Horus wrote: ↑25 Feb 2023, 15:07
አርቲስት ሎሬት ቴዲ አፍሮ 'ጥቁር ሰው' የተሰኘው ታሪካዊ ደርሰቱን ተከትሎ በመንግስት መዋከብ ብቻ ሳይሆን በነጃዋር አስተባባሪነት የነፍጠኛው ምኒልክን ስም በናዝሬት ከተማ አታነሳም ተብሎ ኮንሰርት እንዳልተከለከለ እና አገር አቀፍ 'ጉዞ ወደ ፍቅር ' ኮንሰርቱን እንዳልሰረዘ ይህው ዛሬ የአቢይ አህመድ ኦሮሙማ አገዛዝ ሕዝቡ አንቅሮ ሲተፋው ምኒልክና አድዋ ቁጥር 1 የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆነው ቀረቡ!
መኖር ደግ ነው! Tempus ajax rerum! ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል፣ ግዜ ሁሉን ነገር ይበላል !
እንኳን ደስ ኣለህ፣ ኖረህ ስላየህ። ኣብዮተኞቹ ጓደኞች ሃገር እየተስተካከለች መሆኑን ተነስተዉ በሰሙ።
ታድያ ይህ ቴምፐስ ኣጃክስ ሪረም የሰነፎች መካሻ የአዲስ አበበ ዩኒቨርዚቲን መፈክር ወይም ሞቶ የማያልፍ የሚጠቀስ ነዉ? ኣንተ የሼክስፒር ኣንባቢ የላቲን ጠቃሽ። ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል? እንደዛ እያሉ መሆን አለበት ጋለሊዮ ጋሌሊን ኣስረዉ ከሶስት መቶ አመታት በሁዋላ ይቅርታ የጠየቁት። እንደዛ እያሉ መሆን አለበት የጀርመኑ ማርቲን ሉተር ከኢትዮጵያዊ የሃይማኖት ልሂቅ ተምሮ፣ ኣንተ እንዳልከዉ፣ ቀርፋፎች ብሎ የቀደማቸዉ። እንደዛ እያሉ መሆን አለበት ኣንዳንዶቹ ሃገር አሜሪካ ዉስጥ ተስፋ የቆረጡ የእንግሊዝ ክላዉኖች ሆነዉ ነቲንግ ዊል ቼንጅ በሚል ጥብቅና የኖሩት።
ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል? ኣንተ የኢትዮጵያ ኣብዮተኛ የእንግሊዙን ጆን ሌነን ሙዚቃ ኣዳማጭ፣ የመርካቶ ዱርዬ የቨሪታስ ብርቅነህ። ከመርካቶ ሳትወጣ እዛ የደረስክ መሰለህ? ደግሞ እንደልጅ እንዳታኮርፍ፣ ከፈለክ እንደልጅ ቦርቅ እንጂ፣ ኣንተ እየተጠቀስክ ፈተንኩ ባይ። ስትሳሳት እና ከእኔ መሆን አለበት ስትባል አመሰግናለሁ የማትል።
ከመሬት ላራሹ ኣብዮት ጀምሮ ብዙ ስለጣርክ ብዙ ይጠበቅብሃል። ታድያ የምኒልክ ቆሻሻ ሲሉ የት ነበርክ እና ነዉ ኣሁን ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል የምትለዉ? ለዚህ ነዉ የሰነፎች መካሻ የሆነዉ ግዜ ሁሉን ነገር ያመጣል ሳይሆን የጎበዞች ኢትዮጵያዊያን ጥረት፣ ጥሮ ግሮ መኖር፣ ብዙ ያሳያል የምትባለዉ። ለምሳሌ ሎሬቱ ቴዲ አፍሮ የቀነኒሳን ወደሁዋላ ዞሮ ዞሮ ወንድሙን ሀይሌን ማየት፣ ያዉም ፉክክር ላይ እያለ፣ ቀልቦ የሚልዮኖችን ቀልብ ስቦ አይኖቻቸዉን ያረጠበዉ ግዜን ጠብቆ ነዉ ወይስ ጥሮ ተጣጥሮ ነዉ? ግዜ ሁሉን ነገር ኣያመጣም፣ ግዜ ሁሉን ነግር ኣያሳይም። ጥረት ብዙ ያሳያል።
ያ ጥረት ነዉ ዛሬ ሌላ አድዋን የምያሰማህ። ተቀበላ። የላቲኖቹ ሃገረ ሮማ ወይም የሮማን ኤምፓየር ተከፋፍላ ቆይታ እንደ ኣዉሮፓ ህብረት ዳግም ተቋቋመች ሲባል የግኢዛዊያን እና ሌሎች ሃገረ ኢትዮጵያ ተርፋ ተስተካከለች ይባላል።