Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ቴዲ አፍሮ፣ አጼ ምኒልክና አድዋ ! (መኖር ብዙ ያሳያል)!

Post by Horus » 25 Feb 2023, 15:07

አርቲስት ሎሬት ቴዲ አፍሮ 'ጥቁር ሰው' የተሰኘው ታሪካዊ ደርሰቱን ተከትሎ በመንግስት መዋከብ ብቻ ሳይሆን በነጃዋር አስተባባሪነት የነፍጠኛው ምኒልክን ስም በናዝሬት ከተማ አታነሳም ተብሎ ኮንሰርት እንዳልተከለከለ እና አገር አቀፍ 'ጉዞ ወደ ፍቅር ' ኮንሰርቱን እንዳልሰረዘ ይህው ዛሬ የአቢይ አህመድ ኦሮሙማ አገዛዝ ሕዝቡ አንቅሮ ሲተፋው ምኒልክና አድዋ ቁጥር 1 የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆነው ቀረቡ!

መኖር ደግ ነው! Tempus ajax rerum! ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል፣ ግዜ ሁሉን ነገር ይበላል !

የአድዋን በአል መርሃ ግብር ስሙ

Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቴዲ አፍሮ፣ አጼ ምኒልክና አድዋ ! (መኖር ብዙ ያሳያል)!

Post by Horus » 25 Feb 2023, 15:16

የዛሬ 12 አመት


Right
Member
Posts: 4818
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ቴዲ አፍሮ፣ አጼ ምኒልክና አድዋ ! (መኖር ብዙ ያሳያል)!

Post by Right » 25 Feb 2023, 15:23

Teddy the real leader of Ethiopia. Just like the EOTC this young man has the ability to mobilize Ethiopians for a good cause. God bless Teddy.


Selam/
Senior Member
Posts: 17887
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ቴዲ አፍሮ፣ አጼ ምኒልክና አድዋ ! (መኖር ብዙ ያሳያል)!

Post by Selam/ » 25 Feb 2023, 18:36

ኦነግ-ሸኔዎች ሙሉ ፊታቸውን የሚሸፍን ጥቁር መነፅር ቢለብሱም፣ ፀሃይ ጮራዋን መፈንጠቋን አታቆምም።

ደርግ የአስቴር አወቀ ዘፈን በህዝብ መገናኛ እንዳይተላለፍ ከልክሎ ነበር፣ ወያኔዎችም የቴዲ ‘ኢትዮዽያ’ የሚለው ቅላፄ እንደጦር ስላስፈራራቸው፣ ወንድነትን ከመማር ይልቅ፣ በፍፁም ሊታፈን የማይቻለውን የፍቅር እሳተ ገሞራ ለማጥፋት ሞክረው ግን በስተመጨረሻ ነስር በነስር ሆነው ቤተክርስቲያን እንደገባች አሮጊት ውሻ ተዋርደው ተባረዋል።

በአባቱ ሲገረፍ የነበረ ልጅ፣ የራሱን ልጅ እንደሚገርፍ ሁሉ፣ የወያኔ ውርዴ ኦነግ-ሸኔዎችም አንዲት የፊደል ለውጥ ሳያደርጉ፣ የተለመደውን የፈሪዎችና የደንቆሮዎች የመከልከል ካርድ ሲመዙ ምን ያክል ወደ ኋሊት የሚነዱ ከብቶች እንደሆኑ ነው የሚያስመሰክሩት። ካድሬዎችና ጎጠኞች በስብሰው ሲወድቁ፣ አስቴርም፣ ቴዲም፣ ምኒልክም፣ አድዋም፣ ኢትዮዽያም አሁንም ወደፊትም ያበራሉ፣ ያንፀባርቃሉ። ይኸ የታሪክ ህግ ነው።

Horus wrote:
25 Feb 2023, 15:23



Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቴዲ አፍሮ፣ አጼ ምኒልክና አድዋ ! (መኖር ብዙ ያሳያል)!

Post by Horus » 25 Feb 2023, 20:16

Selam,
በሚቅጥሉት 4 ቀናት ብዙ ድራማ፣ ብዙ ቲያትር እናያለን ። የኦሮሞ ተገንጣይ ልፋት ምኒልክን ከአድዋ የሚገነጥል አድዋ እንደ ክብር ምኒልክ እንደ ወራሪ ለመተረክ የሚዳክሩት አዲሱ ቆሻሻ የጎሳ ናሬቲቭ ያው እንደ ተለመደው አፍንጫቸው ላይ ይፈነዳል ።

ታላቁ መሪ መቃብሩ ውስጥ እንዳያርፍ ይህን ዘመን ሁሉ ለፉ ባከኑ ። ዛሬ የኢትዮጵያ ማነንት፣ የሕዝቧ ህልውና መገለጫው ፈተና፣ ውዝግብ፣ የማይታለፍ ቀይ መስመር የኢትዮጵያ እናት እምዬ ምኒልክ ነው ።

ደሞ ትግሉ ይቀጥላል እንጂ አድዋን በወያኔ ባንዲራ አይከበርም ። ኣድዋን አለ ምኒልክ፣ ምኒልክን አለ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ወይ ፍንክች ! መንግስት የመጣል መንግስት ይሄዳል ! ማንም ይህን ቀይ መስመር ሊጥስ አይችልም !

ለሚቀጥለው 4 ቀናት ጆሮአችን በኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ እንደ ሚዶነቁር ተጠባበቅ!

Naga Tuma
Member+
Posts: 7392
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ቴዲ አፍሮ፣ አጼ ምኒልክና አድዋ ! (መኖር ብዙ ያሳያል)!

Post by Naga Tuma » 02 Mar 2023, 16:00

Horus wrote:
25 Feb 2023, 15:07
አርቲስት ሎሬት ቴዲ አፍሮ 'ጥቁር ሰው' የተሰኘው ታሪካዊ ደርሰቱን ተከትሎ በመንግስት መዋከብ ብቻ ሳይሆን በነጃዋር አስተባባሪነት የነፍጠኛው ምኒልክን ስም በናዝሬት ከተማ አታነሳም ተብሎ ኮንሰርት እንዳልተከለከለ እና አገር አቀፍ 'ጉዞ ወደ ፍቅር ' ኮንሰርቱን እንዳልሰረዘ ይህው ዛሬ የአቢይ አህመድ ኦሮሙማ አገዛዝ ሕዝቡ አንቅሮ ሲተፋው ምኒልክና አድዋ ቁጥር 1 የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆነው ቀረቡ!

መኖር ደግ ነው! Tempus ajax rerum! ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል፣ ግዜ ሁሉን ነገር ይበላል !
እንኳን ደስ ኣለህ፣ ኖረህ ስላየህ። ኣብዮተኞቹ ጓደኞች ሃገር እየተስተካከለች መሆኑን ተነስተዉ በሰሙ።

ታድያ ይህ ቴምፐስ ኣጃክስ ሪረም የሰነፎች መካሻ የአዲስ አበበ ዩኒቨርዚቲን መፈክር ወይም ሞቶ የማያልፍ የሚጠቀስ ነዉ? ኣንተ የሼክስፒር ኣንባቢ የላቲን ጠቃሽ። ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል? እንደዛ እያሉ መሆን አለበት ጋለሊዮ ጋሌሊን ኣስረዉ ከሶስት መቶ አመታት በሁዋላ ይቅርታ የጠየቁት። እንደዛ እያሉ መሆን አለበት የጀርመኑ ማርቲን ሉተር ከኢትዮጵያዊ የሃይማኖት ልሂቅ ተምሮ፣ ኣንተ እንዳልከዉ፣ ቀርፋፎች ብሎ የቀደማቸዉ። እንደዛ እያሉ መሆን አለበት ኣንዳንዶቹ ሃገር አሜሪካ ዉስጥ ተስፋ የቆረጡ የእንግሊዝ ክላዉኖች ሆነዉ ነቲንግ ዊል ቼንጅ በሚል ጥብቅና የኖሩት።

ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል? ኣንተ የኢትዮጵያ ኣብዮተኛ የእንግሊዙን ጆን ሌነን ሙዚቃ ኣዳማጭ፣ የመርካቶ ዱርዬ የቨሪታስ ብርቅነህ። ከመርካቶ ሳትወጣ እዛ የደረስክ መሰለህ? ደግሞ እንደልጅ እንዳታኮርፍ፣ ከፈለክ እንደልጅ ቦርቅ እንጂ፣ ኣንተ እየተጠቀስክ ፈተንኩ ባይ። ስትሳሳት እና ከእኔ መሆን አለበት ስትባል አመሰግናለሁ የማትል።

ከመሬት ላራሹ ኣብዮት ጀምሮ ብዙ ስለጣርክ ብዙ ይጠበቅብሃል። ታድያ የምኒልክ ቆሻሻ ሲሉ የት ነበርክ እና ነዉ ኣሁን ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል የምትለዉ? ለዚህ ነዉ የሰነፎች መካሻ የሆነዉ ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል ሳይሆን የጎበዞች ኢትዮጵያዊያን ጥረት፣ ጥሮ ግሮ መኖር፣ ብዙ ያሳያል የምትባለዉ። ለምሳሌ ሎሬቱ ቴዲ አፍሮ የቀነኒሳን ወደሁዋላ ዞሮ ዞሮ ወንድሙን ሀይሌን ማየት፣ ያዉም ፉክክር ላይ እያለ፣ ቀልቦ የሚልዮኖችን ቀልብ ስቦ አይኖቻቸዉን ያረጠበዉ ግዜን ጠብቆ ነዉ ወይስ ጥሮ ተጣጥሮ ነዉ? ግዜ ሁሉን ነገር ኣያመጣም፣ ግዜ ሁሉን ነግር ኣያሳይም። ጥረት ብዙ ያሳያል።

ያ ጥረት ነዉ ዛሬ ሌላ አድዋን የምያሰማህ። ተቀበላ። የላቲኖቹ ሃገረ ሮማ ወይም የሮማን ኤምፓየር ተከፋፍላ ቆይታ እንደ ኣዉሮፓ ህብረት ዳግም ተቋቋመች ሲባል የግኢዛዊያን እና ሌሎች ሃገረ ኢትዮጵያ ተርፋ ተስተካከለች ይባላል።

Horus
Senior Member+
Posts: 42805
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቴዲ አፍሮ፣ አጼ ምኒልክና አድዋ ! (መኖር ብዙ ያሳያል)!

Post by Horus » 02 Mar 2023, 22:08

Naga Tuma aka defend The Truth,
እኔ ሆረስ ካንተ ጋር አፍ የምካፈትበት ግዜው አልፏል! አሁን ካሻህ ሂድና አንብብ፣ የትግሬ እብሪተኛ እኛን መግፋት ተራራ መግፋት ነው እያለ ሲነፋ ምን እለው እንደ ነበር!!! አንተ ከና ስልጣን ላይ ወጥተህ ሳትጨርስ ያንን የእረኛ ጎማህን አተንፍሰን እያወረድንህ ነው! አሁን ትንሽ ጥሞና ያዝና የዛሬ 500 አመት እንዴት እንደ ታገልንህ ለማሰብ ሞክር! ያን የሚያደርግ አንጎል የለህም እንጂ!! ይህ ጨዋታ ገና መጸነሱ እንጂ በደምብም አልተጀመረም !! በኢትዮጵያ ማንም ነጭ አይደለም፣ እንዳንተ ያለ ጥቁር ጣሊያን የማይዘለው የቀይ መስመር ፋውል አለ!! ይህችን አባባሌ አትርሳት!!!

Post Reply