Horus wrote: ↑15 Jun 2020, 00:11
አቢይና አባ ዱላ ደቡብን አፍርሰው ከአባይ በታች ያለውን ኢትዮጵያ በኦሮሙማ ሄጂሞኒ ስር ለማድረግ እየተጣደፉ ቢሆንም ይህ አላማ የአዲስ ቀውስ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻው አይሆንም ። ፖሊቲካ ልክ እንደ ካራምቦላ ጨዋታ ነው ። አንዱ ጠጠር ሲመታ የቀሩት ሁሉም ይነቃነቃሉ ። የደቡብ መፍረስ የጎሳ ፌዴሬሽኑን ሌላውም ሌላውንም ማፍረሱ አይቀሬ ነው ። ባለ ግዜዎች በወረቀት ላይ እንደ ሚመኙት ሳይሆን ያገሪቱን የፖለቲካ ኢኮኖሚና ሶሺያ ሚዛን ሁሉ ባዲስ መክል ይታመሳል ።
ኢትዮጵያም ኦሮሞም የኢትዮጵያ ጎሳዎች ሁሉ ሰላም የሚያገኙት የዘር ፌዴሬሽን ፈርሶ እያንዳንዱ ጎሳ ራስ ገዝ ሲሆን ብቻ ነው ፤ በቃ !!
አሁን ያለው የጎሳ ፌዴሬሽን(ፌዜሬሽን) እና የዎያኔ ህገ መንግስት እስከ ሚሻሻል እስከ ሚለወጥ ደቡብን መንካት ጠብ ያለሽ በዳቦ ነው !! የጎሳ ፌዴሬሽን ካለ እንዳንዳንዱ የደቡብ ጎሳ ክልል የመሆን መብቱ ይከበር !!
በአዲስ እየተደራጁ ያሉ ክልሎች ከክልሉ ዋና ዋና ቋንቋዎች 2 ወይም 3 መርጠው ለሥራ መጠቀም ይገባቸዋል፡፡ ጉራጌ ክልልነት የማይሰጠው ከአማርኛ ሌላ የራሱንም ቋንቋ ስለማይቀበል ነው፡፡
ሲዳማ በግልጽ የራሱን ቋንቋ የክልሉ የሥራ ቋንቋ ያደርጋል፡፡
ወላይታ ክልል ይሆናል፤ በግልጽ የራሱን ቋንቋ የክልሉ የሥራ ቋንቋ ያደርጋል፡፡
ጋሞ፣ ጎፋ ና ሌሎችም በግልጽ ከራሳቸው ቋንቋዎች መርጠው የክልሉ የሥራ ቋንቋ ያደርጋሉ፡፡
ጋሞ፣ ጎፋ ና ሌሎችም በግልጽ ከራሳቸው ቋንቋዎች መርጠው የክልሉ የሥራ ቋንቋ ያደርጋሉ፡፡
ከፋ፣ ሸክቾ ና ሌሎችም በግልጽ ከራሳቸው ቋንቋዎች መርጠው የክልሉ የሥራ ቋንቋ ያደርጋሉ፡፡
ከምባታ፣አላባ፣ ጉራጌ ና ሌሎችም በግልጽ ከራሳቸው ቋንቋዎች መርጠው የክልሉ የሥራ ቋንቋ ቢያደርጉ ይመረጣል፡፡
ጌድዎ ዞን ከኦሮሚኛ ጋር በጣም የሚቀራረብ ስለሆነ በሂደት ከኦሮሚያ ጋር ሊጠቃለል ይችላል፡፡
በአዲስ የሚደራጁ ክልሎች ማወቅ ያለባቸው ግን በምንም ዓይነት መንገድ በክልሉ አባል ብሔር/ብሔረሰቦች የአፍ መፍቻ ላልሆነ ቋንቋ ዕድል መስጠት የለባቸውም፡፡ የደቡብ ክልል በተባለው ግዑዝ ክልል ነፍጠኛ ተንሰራፍቶ የሀገረ-ሰቡን ዜጋ የሥራና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችና መብቶች ያሳጣው አማርኛ በክልሉ የሥራ ቋንቋ በመሆኑ ነበር፡፡