የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር
ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር
Clouds that look like things: Decipher this my mentally challenged friend!
በየቀኑ ከተተከለ ዛፍና ሳር መሐል ቆመው የኣሥር እና የኣስራ-አምስት ደቂቃ ቡራኬ የሚሰጡን ጠቅላይ ሚንስትር፥ ለምን በሳምንት ኣንዴ እንኳ ሌት ከቀን ከሚታረደውና ከሚፈናቀለው የኣማራ ደሃ መካከል ቆመው የመፅናናትን ድምፅ ሲያሰሙ አንመለከታቸውም? የግብዝ ትርጉም ካልገባህ ይኸውልህ፦ በኣካል ተገልጦልሃል ... ሥጋ ለብሶ ቆሞ ይራመዳል! በሚሊዩን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከበጋ ሀሩር፣ ከክረምት ብርድ መጠለያ ከሆናቸው የሳር ክዳን ጎጆ እያፈናቀለ፥ ሳር ሜዳ ላይ ቆሞ "አወድሰኝ" ይልሀል።
Assegid S. wrote: ↑28 Oct 2022, 09:16በየቀኑ ከተተከለ ዛፍና ሳር መሐል ቆመው የኣሥር እና የኣስራ-አምስት ደቂቃ ቡራኬ የሚሰጡን ጠቅላይ ሚንስትር፥ ለምን በሳምንት ኣንዴ እንኳ ሌት ከቀን ከሚታረደውና ከሚፈናቀለው የኣማራ ደሃ መካከል ቆመው የመፅናናትን ድምፅ ሲያሰሙ አንመለከታቸውም? የግብዝ ትርጉም ካልገባህ ይኸውልህ፦ በኣካል ተገልጦልሃል ... ሥጋ ለብሶ ቆሞ ይራመዳል! በሚሊዩን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከበጋ ሀሩር፣ ከክረምት ብርድ መጠለያ ከሆናቸው የሳር ክዳን ጎጆ እያፈናቀለ፥ ሳር ሜዳ ላይ ቆሞ "አወድሰኝ" ይልሀል።
"ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል በእልፍ አእላፍ ሬሳ" ... ነው ያለው ከያኒው
Assegid S. wrote: ↑05 Nov 2022, 11:09Hello A man of tomorrow (የነገ ሰው.) I just saw your comment and sorry for the late reply.
ምንም እንኳ "አንተም እንደነ ታምራት ካልሰገድክልኝ ነው የምትለው?"ያልከው ለቀልድ እንደሆነ ባውቅም እና ፈገግ ቢያደርገኝም፥ እውነታው ግን ... የስም አጋጣሚ ሆኖ ነው እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆኑ እኔ ጉልበታችንን እና አካላችንን ለስግደት ለማን እና ለማን ብቻ ማጠፍ እንዳለብን በደንብ እናውቃለን።
Y3n3g3s3w3 ... በቆየ አስተያየት ላይ ብዙ ማለት ባልፈልግም፤ እኔ ጠቅላይ ሚንስትሩን የምቃወመው ከመጠን ባለፈ ቸልተኝነታቸውና የማይታመን (አስመሳይ) ባህሪያቸው እንጂ ችግሮችን ለመፍታት ሞክረው ስላልተሳካላቸው አይደለም።
ገና ከጠዋቱ "ይኼ ነገር መስመር እየለቀቀ ነው ... ተረታችንም 'ሳይቃጠል በቅጠል' ነውና ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ መፍትሔ ይፈለግለት" ብለን ስንጮህ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በግብዝነትና ኦቨር ኮንፊደንስ (over confidence) "ኮሽ ባለ ቁጥር አትደንግጡ" እያሉ ስጋታችንን ከማቅለልም አልፈው፥ የከተማ ልጅና የዝንጀሮን ተረት እየጠቀሱ በየኣደባባዩ ሲያላግጡብን ይኸው ዛሬ ልንመልሳቸው የማንችላቸውን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንድናጣ አድርገውናል። በተደጋጋሚ "ኮሽታ" ሲሉ ያንኳሰሱት ህግ-አልበኝነት ከቀን ወደ ቀን ሳይታረም በመቅረቱ ዛሬ ላይ ነጎድጓድ ሆኖ የስንቱን ነፍስና decent ኑሮ ጉድጓድ ውስጥ ጨምሮታል።
Y3n3g3s3w3 ... ሰው ደካማ ሥጋ በመልበሱ "ይሳሳታል" በሚል ምክንያት ከተቃውሞም ሆነ ከነቀፉ ሊድን የሚችለው ቸልተኛ፣ ዘረኛና አስመሳይ ስለሆነ ሳይሆን፤ ሁሉ ነገር በተከሰተበት ቅፅበት ለመገኘትና ለማወቅ ሳይችል ሲቀር፣ ዛሬ መፍትሔ ይሆናል ብሎ የወሰደው ቅን እርምጃ ነገ ስህተት ሆኖ ሲገኝና በመሳሰሉት መመዘኛዎች ብቻ ነው። ምክንያቱም እነዚህ Omnipresent, Omniscient, Omnipotent, etc ባህሪያት አምላካዊ ብቻ ናቸውና።
መልካም ሰንበት ... ወንድም የነገ ሰው
Hello Y3n3g3s3w3; ያነበብኩትን የኣንተን እምነትና ምልከታ አከብርልሀለሁ። ያ ማለት ግን የእኔ እምነትና ምልከታ ከኣንተ ጋር ልዩነት የለውም ማለት አይደለም።Y3n3g3s3w wrote: ↑05 Nov 2022, 16:59Assegid S.,
እኔ የዶ/ር አብይን መንግስት ለተፈጠሩ ኝግሮች ሁሉ ተጠያቂ ለማረግ ምክንያት ያጥረኛል።
እውነቱን ለመናገር ከዚህ ጦርነት ቀደም ሲል በተለይ የአብይ መንግስት ወደ ስልጣን እንደመጣ ግጭቶችን ለመፍታት መንግስት ያሳይ የነበረው ትግስት(በወቅቱ እኔ ቸልተኝነት ነበር የምለው) በጣም እልህ አስጨራሽ ነበር። ነገር ግን እኔ በበኩሌ የችግሩን ጥልቀት እየተረዳሁ ስመጣና ምን ያህል ምዕራባውያን ተሳታፊ እንደነበሩ ሙሉ ግንዛቤ ሳገኝ ፣ ከተችነትና ጠዋት ማታ የመንግስትን ዳተኝነትና ቸልተኝነት ከማቀንቀንና ከማውገዝ ይልቅ በፍጥነት ወደ ድጋፍ፣ ማበረታታትና የቻልኩትን ወደ መርዳት ነው በቀጥታ የተሸጋገርኩት። አንዳንዶች የማይመቻቸው አንድ ትልቅ እውነታ አለ ፣ ይሄውም የአብይ መንግስት ከዜሮ የጀመረ መንግስት ሆኖ አሁን ግን ከፍተኛ አቅም የገነባ መሆኑ ነው። በወያኔ ደህንነት ውስጥ የኢትዮጵያ ደህንነት መስርቶ (ይሄ ሊሰመርበት ይገባል) እዚህ ደረጃ መድረስ ችሎታ ነው። በዚህ መሀል ነው እንግዲህ ራሱን የቻለ መንግስት(ከወያኔ ነፃ የሆነ) ለማረግ እየጣረ በነበረበት ወቅት ነው የትችት ናዳ ስናውርድበት የነበረው(እኔን ጨምሮ)። እነሱ(ወያኔዎቹ) መንግስት ውስጥና ወጭ ሆነው የመንግስትን ተዐማኝነት ለማጠልሸትና ከህዝብ ጋር ለማጋጨት ሲታገሉ ፣ መንግስት ደግሞ እራሱ ከወያኔ ተፅዕኖ ለማላቀቅና መንግስት ሆኖ ለመቀጠል የሚያስችለው አቅም እየገነባ ባለበት ሁኔታ ነው ዋናው ጦርነት የተጀመረው። ከዛማ 300ሺ ጦር ከ44ሺ ጦር ጋር ገጥሞ ነው የሰው ዱቄት በድሮን ሲቦን ያሳየን፤ እዛው ላይ ነው እነግዲህ ምዕራባውያኑ ምን ያህል እንደ ዱቄት የቦነነውን የወያኔ ዱቄት መልሰው ነፍስ ዘርተውበት እዚህ ያደረሱን። አሁንም አንዳንዶች "ዱቄቱን ወደ TDF የቀየረው የአብይ መንግስት ስተት/ቸልተኝነት/አጉል ንቀት ነው ሲሉ ይደመጣል- ይሄ ተልቅ ስተት ነው። አስታውሱ የኢትዮጵያ ጦር 44ሺ ነበር ፣ ምዕራባውያን በተራድዖ ድርጅቶቻቸው ትግራይ ገብተው ጦርነቱን ህዝባዊ ጦርነት ነው ያረጉት። ይሄን የአብይ መንግስት መተንበይ ይችል ነበር? ? እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ no f****n way! ! ማናችንም የምዕራቡ አለም ኢትዮጵያን ለመውጋት ወያኔ ላይ ያን ያህል ኢንቨስት ያረጋል ብለን፤ 15 ጊዜ የተመድ የፀጥታ አማካሪ (UNSC)ይሰበሰባል ብለን ገምተን አልመን አናቅም። መተቸት ቀላል ነው ፣ትችት እውነታን ያገናዘበ ሲሆን ለራስም ለተተችውም ይጠቅማል እላለሁ።