Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Y3n3g3s3w » 27 Oct 2022, 16:47

Good job boys! (ይሄንንም ደሞ ማሽቃበጥ ነው በሉ).... :lol:

የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር

ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Y3n3g3s3w » 28 Oct 2022, 00:09

by 'we' you mean the entire organization/association....
Deciphering you acronym name was agreat service for the forum(ER)
TGray Association of north AMerica

A wolf in sheep's skin .....
TGAA wrote:
27 Oct 2022, 18:25
No Sir, we know one when we see one. :wink:

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by TGAA » 28 Oct 2022, 00:32

Y3n3g3s3w wrote:
28 Oct 2022, 00:09
by 'we' you mean the entire organization/association....
Deciphering you acronym name was agreat service for the forum(ER)
TGray Association of north AMerica

A wolf in sheep's skin .....
TGAA wrote:
27 Oct 2022, 18:25
No Sir, we know one when we see one. :wink:
Clouds that look like things: Decipher this my mentally challenged friend!

Selam/
Senior Member
Posts: 16874
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Selam/ » 28 Oct 2022, 02:55

Why would you be surprised if social media morons call this ማሽቃበጥ? Let alone joyful faces, a tragedy upsets them because they don’t know what they want.

Y3n3g3s3w wrote:
27 Oct 2022, 16:47
Good job boys! (ይሄንንም ደሞ ማሽቃበጥ ነው በሉ).... :lol:

የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር

ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Assegid S. » 28 Oct 2022, 09:16

Y3n3g3s3w wrote:
27 Oct 2022, 16:47

በየቀኑ ከተተከለ ዛፍና ሳር መሐል ቆመው የኣሥር እና የኣስራ-አምስት ደቂቃ ቡራኬ የሚሰጡን ጠቅላይ ሚንስትር፥ ለምን በሳምንት ኣንዴ እንኳ ሌት ከቀን ከሚታረደውና ከሚፈናቀለው የኣማራ ደሃ መካከል ቆመው የመፅናናትን ድምፅ ሲያሰሙ አንመለከታቸውም? የግብዝ ትርጉም ካልገባህ ይኸውልህ፦ በኣካል ተገልጦልሃል ... ሥጋ ለብሶ ቆሞ ይራመዳል! በሚሊዩን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከበጋ ሀሩር፣ ከክረምት ብርድ መጠለያ ከሆናቸው የሳር ክዳን ጎጆ እያፈናቀለ፥ ሳር ሜዳ ላይ ቆሞ "አወድሰኝ" ይልሀል።

"ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል በእልፍ አእላፍ ሬሳ
" ... ነው ያለው ከያኒው

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Y3n3g3s3w » 28 Oct 2022, 17:30

It's not that I care much Just wanted to make the likes of TGAA(TiGray Association of North America aka wolf in a sheep's skin) pull their remaining hair out :twisted:
Selam/ wrote:
28 Oct 2022, 02:55
Why would you be surprised if social media morons call this ማሽቃበጥ? Let alone joyful faces, a tragedy upsets them because they don’t know what they want.

Y3n3g3s3w wrote:
27 Oct 2022, 16:47
Good job boys! (ይሄንንም ደሞ ማሽቃበጥ ነው በሉ).... :lol:

የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር

ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by TGAA » 28 Oct 2022, 21:22

ማሽቃበጥ Whether justified or not it is within your right to do. The problem arises when you try to convince us to dance to every tune of Walta and ETV as zombies. We don't support or oppose for its own sake, but we take the whole and judge the particular. The blind supporter bunches tend to do the reverse and anyone who questions the validity or the relevancy of the particular to the general is called public enemy number one. Don't try to reinvent the wheel again -- it's a tried and tired propagandist tactic of weyanes to attack anyone who questions their hyperbolic statements. You are falling for the same trap.

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Y3n3g3s3w » 29 Oct 2022, 10:38

ዶር አብይም ሆነ መንግስታቸው እንከን የለባቸውም የሚል እምነት በፍፁ አይነካካኝ ፣ እንደሰውና ሰው እንደሚመራው መንግስት ሁለቱም ፍፁም አይሆኑም ነገር ግን እየተፍጨረጨሩበት ስላለው ትግልና አገሪቷን ወደ ተሻለ አቅጣጫ ለመምራ የሚያደርጉትን ጥረት ግን ባልደግፍ ወይም ባላበረታታ ከራሴም ጋር እንኳን ተስማምቼ አላድርም ፣ በወያኔ ድንዙዛን ስርዐት ውስጥ ሲዳክሩ የነበሩ የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይ ለምሳሌ አማራውን ብንወስድ ፤ ሲወገዝ፣ ስም ሲወጣለት ፣ሲገደል ፣ ሲሰደድ ፣ ትውልድ ሀገሩ ገሀነም ሆናበት ለ 27 አመት ሲዳክር ቆይቶ ይሄው ዛሬ እራሱን ነፃ ሊያወጣ ዳር ሲደርስ እዚጋ አንዱ ቀዝብ ተነስቶ የሰሜን ሰዎች ሰለሆንን ከወያኔ ጋር እናብር እዛ ጋ የአብይን መንግስት ለመታገል የ12ኛ ክፍል ፈተና እምቢ በል(~13000 ተማሪ ሜዳ ላይ ዘረገፏቸው)፤ የወያኔው ዘመን አንሶት አሁን ደሞ ላንተ ነው የምንታገለው የሚሉት ግራ ሊያጋቡት ይጋጋጣሉ:: ተስፋ ሰጪው ነገር ግን አብዛኛው ሀገሩ ውስጥ ያለው ህዝብ ከመንግስት ጋር ሆኖ ዋና ጠላቱን ለይቶ እየመታው ነው። ምክንያቱ ደግሞ ቀላል ነው ፣ይሄ ጦርነት በኢትዮጵያና በምዕራቡ አለም መካከል እንደሆነ እኮ አዕምሮና አይኑ ላልታወረ ወይም ሌላ የራሱ እቅድ ለሌለው ኢትዮጵያዊ መረጃውማ ሞልቶ ተትረፈረፈ።
እና ኢትዮጵያውያን በምን መስፈርት ነው ምዕራባውያኑን እየተፋለመ ያለን መንግስት የሚቃወሙት?? በርግጥ የአብይ መንግስ ብዙ ውስጣዊ ተግዳሮቶች አሉበት ዳሩ ግን ሁሉም በሚባል ደረጃ የተያያዙ ናቸው ምንጫቸውም ከአብይ መንግስ ለምዕራቡ አለም እንደወያኔ እጅ አልሰጥም ከማለቱ ይመነጫል። ይሄን የሚከራከር ካለ እሱ ዘገምተኛ ነው ወይም ሌላ ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለራሱ የተደበቀ እቅድ አለው ።

አሰግድ, ወደ አንተ ስንመጣ ፣

ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ( በነገራችን ላይ ጠ/ሚንስትሩ በቀን ስንት ሰዐት እነደሚያርፍ ግን ማወቅ እፈልጋለሁ) በምሳሌነት እያሳየ ፣ እንስራ እንደግ የሚልህን ፣ ህዝብ በአብላጫ ድምፅ የመረጠውን መንግስት ምንድነው አርግ የምትለው? አስገራሚው ጉዳይ የአብይ መንግስት የሚከሰስባቸው (ጦርነቱ፣የህዝቦች መፈናቀል፣ ግድያው ፣ ወስጣዊ ሰላሙ ....ወዘተ) ድርጊቶች በሙሉ የሚቀነባበሩት በከሳሾቹ ነው። ይሄህ ለመገንዘብና በረጋ መንፈስ ለመመርመር እንዴት ጊዜና ትግስት አጣህ? ወይስ አንተም እንደነ ታምራት ካልሰገድክልኝ ነው የምትለው?

Assegid S. wrote:
28 Oct 2022, 09:16
Y3n3g3s3w wrote:
27 Oct 2022, 16:47

በየቀኑ ከተተከለ ዛፍና ሳር መሐል ቆመው የኣሥር እና የኣስራ-አምስት ደቂቃ ቡራኬ የሚሰጡን ጠቅላይ ሚንስትር፥ ለምን በሳምንት ኣንዴ እንኳ ሌት ከቀን ከሚታረደውና ከሚፈናቀለው የኣማራ ደሃ መካከል ቆመው የመፅናናትን ድምፅ ሲያሰሙ አንመለከታቸውም? የግብዝ ትርጉም ካልገባህ ይኸውልህ፦ በኣካል ተገልጦልሃል ... ሥጋ ለብሶ ቆሞ ይራመዳል! በሚሊዩን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከበጋ ሀሩር፣ ከክረምት ብርድ መጠለያ ከሆናቸው የሳር ክዳን ጎጆ እያፈናቀለ፥ ሳር ሜዳ ላይ ቆሞ "አወድሰኝ" ይልሀል።

"ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል በእልፍ አእላፍ ሬሳ
" ... ነው ያለው ከያኒው

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Assegid S. » 05 Nov 2022, 11:09

Hello A man of tomorrow (የነገ ሰው.) I just saw your comment and sorry for the late reply.

ምንም እንኳ "አንተም እንደነ ታምራት ካልሰገድክልኝ ነው የምትለው?"ያልከው ለቀልድ እንደሆነ ባውቅም እና ፈገግ ቢያደርገኝም፥ እውነታው ግን ... የስም አጋጣሚ ሆኖ ነው እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆኑ እኔ ጉልበታችንን እና አካላችንን ለስግደት ለማን እና ለማን ብቻ ማጠፍ እንዳለብን በደንብ እናውቃለን።

Y3n3g3s3w3 ... በቆየ አስተያየት ላይ ብዙ ማለት ባልፈልግም፤ እኔ ጠቅላይ ሚንስትሩን የምቃወመው ከመጠን ባለፈ ቸልተኝነታቸውና የማይታመን (አስመሳይ) ባህሪያቸው እንጂ ችግሮችን ለመፍታት ሞክረው ስላልተሳካላቸው አይደለም

ገና ከጠዋቱ "ይኼ ነገር መስመር እየለቀቀ ነው ... ተረታችንም 'ሳይቃጠል በቅጠል' ነውና ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ መፍትሔ ይፈለግለት" ብለን ስንጮህ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በግብዝነትና ኦቨር ኮንፊደንስ (over confidence) "ኮሽ ባለ ቁጥር አትደንግጡ" እያሉ ስጋታችንን ከማቅለልም አልፈው፥ የከተማ ልጅና የዝንጀሮን ተረት እየጠቀሱ በየኣደባባዩ ሲያላግጡብን ይኸው ዛሬ ልንመልሳቸው የማንችላቸውን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንድናጣ አድርገውናል። በተደጋጋሚ "ኮሽታ" ሲሉ ያንኳሰሱት ህግ-አልበኝነት ከቀን ወደ ቀን ሳይታረም በመቅረቱ ዛሬ ላይ ነጎድጓድ ሆኖ የስንቱን ነፍስና decent ኑሮ ጉድጓድ ውስጥ ጨምሮታል።

Y3n3g3s3w3 ... ሰው ደካማ ሥጋ በመልበሱ "ይሳሳታል" በሚል ምክንያት ከተቃውሞም ሆነ ከነቀፉ ሊድን የሚችለው ቸልተኛ፣ ዘረኛና አስመሳይ ስለሆነ ሳይሆን፤ ሁሉ ነገር በተከሰተበት ቅፅበት ለመገኘትና ለማወቅ ሳይችል ሲቀር፣ ዛሬ መፍትሔ ይሆናል ብሎ የወሰደው ቅን እርምጃ ነገ ስህተት ሆኖ ሲገኝና በመሳሰሉት መመዘኛዎች ብቻ ነው። ምክንያቱም እነዚህ Omnipresent, Omniscient, Omnipotent, etc ባህሪያት አምላካዊ ብቻ ናቸውና።

መልካም ሰንበት ... ወንድም የነገ ሰው

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: የአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያንን ለልጆቻችን እናስረክባለን -ጠ/ሚኒስትር ፤፤፤ማሳካት የፈለግነውን 100 በ 100 በሚባል ደረጃ አሳክተናል -ትምርት ሚኒስትር

Post by Y3n3g3s3w » 05 Nov 2022, 16:59

Assegid S.,

እኔ የዶ/ር አብይን መንግስት ለተፈጠሩ ኝግሮች ሁሉ ተጠያቂ ለማረግ ምክንያት ያጥረኛል።

እውነቱን ለመናገር ከዚህ ጦርነት ቀደም ሲል በተለይ የአብይ መንግስት ወደ ስልጣን እንደመጣ ግጭቶችን ለመፍታት መንግስት ያሳይ የነበረው ትግስት(በወቅቱ እኔ ቸልተኝነት ነበር የምለው) በጣም እልህ አስጨራሽ ነበር። ነገር ግን እኔ በበኩሌ የችግሩን ጥልቀት እየተረዳሁ ስመጣና ምን ያህል ምዕራባውያን ተሳታፊ እንደነበሩ ሙሉ ግንዛቤ ሳገኝ ፣ ከተችነትና ጠዋት ማታ የመንግስትን ዳተኝነትና ቸልተኝነት ከማቀንቀንና ከማውገዝ ይልቅ በፍጥነት ወደ ድጋፍ፣ ማበረታታትና የቻልኩትን ወደ መርዳት ነው በቀጥታ የተሸጋገርኩት። አንዳንዶች የማይመቻቸው አንድ ትልቅ እውነታ አለ ፣ ይሄውም የአብይ መንግስት ከዜሮ የጀመረ መንግስት ሆኖ አሁን ግን ከፍተኛ አቅም የገነባ መሆኑ ነው። በወያኔ ደህንነት ውስጥ የኢትዮጵያ ደህንነት መስርቶ (ይሄ ሊሰመርበት ይገባል) እዚህ ደረጃ መድረስ ችሎታ ነው። በዚህ መሀል ነው እንግዲህ ራሱን የቻለ መንግስት(ከወያኔ ነፃ የሆነ) ለማረግ እየጣረ በነበረበት ወቅት ነው የትችት ናዳ ስናውርድበት የነበረው(እኔን ጨምሮ)። እነሱ(ወያኔዎቹ) መንግስት ውስጥና ወጭ ሆነው የመንግስትን ተዐማኝነት ለማጠልሸትና ከህዝብ ጋር ለማጋጨት ሲታገሉ ፣ መንግስት ደግሞ እራሱ ከወያኔ ተፅዕኖ ለማላቀቅና መንግስት ሆኖ ለመቀጠል የሚያስችለው አቅም እየገነባ ባለበት ሁኔታ ነው ዋናው ጦርነት የተጀመረው። ከዛማ 300ሺ ጦር ከ44ሺ ጦር ጋር ገጥሞ ነው የሰው ዱቄት በድሮን ሲቦን ያሳየን፤ እዛው ላይ ነው እነግዲህ ምዕራባውያኑ ምን ያህል እንደ ዱቄት የቦነነውን የወያኔ ዱቄት መልሰው ነፍስ ዘርተውበት እዚህ ያደረሱን። አሁንም አንዳንዶች "ዱቄቱን ወደ TDF የቀየረው የአብይ መንግስት ስተት/ቸልተኝነት/አጉል ንቀት ነው ሲሉ ይደመጣል- ይሄ ተልቅ ስተት ነው። አስታውሱ የኢትዮጵያ ጦር 44ሺ ነበር ፣ ምዕራባውያን በተራድዖ ድርጅቶቻቸው ትግራይ ገብተው ጦርነቱን ህዝባዊ ጦርነት ነው ያረጉት። ይሄን የአብይ መንግስት መተንበይ ይችል ነበር? ? እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ no f****n way! ! ማናችንም የምዕራቡ አለም ኢትዮጵያን ለመውጋት ወያኔ ላይ ያን ያህል ኢንቨስት ያረጋል ብለን፤ 15 ጊዜ የተመድ የፀጥታ አማካሪ (UNSC)ይሰበሰባል ብለን ገምተን አልመን አናቅም። መተቸት ቀላል ነው ፣ትችት እውነታን ያገናዘበ ሲሆን ለራስም ለተተችውም ይጠቅማል እላለሁ።

Assegid S. wrote:
05 Nov 2022, 11:09

Post by Assegid S. » 06 Nov 2022, 12:19

Y3n3g3s3w wrote:
05 Nov 2022, 16:59

Hello Y3n3g3s3w3; ያነበብኩትን የኣንተን እምነትና ምልከታ አከብርልሀለሁ። ያ ማለት ግን የእኔ እምነትና ምልከታ ከኣንተ ጋር ልዩነት የለውም ማለት አይደለም።

ትዕግስተኛነት፦ በእኔ ትርጓሜ ... በራስ ላይ የሚደርስን ጥቃት ለመሸከም የሚያስችል ደልዳላ ትከሻ እንጂ፥ የሰውን መከራ ተመልክቶ ለመዳኘት የማያስችል ደንዳና ልብ ባለቤት መሆን አይደለም። እስቲ ባሳለፍናቸው ዓመታት ሁሉ በጠቅላይ ሚንስትሩም ሆነ የእኔ ብለው በሚጠሩዋቸው ቤተሰቦች አልፎም የቅርብ ዘመድ-ኣዝማዶች ላይ ምን ጥቃት ደረሰ? መልሱ በሹመታቸው ማግስት በርቀት ጧ ብላ እንደ ልደት ፊኛ ከፈነዳች ቦንብ በስተቀር የሰማነውም ሆነ ያየነው ነገር የለም። ይኽን የምለው እንደ እሳቸው ግለኛ ሆኜ ለማሰብ እየሞከርኩ እንጂ፥ እንደተሰጣቸው ኃላፊነትም ሆነ ሰው ሆነው እንደመፈጠራቸው፥ የእያንዳንዱ ዜጋ ጥቃት የእርሳቸውና የቤተሰባቸው ጥቃት ሆኖ ሊሰማቸው ይገባ ነበር።

ትዕግስት፦ የሰውን አንገት በሜንጫ እያስቆረጠ በሞት ንግድ ያተረፈን ከበርቴ በታጣቂ አስከብበው እየተከላከሉ፥ single mom የሆነችን ምስኪን ጋዜጠኛ ከህፃን ልጇ ነጥሎ ማሰር አይደለም። ይኼ ንፁህ ዘረኝነት ነው። ሰውን ለመግደል በጠራራ ፀሐይ ካራ ተሸክሞ የከተማን አደባባይ በሞተር ሳይክል ሲጋልብ የሚያመሽን ግለሰብ፣ በየሶሻል ሚዲያው እግሩን አንፈራጦ “ሳንጨራረስ ኣማራ ከክልሌ በሰላም ይውጣ!” እያለ የሚፎክርን “ሰባኪ” እንዳላየ እያለፉ፥ ይህን ተቃውመው የተናገሩና የፃፉ ግለሰቦችን ... ወንድ - ሴት፣ ወጣት- ኣዛውንት ሳይሉ … አቶ ታድዮስ ታንቱን ጨምሮ ዘብጥያ ማወረድ ወገንተኝነት እንጂ ታጋሽነት አይደለም።

በእኔ እምነት፦ የደሃን ደም፣ የምስኪኑን እንባ እንደ moisturizer lotion እየተቀባ በኣደባባይ መልካምና ለሀገር አሳቢ መስሎ ለመታትየት መሞከር "ታጋሽ" ሳይሆን PURE EVIL መሆን ነው።

በአጠቃላይ፦ ኦሮሞ በጥፋቱ ሲታሰር ኣማራን እንደ አልባሌ ወረቀት ቆጥሮ "አባሪ" አድርጎ መላክ፣ ዜጎችን ወደ ከተማቸው “አትገቡም!” ብሎ በር ዘግቶ ማጉላላት “ጠንካራ መንግስት እንደ መገንባት ” ሆኖ ከተቆጠረ … ምናለ “ይሁና!” ብቻ ሳይሆን “ልናይ ኋላ!” ያስብላል። እውነት ለመናገር ይህ መንግስት በያዘው አስተዳደራዊ ፍልስፍና … ከህዝባዊ ይልቅ አሁን ባለው ወታደራዊ አገዛዝ ውስጥ ቢቆይ የተሻለ ህልውና (ዕድሜ)ይኖረዋል።

ከዚህ ባለፈ ግን፦ በኣንዳንድ ውስጣዊ ችግሮቻችን ላይ የህወሃትንም ሆነ የውጭ ሀገራትን ኣሻራ ለማየት አይኔ የታወረ አይደለም። ምክንያት ሊሆኑ በማይገባቸው ቦታ ላይ ሁሉ ምክንያት ሆነው ሲቀርቡ ደግሞ "ትክክል ነው" ብዬ ለመቀበል አእምሮዬ አልዶለዶመም፤ ስለዚህም "አግባብ አይደለም" ብዬ እቃወማለሁ። አለበለዚያ ... ይህ መንግስት መቼም ቢሆን ከማሳበብና ውንጀላ ነፃ አይወጣም። የሰበቡን ሽግግር ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ ህወሃት ... ከህወሃት ወደ ውጪ-ጫና እንደሄደ ሁሉ፤ ከውጪ-ጫና ሌላ ምክንያት የሚሆን ቢጠፋ እንኳ፥ "ነብያቶቹ" እጅግ በጣም ደፋር ሆነው ሚስትን በባሏ ላይ እንደተነሳች አድርገው ለመክሰስ እንደማይመለሱ ማስረጃ ሰጥተውናል።

መልካም ሰንበት ... Brother.

Post Reply