Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
pushkin
Member+
Posts: 9690
Joined: 23 Jul 2015, 06:10

የሰሞኑ የውሸት ዜናዎች Fake ስዕሎችና ቪዲዮዎች!!!!

Post by pushkin » 25 Jun 2021, 05:54

አሁን ዋነኛው የፕሮፓጋንዳና የውሸት ምንጩ የብላታ ሃይለማርያም ልጅ ወይም የሊላይ ሃይለማርያም ወንድም ነው። ርዝራዡ መመሪያ የሚቀበለው ከካሳ ሃይለማርያም ነው። ሰዉ የሚያውቀው እነ አሉላ ሰሎሞንን እነ ስታሊን ገብረስላሴን ነው። ከካሳ ሃይለማርያም ጋር ሲነፃፀሩ እነዚህ ድንክየዎች ናቸው። ካሳ ሃይለማርያም ከትግርኛና ከእንግሊዝኛ ውጪ አንድም ቀን ባማርኛ ፅፎ አያውቅም !!

:arrow: ከሶስት ወር በፊት april 6 ቀን ካሳ ሃይለማርያም አንድ ወሳኝ መመሪያ አውጥቷል።ምንም አዲስ ነገር የለውም።አሁን ርዝራዡና ደጋፊዎቹ ያንን መመሪያ እየተገበሩት ነው።

:arrow: መመሪያው የወጣው አንድ የውሸት ምስል ከተጋለጠ በኋላ ነው ። ታስታውሱ እንደሆነ ደብረፂዮን በረሃ ውስጥ እየጨፈረ የሚያሳየው አነጋጋሪ ምስል በተለጠፈ ማግስት ነው።ምስሉን በመጀመሪያ የለጠፈው ካሳ ሃይለማርያም ነው።

:arrow: April 6 ላይ ካሳ ሃይለማርያም ለርዝራዡ ባስተላለፈው መመሪያ ላይ ምን ፃፈ?

- የውሸት መረጃዎችን የማሰራጨት አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥቶ ፅፏል

- ፌክ ፎቶዎች መለጠፍን የሚያስተምር አጭር ኮርስ ሰጥቷል

በዚህ ፅሑፉ ላይ------

1- የውሸት መረጃዎችን ከመጠቀም ወደኋላ ማለት እንደሌለባቸው ገልጿል።ቃል በቃል 'መሳቀቅ' የለባችሁም ብሏል-

2- የውሸት መረጃዎችን ከመለጠፋቸው በፊት መረጃው በቀላሉ እንዳይጋለጥ መውሰድ ስላለባቸው ቅድመ ጥንቃቄ ለማስረዳት ሞክሯል።
በተለይ የቆየ ፎቶ ሲጠቀሙ ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ እንዲህ ይላል።

የተላከላችሁን ፎቶ originality ማጥፋት አለባችሁ። ይህንን ለማድረግ ፎቶውን በሞባይላችሁ እንደገና ማንሳት ይገባል።ይህን ስናደርግ የፎቶው location እኛ ያለንበትን ቦታ ነው የሚጠቁመው። ከዛ በኋላ save እናደርገዋለን። ይህን ካደረግን በኋላ ቀጣዩ ስራ የፎቶውን Back ground መቀየር አለብን።

በመጨረሻም ምስሉን crop እናደርገዋለን።ዛሬ ደብረፂዮን ሲጨፍር የሚያሳየው ምስል እነዚህን ፈተናዎች ያለፈ ምስል ነው። ጠላት location ሊያውቅ ይቅርና ጭፈራው የበረሃ ይሁን የከተማ ምንነቱን ለማወቅ አይችልም።

እናማ ወዳጄ ....አዲግራትን ተቆጣጥረናል ብለው በተናገሩ በሰዓታት ልዩነት ሰላማዊ ህዝብ ተጨፈጨፈ ብለው የማለቃቀሳቸው ምስጢር ምን ይመስልሃል ??
ለቀናት celebrate ማድረጉ እንኳን ቢቀር አንድ ቀን ማደር የማይችል ድል አለ'ንዴ ?

ምክንያቱ ግን ነገረ ስራቸው በሙሉ ውሸት ውሸት ውሸትና ውሸት ስለሆነ ብቻ ነው !!!!

ስርዝ ድልዞች ናቸው !!

(የተሰመሩባቸውን ቃላት በደንብ ተመልከቷቸው)





Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: የሰሞኑ የውሸት ዜናዎች Fake ስዕሎችና ቪዲዮዎች!!!!

Post by Ejersa » 25 Jun 2021, 07:01

ጁንታው በሴረኝነት ብቻ ነው የተካነው! ምን የሚባል የክፉዎች ምክር አላቸው? "ዋሽ ነገር ግን በምትዋሽ ጊዜ ቲኒሽም ብትሆን እውነት አትቀላቅልበት! በቃ እስከመጨረሻው ድረስ ዋሽ! የእውነታው ድራሹ እስከማይታወቅ ድረስ በውሸትህ ፅና! ሁሉም እራሱን መጠራጠር እስኪጀምር ድረስ ውሸትን አቀናብራት ሽፋን እንድታገኝ አድርጋት፣ ሀሰተኛ ዘገባ ዘግብ! ማንም በያምንህም በውሸትህ ፅና! በእሷ ላይ ተመስርተህ ቀጣይ እርምጃህን ፈፅም! እራስህ የፈጠርከውን ሀሰት እራስህ አሰራጨው ከዚያም ለእርሱ የሚመጥን እርምጃ ውሰድ። ያኔ ሁሉም ሰው በግራ መጋባት ውስጥ ሁኖ ጆሮ ይሰጥሀል! በተቻለ መጠን የሀሰት ማስረጃዎችን አሰራጭ! ያሰራጨኸውን ሀሰተኛ መረጃ የሚያጠናክሩ የሀሰት ምስክሮችን ከያቅጣጫው አዘጋጅተህ አቅርብ።

የሚያውቁህ በሙሉ አያምኑህም አይሰሙህም! እነርሱን እርሳቸው! አይናቸው እያየ ጆራቸው እየሰማ በአደበባይ ሀሰተኛ መረጃን ልቀቅ እነርሱ እውነቱን ስለሚያውቁ እነርሱን ለማሳመን አትጃጃል! ይልቅ በተደራሽነትህ ተጠቅመህ ቅደማቸውና ያንተ ሀሰት የእነርሱን እውነታ እንዲሸፍን አድርግ! ያኔ በዙሪያህ ያለው ህዝብ እውነቱን ስለሚያውቅ አንተን እነ የሀሰት ፕሮፓጋንዳህን አምርሮ ነመጥላት ውጭ ምንም አያመጣም! ነገር ግን ያንተ መረጃ በመላው አለም ተቀባይ ይሆናል! ተቃዋሚወችህ እውነቱን በእጃቸው ይዘው ቁመው ይቀራሉ ! የማያውቅህ የሩቅ ሰው ግን አማራጭ አጥቶ ከአንተ ጎን የመሆን እድል ይኖረዋል።

ተቃዋሚወችህ አንተ ደረሰብኝ ያልከውን ሁሉ ባይፈፅሙትም አንተ እራስህ እነርሱን መስለህ ድርጊቱን ተውነው ንፁሀን ተገደሉብኝ ካልክ በቃ ንፁሀን እንዲገደሉ አድርግ ወይም ማንነትህን ሰውረህ ንፁሀንን ግደል! ይህ የትግሉ መንገድ ነው! ድሉን ለማግኜት ማንኛውንም ነገር መፈፀም ግድ ይልሃል! ንፁሀን በግፍ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉብኝ ብለህ ካሰራጨህ እና ተቀዋሚዎችህ ያንን ካልፈፀሙት ይህ ነገር እንዲፈፀም የራስክን ድርሻ ተወጣ ! ንፁሀን በሚገኙበት ቦታ ውጊያ ክፈት! ንፁሀን አልወጣ ካሉህ ውጡ እና ተዋጉ በላቸው! እምቢ ካሉህ ማንነትህን ሰውረህ የጠላትን ገፅታ ተላብሰህ ጥቃት አድርስባቸው! ከዛ ሚዲያ ለይ ውጣና ድርጊቱን በእጅጉ አውግዝ! ማውገዝ ብቻም ሳይሆን አፀፋ እወስዳለሁ ብለህ ተናገር! ዋሽ እየዋሸህ ፅና! የዋሸህውን ውሸት ሌላው ባያምነው አንተው እመነው እና በዛ ተመስርተህ አፀፋ መልስ ስጥ! ነገሩ ካቅም በላይ ሲሆንበት ሁሉም ይምታታበትና ያንተ ውሸት ከእነርሱ እውነት በላይ ተሰሚነት ያገኛል! " የሚል ፍልስፍና አላቸው።

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: የሰሞኑ የውሸት ዜናዎች Fake ስዕሎችና ቪዲዮዎች!!!!

Post by Ejersa » 25 Jun 2021, 07:53

ይህንጉዳይ እንዲሁ ማለፍን መርጬ ነበር፣ ሆኖም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በአንዳንድ ሰዎች የተዛቡ መረጃዎች እየተሰራጩ ስለሆነ እውነታውን በአጭሩ መግለጽ እንዳለብኝ ተሰምቶኛል። ከሶስት ቀን በፊት በራያ ባላ በኩል ለማጥቃት ሞክሮ የነበረው የትህነግ ትርፍራፊ ቡድን በአማራ ልዩ ሀይልና በአካባቢው ሚሊሻ ዋጋውን አግኝቶ የበርካቶችን ህይወት አጥቶ ጭምር ወደ መጣበት አቅጣጫ ተመልሷል።

በትላንትናው ዕለት ደግሞ በሌላኛው የራያ ግንባር ወፍላ ወረዳ በኩል ሰፊ ማጥቃት በመፈጸም ኮረምን በመቆጣጠር ጭምር ለመላው ዓለም የድል ዜና ለማሰማት ጓጉቶ የነበረው ትህነግ በጀግኖቹና አይበገሬዎቹ የአማራ ልዩ ሀይል አባላትና በአካባቢው ህዝብ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ሌላ ደማቅ የድል ታሪክ አስመዝግበዋል።በዚህም በርካታ የትህነግ ታጣቂዎች ተገድለው በርካቶች ደግሞ ተማርከዋል።

እውነታው ይኸ ሆኖ እያለ ድሉን በቦታው ላልነበረው መከላከያ ሰራዊት ለመስጠት የሚጣደፉ ሰዎችን እየተመለክትን ነው። እንደ አጋጣሚ ሆኖ የመከላከያ ሰራዊት በራያ ባላም ሆነ በወፍላ ወረዳዎች አካባቢ የለም፣ በመሆኑም አካባቢዎቹን በብቸኝነት እየጠበቁ የሚገኙት የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ናቸው። ይህን እውነት በቅርቡ በቦታው ተገኝቼም ጭምር ያረጋገጥሁት ሀቅ ነው።

በእርግጥ የመከላከያ ሀይላችን በትግራይ ክልል ውስጥ በየዋሻውና በየጥሻው የሚሹለከለከውን ጁንታና ጀሌውን እያሳደደ በመምታትና በመማረክ ላይ ስለሆነ ገድሉ በስርአቱ ሊዘገብ ይገባል። ሆኖም የቄሳርን ለቄሳር መሆን ስላለበት ነው ይህን እውነት ማሳወቅ የፈለግሁት። ይህም ሆኖ ሁለቱም ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያን የሚጠብቁ ስለሆኑ ተደጋግፈው ይሰራሉና ድሉ የሁለቱም ነው ብለን እናምናለን።
Sisay Mengiste

Post Reply