በእውነቱ ሁላችሁም ወንድሞች በዚህ ጉዳይ ላይ ያቀረባችሁት መረጃ በምንም መልኩ አላስቀየመኝም። ምናልባት ከእኔ ሃሳብ አቀራረብ የማብራርያ ነጥብ ጉድለት ካልሆነ በስተቀር። ሁላችንም በዚህ ፎረም ላይ የበለጠ ለማወቅ እና ሃሳብ በመስጠት የተሻለ እውቀት ለመገብየት - ሌሎችም እውነቱን እንድረዱት የማድረግ ስራ ነው ብየ አምናለሁ። አንዳዶች በእርግጥ የፓለቲካ : የማሳሳት እና የማሳመን ስራዎች ላይ የተሰማሩም አሉ - ወቱትን ጥቁር ነው የሚሉ። እኔ ግን ከእነዚህ ተርታ አንድም ቀን የለሁበትም።
ትምህርት አያልቅም። አንድ መሪ ቃል አውቃለሁ - ሁሉም ቦታ ትምህርት ቤት ነው። ሁላችንም በህይውት ተገደን ይሁን ወደን ትምህርት ቤት ተወልደን በትምህርት ቤት ወስጥ እና ሞታለን። ስለዚህ ይህ ፎረም ትምህርት ቤት ነው - ኢ-መደበኛ ትምህርት ቤት - በቅጡ ለተረዳው የፓለቲካ ቅጥፍና ሳይጨምርበት።
-- አጠር ባለ መልኩ በዚህ ዙሪያ አስተያየቴን በሴም ቋንቋዎች ዙሪያ ልቋጭ። በእርግጥ በቀረቡት ማስረጃዎች መሰረት የሴም ቋንቋዎች መሰረታዊ ዝምድና እና የጋራ ግንድ ያለቸው መሆኑ ግልጽ ነው። ለእኔ ይህ አያሰደንቀኝም ምክንያቱም በመልክዐ ምድር እና በህዝብ አሰፋፈር እንደ ዛሬው አገር በፓለቲካ ካርታ ሳይካለል ተፈጥሮአዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር ነበር። በስነ-ሰብዕ ጥናትም ኩታ-ገጠም ህዝቦች ተመሳሳይ እና ተቀራራቢ የባህል እና የስነ-ልሳን ተግባቦዎች እና ውርሶች አሏቸው። አለም አሀጉር፥አሀጉር ደግሞ የኢኮኖሚ እና የፓለቲካ የበላይነት መለኪያ እና ማወዳደርያ በዚህ ዘመን ሲሆን አፍሪካዊያኑ ሰሜቲክስ በነባሩ ሳይሆን ከማዶው ማሰብ ጀመሩ - አንዳንዶች ከዚያ ማዶ ነበርን ብሎ ህሌናቸውን ማዞር። ምናልባትም ሶስት ወይም አራት ልሳኖች ብቻ አይደሉም በርካታዎች ከባህር ማዶ የመጥተናል አፈታሪክ የመፈልሰፍ። ይህ ትክክል አይደለም - ነባር ሴሜቲክ ህዝቦች በአፍሪካ ነበሩ አሁንም አሉ ለማለት ነው። እነኝህ ህዝቦች የስልጣኔ አብሪ ክዋክብት ነበሩ። እኔ የማልስማማበት ከባህር ማዶ መጣን የሚለውን ነው። በእርግጥ ፍልሰት ህዝብ በታሪክ ያንቀሳቅሳል - ከአፍሪካ ወደ ውጭ ከውጭ ወደ አፍሪካ ተሰባጥሯል ይህ ማለት ግን የአፍሪካን ሴማዊ ሚዝን ለውጧል ማለት አይቻልም።
Abe Abraham wrote: ↑11 Feb 2022, 18:51Abere wrote: ↑11 Feb 2022, 18:31Good point! Geographic proximity is a factor involved , it this should not be what originated where. I noticed people generally in Ethiopia look for a thread to connect their roots somewhere outside. The truth is , Ethiopia is the origin. For instance, researchers agreed that the origin of Arabic language or Semitic language is in Ethiopia, not the Arab world or the middle east we know now today. But it is not uncommon to hear some to believe differently. Simply there is sea between Africa and the middle east does not mean they are not geographically connected.
ወንድሜ ኣበረ
መመራመር የሚያስቆጣ ከሆነ ለምን ሓሳብህን ኸኛ ጋር ትካፈላለህ ? ሁሉ ነገር እንደ ብሩህ/obvious ከተወሰደ ለምን ኣባትህና እናትህ ወደ ትምህርት ቤት ላኩህ ? ለኔም እንደሱ ማለት ነው ። ስለ'ዚ ኣቀራረብህ ኣልገባኝም።
![]()