሚነግሩኝ ድርቡሽ ወይም ቱርክ ወይም ግብጽ አሸነፈ ቢሉኝ እመርጣለው” ይሉ ነበር። ደጃዝማች ባህታ ግን “እኔ እንኳን እዝችው ያለሁበት ቦታ እሞታታለው እንጂ ቱርክ ወይም ግብጽ አሸነፈ ከሚሉኝ አጼ አሸነፈ ቢሉኝ ነው የምመርጥ።” አሉ።
ይህች ንግግራቸው ወደ ራስ አሉላ ስለደረሰች ራስ አሉላ ደስ ብሏቸው “የሓጎስ ልጅ ወደኔ ቢመጣ እኮ የአከለጉዛይን ምድር በሙሉ እንዲያስተዳድር በሰጠሁት” በማለት በተሰበሰቡ ሰዎች መካከል ተናገረ። አንዳንድ ሰዎችም ወደ ደጃዝማች ባህታ በማምራት ኑ እንሂድ ወደነ አሉላ እንግባ ብለው ሲለምኗቸው “ፈጽሞ አይታሰብም እነዚህ እንደሆኑ መሃላ መጣስ አመላቸው ነው፣ መሀላን ለማፍረስ ወደ ኋላ የማይሉ ትውልዶች ስለሆኑ እኔ አላምናቸውም፣ በነሱ ስር ደግሞ ፈጽሜ አልሆንም።” አሉ።
ጣልያኖች የምጽዋን ከተማ እንደተቖጣጠሩም “እራት የፈለገ እንግዳ ህጻንን ከነ ንፍጡ ይስማል” እንደሚባለው፣ ጣሊያኖች ይዘውት የመጡትን የማሪያ ተሬዛ ገንዘብ ላገኙት ሁሉ ማደል ተያያዙት። ይህን ያዩ ገራገሮችም፣ ጣሊያን እንደሆን ገንዘብ ይሰጣል እንጂ እንደሌሎች የሰውን ገንዘብ አይዘርፍም አይወርም አይቀማም፣ መንግስት ማለት ይህን ነው አሉ።ብዙዎችም ክርስትያኖችና እስላሞች ሁሉም ከየቀያቸው ይሁን ሸፍተውበት ከነበረ በረሀ እየወጡም ወደ ምጽዋ በማምራት ከጣሊያኖች ጋር ታጠቁ። በዚህ ወቅት ደግሞ መጥፎ ወረርሽኝና ህመም እንዲሁም ረሃብ ተስፋፍቶም ነበር።
ደጃዝማች ባህታም “ጣሊያን ና ወደኔ የሀገርህን ግዛት እሰጥሃለሁም እያለኝ ነዉና ምን ባደርግ ይሻላል?” በማለት ከጓደኞቻቸው ጋር ተመካከሩ። ጓደኞቻቸውም ይህን ሁሉ አመታት በበረሃ እንደ አራዊት ስንኖር ቆይተንስ አሁን ና እንሹምህ የሚል ተገኝቶስ እሽ እንበላቸው እንጂ አሏቸው። ደጃዝማች ባህታ ግን “እናንት ሰዎች እነዚህ ትግራዮችንና ፈረንጆችን አላምናቸውም። ሙሲንጀር ፓሻ እንኳን ሳይቀር አሳልፎ ለራስ አሉላ ሊሰጠኝ የነበረ፣ አሁንም ይህ ጣሊያን የሚባል አሳልፎ እንዳይሰጠንና እንዳይከዳን እጠራጠራለው። አይ የግድ መግባት አለብን ካላችሁ ግን እሽ በሉ ይሁንላችሁ” በማለት ከነተከታዮቻቸው ጋር በመስማማት ወደ ምጽዋ በመውረድ ከጣሊያኖች ጋር ተቀላቀሉ። በዚህ ተግባራቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ የምትገልጽ ራሳቸው የደረደሯት ሙሾም እስከ ዛሬ ድረስ ትደገማለች፦
ሰንጋል ወንድሜ ሆይ ብዙም አትሞኝ፣
ገብረመድኅን ልጄ ብዙም አትሞኝ፣
ብላታም ብትሆን ብዙም አትሞኝ፣
ልቤ ተሰብሮ ነው ይህንን ስቀኝ።
አስተውል አስተውል አስተውል ልብ አርገህ፣
ነጭ እባብ እንደሆን አንዴ ከነከሰህ፣
ፈውሱ አይገኝም ፈልገህ ፈላልገህ።
እግሩ ግብጽ ላይ፣
ትራሱ አሰብ ላይ፣
አምላክ ፈልጓል ወይ ይህን ጉድ እንድናይ! አሉ።
ምንም እንኳን በብዙ መጻሕፍቶች ላይ ይህን ሙሾ የደረደረው ሰንጋል ወንድማቸው ነው ቢባልም ፣ ብዙ ታላላቅ ሰዎች የሚስማሙበት ግን ይህ ሙሾና በርካታ ሙሾዎችን በመደርደር ልቦና የሞላው ጥበባዊ መልእኽትን በማስተላለፍ የሚታወቁት ራሳቸው ደጃዝማች ባህታ እንደሆኑ ነው።
አባ ቪካር የተባሉ አንድ ካህን “ የቁልቋል ፍሬ(በለስ) ና ጣልያን እያደር ይወርስሃል” እንዳሉት፣ ደጃዝማች ባህታም የጣሊያን ተግባር አስቀድሞ ቢታያቸውም እንኳን፣ በጓደኞቻቸው ግፊትና ጠላቶቻቸውን ለመጠራረግ ይህን ዕድል ለመጠቀም ሲሉ ወደ ደኾኖ በመሄድ ከጣሊያን ጋር ተስማሙ። ነሓሴ 3 1889 ጣሊያን አስመራ ገብቶ መላ ኤርትራን እንደተቆጣጠረም፣ ደጃዝማች ባህታን የአድግና ተገለባ ማለትም የአከለጉዛይ ምስለኔ በማለት ሾሞ በሰገነይቲ ቀያቸው እንዲቀመጡ አደረገ። ከጣሊያን ጋር በደኾኖ በተገናኙበት ወቅትም ደበብን እዛው ስላዩት በማዶ እየተያዩ ተለያዩ። የኋላ ኋላም ነገሩን ሲያሰላስሉት በህይወት ዘመኔ ከሰራሁት ሶስት ትልልቅ ስህተት መካከል “ደበብን እያየሁ የተውኩበት ቀን፣ ከዓሳሊሰን ጋር በብርኩታ (የእረኛ ምግብ) ምክንያት ደም የተፋሰስኩበት ቀን እንዲሁም ወንድሜ ካሕሱን የገደልኩበት ቀን ነው” በማለት በማንም ሰው የሌለ የግልጽነትና ስህተትን የማመን ጠባያቸውን እንደሚገልጽ ይነገርላቸዋል።
በዚያን ወቅት አጼ ዮሃንስ በድርቡሾች ተሸንፈው እንደሞቱ፣ ይህ አካባቢ በተለይም ትግራይ በረሃብ ተሰቃየ፣ ትልቅ እልቂትም አጋጠመ። ይህ ረሃብና ድርቅ በተለይ ትግራይ ውስጥ እንደነበረ የሚያስረዳም ባሻ ገብረእዝጊ ወደንገዘ የተባሉ በትውልድ የመረታ ሰበነ ተወላጅ መሆናቸውን የሚያምኑ የትግራይ ተወላጅ፣ እናቶቻቸው የሞቱባቸው 60 የሚሆኑ ህጻናትን በማሰባሰብ አሳደጓቸው። እስከ አሁን ድረስም እነዚህ ልጆች “ገብረዝጊ ይሙት” በማለት ይምላሉ። ይህ በጣም በሁሉ መአዘናት ችግርና እልቂት የበዛበት ዘመን ነበር። “ዘመን አካሂዳ” ወይም “የመካካጃ (የመካካድ) ዘመን” በመባልም ይታወቃል። ይህም የሚያስረዳን ህዝብ ምን ያህል ተጨንቆና እርስ በራሱ ተካክዶ እንደነበረ ነው። በዚህ የተነሳም አቶ ዕንዳይ የተባሉ በጽንዓደግለ የአዅሩር ተወላጅ እንዲህ ብለው ነበርም ይባላል፦
ምን ዓይነት ዘመን ነው ዘመነ ገጣጣ፣
ሁሉ ሚመጣብን እየያዘ ጣጣ፣
ምጽዋ ብንሄድ ጣልያን መጣ፣
ወደቆላ ብንወርድ ድርቡሽ መጣ፣
ቀያችንን ለቀን ታድያ የት እንውጣ፣
ማርያም ራስሽ አውጭን ከዚህ ከጋሬጣ፣
በፍቅር በሰላም በድል እንድንወጣ።
ይህን ሁኔታ ወደ ጥቅሙ ለመቀየር የፈለገው ጣሊያንም ለፖለቲካው ሲል በመርከብ እህል ጭኖ አስገባ። በዚህ ወቅትም ነበር የእርዳታ እህልን ለፖለቲካ አላማ መሳርያነት በሀገራችን ውስጥ መጠቀም የተጀመረው። የዚህን ምስጢር ጠንቅቆ ያላወቀ ዜጋም፦
ባቡር(መርከብ) መጣች ጢስ እያቦነነች፣
የእህል ክምር ይዛልን ነጎደች(ከነፈች)፣
ጎበዝ ሁሉ ሄደ እህል ሊከፋፈል፣
አሁንስ አክትሟል በእርዛት መቁሰል።
በማለት ተቀኘ።
የጣልያን መንግስት በረሃብ ተሸንፎ የነበረውን ህዝብ እህል ያድለው በነበረበት ወቅት ደጃዝማች ባህታ ሓጎስ ሰራዊታቸውን ወደ ዓድሮሶ በመላክ በኩባያ አስራት ይሰበስቡ ስለነበሩ “ዘመነ ኩባያ” እየተባለም ይታወቃል። በዚህ ወቅት ብዙ የተሰቃዩት ደግሞ ከትግራይ ይመጡ የነበሩት እርዳታ ጠባቂዎች ነበሩ። የምድሪ ባሕሪ ህዝብ ግን ያ ይፈጽሙ የነበሩትን ግፍና በደል በመርሳት ይተባበራቸው እንደነበረ ይነገራል። ከዚህ በኋላ ግን በደጃዝማች ባህታ አምስት የአስተዳደር ዘመናት ችግርና ረሃብ ተወግዶ ህዝባቸውን በሰላምና በጥጋብ እንዳስተዳደሩ ይነገራል። በዚህ ወቅትም አንድ የቶርዓ አዝማሪ በሳሆ ቋንቋ እንዲህ በማለት ሙሾ ደረደረ፦
ልቦክ ዳልተ ዳጊራቶ፣
ሕያው ናጋዶ ዛዛዕቶ፣
ክሳብ ገደም ክሳብ ሮብቶ። ወዘተ አለ። ትርጓሜውም
አንበሳ ወለደች የደግራዋ እናት፣
በሰላም ሚገዛ ሁሉንም በሙላት።
ከገደም እስከ ሮብቶ ሃገር ሚያስተዳድር
ነጋዴ እንዲነግድ ህዝብም ሳያማርር
በሰላም የሚያኖር ያላንዳች መቃቃር
ይህን ነው መሪ ማለት ተቆርቋሪ ላገር። እንደማለት ነው።
ይህን በደጃዝማች ባህታ ላይ የነበረውን የህዝቡን አመኔታ ጣሊያኖች እንዳዩም ደስ ስላላላቸው ተልንቲ ሳንጉነቲ የተባለ ተቆጣጣሪ ላኩባቸው። (ይቀጥላል)