አማራ የጋፋት ብረታ ብረት ቴክኖሎጂ ለማዘመን መነሳታቸው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው።
በታሪክ እንደ ሚታወቀው አጼ ቴዎድሮስ ጋፋት የሚባሉ አፈር አቅልጠው ብረት መፍጠር የሚችሉ ጠቢባን በጎጃም ደጋ ዳሞት አሉ ሲባል ሰምተው የተወሰኑ ነገደ ጋፋቶችን ዛሬ ያሉበት ጎንደር አስፍረው ዝነኛውን የቴዎድሮስ ካስት አይረን (የአር ብረት) መድፍ እንዲሰሩ አደረጉ ። ስለዚህ ዛሬ ጎንደር ያሉት ነገደ ጋፋቶች የመጡት ከጎጃም ደጋ ዳሞት (የጋፋት ዝርያዎች ያሉበት) እንደ ሆነ ይታወቅ።
ስለ ጋፋት ይህን ለማለት ያነሳሳኝ ጉዳይ እኔ በዚህ ፎረም ላይ ብዙ ግዜ ብዬዋለሁ ። ነገደ ጋፋት አገሩ የዛሬ አዲስ አለም ፣ ግንደ በረት ነበር ። በኢትዮጵያ ካሉት ሰባት የሴም ዘሮች አንዱ ነበሩ ። ከዠማ ወንዝ ደቡብ፣ ከስሜን ጉራጌ ሰሜን እስከ አባይ ድረስ በከብት አርቢነት እና በብዙ የእጅ ጠቢብነት የታወቁ ነበሩ ።
አባይ ተሻግረው በጎጃም ተራሮች ተከላካይነት የሰፈሩትና የተሸሸጉት ከኦሮሞ ወረራና እልቂት ለመዳን ነበር ። የነሱ አገር የዛሬ አምቦ፣ ሆለታ፣ አዲስ አለም፣ ግንደ በረት ማለትም (ምራብ ሸዋ የጋፋት አገር) ነው/ ነበር።
በዚያን ዘመን ምድረ ጋፋት እንደ ገብጣን ይባል ነበር። የጋፋቶች ሌላ ስም ወምበርማ ይባል ነበር።
ቋንቋቸው በአምቦ አካባቢ ያልሞቱ ተናጋሪዎች ተገኝተው በትንሹም ቢሆን ተመዝግቧል። ያጠናው ሊንጉዊስት ሀርትዝ ይባላል ። መጽሃፍ ቅዱስም በቋንቁቸው አለ። በቋንቋ ሊቃውንቶች ጥናት መሰረት ልሳለ ጋፋት ከሰሜን ጉራጌ ክስታኔኛ ቋንቋ ጋር እህታማና ባንድ ወቅት ተናባቢ እንደ ነበሩ ደምድመዋል ።
ማለትም ጋፋቶችና ጉራጌዎች ከ16ኛው ኦሮሞ ወረራ በፊት ድምበርተኛ ወንድማማች ነገዶች ነበሩ ። ጋፋት አንዱ የመሃል ኢትዮጵያ የሴም ዘር ነበር ። ዛሬ ቋንቋውና ባህሉ ቢጠፋም ጂኑ በጎጃሞች ውስጥ ደጋ ዳሞት ጎጃም አለ። አጼ ቴዎድሮስም መድፍ እንዲሰሩለት ወደ ጎንደር ያመጣቸው ይህው ዛሬ በስማቸው፣ በጥበባቸው አማራ ሊዘክር፣ ሊያነሳቸው ሆነ !!
ለምሳሌ ወንጪ ሃይቅና በውስጡ ያለው ደሴት ለመጨርሻ ግዜ የደርግ መንግስት ሁለት ልሳነ ጋፋት ተናጋሪ አሮጊቶች ያገኘበት ቦታ ነው። ሆለታ ወዘተ ሚሉት ስሞች የጋፋት ቃላት ናቸው ። እንደ ገብጣን ማለት ዛሬ በጉራጌ ጌኧንዳ (ቤተንዳ) የምንለው ነው ። እንደ ገብጣን ማለት ቤተ ግብጣን (ቤተ ጋፋታን) ማለት ነበር። ለምሳሌ ግንደ በረት ማለት ጌኧንዳ በራት (ቤተ ብርሃን) ማለት ነው ። በራት ብርሃን ማለት ነው፣ በጋፋትም በክስታኔም !! ምሳሌ ለመጥቀስ ነው !!
ግዜ ለኩልክሙ! ግዜ ለኩልሙ እንዲል !!! ኬር !!!!
ደስታዬን ለመግለጽ ነው ! በዚህ አጋጣሚ የጉራጌ ብረት አቅላጮችም ዬቦ ለናንተ ጠቢባን እላለሁ !!!
ሆረስ አይነ ብርሃን






