Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40166
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Horus » 21 Apr 2020, 01:37

Dawi wrote:
21 Apr 2020, 00:51
Horus wrote:
20 Apr 2020, 22:58
Horus - Thanks for sharing.

Very interesting presentation; the last man that took the podium in the video pointed out of the best way to raise your kids; it reminded me of an interview I saw of the famous Neil deGrasse Tyson on Impact Theory a while ago.

This is Exactly How You Should NOT Raise Your Kids! | Neil deGrasse Tyson on Impact Theory


Dawi,

Thank you so much for posting Neil's program. Neil is amazing. If you remeber, back then he proposed that he could build a machine for time travel (travel to the past) and after a lot effort it was proven impossible. Remeber, according to the arrow of time, we can never go back in time. But he wanted to see his father as a young boy and built a machine to bring back the boyhood of his fatherhood. In the world of astrophysics, he could not do it but his mathematical work helped all kinds of other discoveries. I used to follow Neil real good.
He is amazing and a true creative genius.

Coming to our own humble world, Ethiopia, this is a very exciting time. It is like a new sun rising !!! Ezedin is just one curious young man but he is challenging his peers. I just love it. !!!

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Ethoash » 21 Apr 2020, 07:55

አንተ ቡዳ አቶ ፀሐይ። ፈጠራ የሚጀምረው እንደዚህ እኮ ነው። ልጁ እርዳታ ቢያገኝ ቻይና ሄዶ ፈጠራውን መተግበር ይችላል። ቻይና ውስጥ አንት ራስ ህ ቴሌፎን ዲዛይን ብታረግ እነሱ ዲዛይንህን ወደ ፕሮዳክት ይቀይሩልሀል።

የመጀመሪያው ኮምፒተር እኮ አንድ እና አንድ ለመደመር ሳምንት ልፈጅበት ይችላል። በዚህ ላይ ቤት የሚያክል ኮምፒተር ነበር በዚያን ግዜ አረ እኛ በእጃችን ብንደምር እንፈጥናለን በለው የኮፒተርን ፋጠራ አላጥላሉትም። በዚህም ያለንበት ደረጃ ደርስናል።

በሐይሌ ስላሴ ግዜ ሮኬት ስራን ያሉትን ተማሪዎች ብንከባከባቸው ኖሮ የት በደረስን ነበር። ዛሬ እኮ ፹ ዓመት አለፈው ንጉስ አገዛዝ ካለፈ በዚህን ግዜ ሁሉ ትልቅ ደረጃ እንደርስ ነበር። እኛ ልንስራ የማንችለውን ነገር ባናጥላላ ትልቅ ነገር ነው። ልጁ ከ፴ በላይ የፈጠራ ውጤት አለው እነሱን በሙሉ ቢያዳብር የት በደረስን ነበር ።

የአገር ስራፈት ይዘን ችግር አንጥራ ።። ልጁ ፰መቶ መተንፈሻ እስራለሁ ያለው እኮ ነገሮች ቢሟሉለት ነው። በዚህ ላይ በጠቅላላ አንተ የዘረዘርካቸው የነጮች ድርጅቶች እኮ ልክ እንደልጁ ነው የተነሱት ። አታካብድ ። በዚህ ላይ ልጁ ያየውን እነዚህ ትልልቅ ድርጅቶች ላያዩ ይችላሉ ስለሚኮፈሱ። ለዚህ ብዙ ማስረጃ አለ ትልልቅ ድርጅቶች ሳያውቁት እንደተበለቱ። ለምሳለ የመኪናን ፋብሪካ ተስላ የኤሌትሪክ ካፓኒ በአፍጥሙ አቅሞታል የትርሊዬን ዶላርን የስትላይትን ድርጅት ናሳንም በአፍጢሙ ደፍቶታል ። በጣም ብዙ ምሳሌዎች አሉ ስለዚህ አትሟዘዝ ። ምንም አይነት ነገትቪቲ አትጭምር ። ይቻላል የሚል ስሜት ብቻ መጫሩ ትልቅ ነገር ነው።

እንደፈረድብህ እኔ እኮ ማለት የፈለግሁት እያልክ የሞት ነጭ ገገማ ጥቅስ አትጠቅስልን። እንዳንተ አይነቱን ነበር ስብስቦ ገደል መክተት ። ኮሮላ ቢይዝ ህ ማስተንፈሻ መክልከል የዛን ግዜ ዋጋህን ታገኝ ነበር ። ምን አይነት ደደብ ነው ኢትይዽያ የምትቀልበው እደሜ ለመሆኑ ስንት ነው። ከዚህ ህፃን ጋራ የምትፎካከረው

ደግሞ ኮተት ህን ይዘህ ጥርግ በል ጠንቋይና መትታም ቃልቻ የሚሉትን ከዚህ የፈጥራ ባለቤት ጋራ አታያይዘው። ልጁ ሌላው ቢቀር ማስቡ ብቻ ሊበረታታ ይገባል።

በአንተ ቤት እኮ አበበ በቂላ ነጮችን ሮጭ አሽንፋለሁ ቢልህ ። እነዚህ ነጮች እኮ ብር አላቸው በቴክኖለጂ ዳብረዋል የሚበሉት የሚጠጡት ብቻ ፋጣን ያረጋቸዋል አንተ እንጀራ ብቻ በልተህ በቀን አንድ ግዜ እንዴ ነው ነጮችን የምትዳፈረው ። ማንም ጥቁር ነጮችን አሽንፎ አያውቅምና አትዳፈር መሳቂያ ታረገናለህ። ደግሞ በባዶ እግር ነው ልሩጥ የምትለው ወቼ ጉድ አንተ በአይሮፕላን ተሳፈረህ የነጮችን አገር ልትጎበኝ እንጂ ሮጠህ ልታሽንፍ አይደለም የአገሪቱን ገንዘህ በአንተ ሽርሽር ማቦከን የለብንምና አትሞዘዝ በለህ የሩጫ በህላችንን ታኮላሽ ነበር ።

እንደፈረደብን እኔ ማለት የፈለጉሁት ይህ ነው በለህ የነጮችንን ምሳሌ ለጥፋ ገገማ ። እኔ ሆረርን ምንም አልደግፈውም ግን እንዲህ አይነቱን ለሀገር የሚጠቅም ነገር ሲያመጣ እደግፈዋለሁ በርታ እለዋለሁ

Horus
Senior Member+
Posts: 40166
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Horus » 21 Apr 2020, 15:11

Ethoash,

እኔም ነገሮችን በትክክል ስታይ እስማማሃለሁ ። ይህ ጸሃይ ካልከው ሰው አፍ ላለመካፈት በስድብ ነው የዘጋሁት ። ያልከው ሁሉ ትክክል ነው ። ይህ ወጣት 17 ፓተንቶች አስመስግቧል፣ ማለትም አዲስ ነገር ወይም ያሻሻለው ነገር ትብሎለት ማለት ነው። ያም ማለት ልጁ የማንም የኔ ብጤ ተነስቶ የሚያንኳሠው ፌክ ነገር አይደለም ።

ባሁን ሰአት የሶላር ባጃጅ ሰርቶ በዚያ ነው ራሱ ሚጓጓዘው ። አንዱ ቪዲዮ ላይ ከሰማሃው ባለ 4 ጎማ መኪና ሶላር፣ ጋስ፣ ወይም ኤሌክትሪክ የማይጠቀም መኪና ሰርቼአለሁ ብሏል ። የፕሮዳችት ሚስጥሩን ሊያወጣ አልፈለገም ። በእኔ ግምት በነፋስ ሃይል የሚነዳ ሊሆን ይችላል ።

ለማለት የፈልግሁት ልጁ የእወነት ጂኒየስ ነው ። ገና መጀመሩኮ ነው ።

አንተ አት ስማማም እንጂ እኔ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የቴክ ማእከል ይሆናል ስል ነበር ። ይህው ነው የቴክ መፈልፈያ (ኢኩቤሽን) ማለት ።

sun
Member+
Posts: 9582
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by sun » 21 Apr 2020, 18:43

Abdelaziz wrote:
21 Apr 2020, 00:50
Horus wrote:
20 Apr 2020, 15:00
The entire system Meshrefet is trying to create is based on the creation of such absurd deceptions.
WA'AA...!

Why do you politicize the issue in way that fits your bitter parochial petty political interests when the issue concerns only ato horus who brought it online. You are no different from this bab**n calling himself horus trying to use the kid for his own financial and political interests. Ato horus is trying to insult our intelligence by claiming that the kid will soon produce 800 ventilators per day. Mind boggling claim in 21st century. 8)


Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Ethoash » 23 Apr 2020, 07:35

ወጣት ፈጣሪ ዲዛይን ካሚልን አይቶ የማይደስት አቃቂር የሚያውጣ ወይ ኤርትራዊ መሆን አለበት ወይ ዲቃላ መሆን አለበት ወይ ደግሞ አቶ ህፃን (እርሱን ፀሐይ ብሌ የሚጠራው ) መሆን አለበት ። ቪዲዬወን አልጨረስኩትም እየሰስትኩት ነው እንደ እርጎ የምጋተው ።

ለሳንባ ማስተንፈሻው ደግሞ ቪድዬው ላይ አለ። ባይስራም እንኳን በዚህ አጭር ግዜ ለዚህ ለመስለ ናሙና መብቃቱ በጣም የሚያስመርቀው ልጅ ሆኖዋል። እንዳንዴ ያ እብድ ህፃን(ህፃን ማለትም ያሳፍረኛል እቧጭ ጭቃ ራስ) እንዴት ተሳነው ቪዲዬውን ሳንባው ሲስራ ማየት ። አዋ ፈረንጆች ከመጠን በላይ አውሳስበው ማምጣታቸው ዋጋ ለመጭመርና ማንም አስመስሎ እንዳይስራባቸው ነው እንጂ ብዙ ነገሮች ስራቸው በጣም ቀላልና ያልተውሳስቡ ናቸው ። በዚህ ላይ የኮምፒተር ፈጣሪን ልክ ኮምፒተሩን እንደፈጠረ ፭ጂ ካልደረግህ። በለን ብንደርቅ ምንም ነገር አይፈጠርም ። ዛሬ ቲቪ አራት መሀዘን ሳጥን እንደሚመስል ተረስቶዋል ። ሽንቃጣው ቲቪ ከመጣ በኋላ አራት መሀዘን ሳጥን ቲቪ መመርትም አቁሞዋል ግን ገና ቲቪ ሲጀመር ለምን ሸንቃጣ አልሆነም ብንል ገገማ ነን ማለት ነው ልክ እንደ አቶ ልጅ ። እኔ ከድሮም አውቄው አቶ ፀሐይ ነኝ ሲለን አቶ ልጅ ብዬ ስም ያወጣሁለት ነገረ ስራውን አይቼ ነው። እሲቲ ያንን ረዝም መልስ ስጥቼው ለምን ዘጋኝ መልስ ቢኖረው ። በፍፁም እቺ ገፅ ላይ አይደርሳትም ። ምድረ ገገማ ሽማግሌ ሁሉ። አቶ ልጅ እደሜውን የጨረስው ቋንቋና ታሪክ ሲያጠና ነው ለዛውም የነጮቹን ስለዚህ ይህ ብሎ የሚያሳየው ውጤት ስሌለለ ያለው አማራጭ እንብጦች ሲበቅሉ መጨፍጨፍ ነው። አቶ ልጅን ያልገባው ነገር ቢኖር በዚህ ልጅ ላይ ኢንቨስት ቢያረግ የትና የት ታሪክ በስራ ነበር ሁሉን ፈጠራው ከመቶ ሽህ ስራ ፈቶችን ስራ ማስገኘት የሚችል ነው።

አቶ ሆረር ። በዙ ግዜ ይህንን ልጅ ፕሮሞት ስታረገው ባይም ። ዝም ብዬ ነበር ጉራጌ ስለሆነ መስሎኝ ። እንዳልኩህ ጥሩ ነገር ካየሆ የአንተን ሞቲቪ ብቃወምም የመጣህውን ጥሩ ነገር ከቆሻሻው ውሀው ጋራ አውጥቼ አልደፋምና ዝም እላለሁኝ ። ግን አቶ ልጅ ምን እንደሚልህ ትሰማለህ ገንዘብ በልጁ ላይ ልትሰራበት ፈልገህ ነው ይልሀል ። ታድያ ምን ነወር አለበት ። ይህንን ያህል ፕሮሞት ካረግህው ካስተዋወቅኸው የስራህን ፍሬ ብታገኝ ምኑ ነው ጥፋቱ።

ልጁን ዲዛይን ካሚልን የማደንቀው በመፍጠሩ ብቻ አይደለም ሌሎቹን ሰዎች አስተባብሮ ፈጠራውን ተግባር ላይ ለማረግ በመጣሩ ነው። ደግሞም ፈጠራ ብቻ ዋጋ እንደሌለው ተረድቶ ። ፓተንቱን እስከውጭ አገር ድረስ ሄዶ ማስመዝገቡ የልጁን ብስለትና አራዳነት ያሳየል ።

ከገረመኝ ፈጠራው እንዴት በአጭር ግዜ ያለ እጅ ንኪኪ የእጅ መታጠቢያ መስራቱ ነው። በጣም አጃይብ የሚያስብል ስራ ነው። ፈሳሽ ሳሙና መጠቀሙ ደግሞ ከንኪኪ ነፃ ያረገዋል ። እንዱ በታጠበበት ሳሙና ሌላው ሳይታጠብ በንፅህና ሁሉም መታጠብ ይችላል። እንግዲህ እዚህ ላይ ፈሳሻ ሳሙናን አገር ቤት የሚስሩ የፈጠራ ባሌቤቶች አሉ እነሱን እፋልጎ ፈሳሽ ሳሙናውን ከነሱ መግዛት ከተቻለ ሙሉ በሙሉ አገራዊ የእጅ መታጠቢያ ማረግ ይቻላል። ሌላው የገረመኝ ደግሞ ያለኤሌትሪክ መስራቱ በእግር መረገጡ ነው። ብዙ የሚሻል ነገሮች ሊኖሩት ይችላል ያ ሁሉ ቀስ በቀስ ሊመጣ ይችላል። ግን ሁቴሎች ከዚህ ፈጠራ በኋላ በእጂ የሚዘጋ ቧንቧ መጠቀም ይቆማሉ ብዬ አምናለሁ።

ልጅ ዲዛይን ከሚል በነኔ ሚና በሚለው ቲቪ ወይም የክልሉ ቲቪ የመስለኛል ከፍተኛ ድል ነው። ለምን ቢባል ታዳሚዎቹን ብቻ ማየት ይቻላል ብርቅቄ የጉራጌ ሴቶች ማየቴ በጣም አስደስቶኛል ። እንደዚህ አይነቱ የፈጠራ ሰዎች የክልላቸው ቲቪ ጎልጉሎ ነው የሚያወጣቸውና ታላቅ ደስታ ተስምቶኛል አንዱ ጉራጌ ውይም ወንድም ብሎ የጠራው ፩ሺህ ዶላር የማይሞላ ገንዘብ ልኮለት የኤሌትሪክ የሚስራውን ባለ ሶስት እግር ቢስክሌት ለመጨረስ መብቃቱ ታላቅ ኩራት ነው። ለምን ቢባል ምንግዜ እዛ ተውልደው የደጉ ልጆች እርስነት ስሜት ስለሚስማቸው ከልባቸው ያግዙታል ይህ ደግሞ ታላቅ ቁምነገር ነው። አገሩን ከማወጥ ፖለቲካ ፓርቲ በመመስረት እንደዚህ ያሉትን ልጆች በመደገፍ ክልላቸውን የሚያሳድጉትን ግለስቦች ክፍ ከፍ ማረግና እውቅና መስጠት እንደ ጁሐር አይነቶችን ይቀንስልን ነበር።

ከዚህ ኤሌትሪክ ባለሶስት እግር ሳልወጣ ። የበጃጅ ዋጋ ስንት እንደሆነ ባላውቅም ከመቶ እምሳ ሺህ እስከ ሶስት መቶ ሺህ የሚፈጅ የመስለኛል ከዚይ በኋላ የበጃጁ ባለቤት በቀን መቶ ብር ቢያወጣ ለጋዝ በአመት ፫፭ ሺህ ብር ብቻ ለጋዝ የወጣል ታድያ ከከሚልን የኤሌትሪክ ሞተር ቢያስመጣ እና ፪፭ሺህ ብር ቢከፍል የጋዝ ወጭው አይቀንስም እንዴ።

ሌላው ደግሞ እኔ አስተያየት የምስጠው አንድን በጋዝ የምትሄድ በጃጅን ወድ ኤሌትሪክ በጃጅ ኮንቨርት ማረጉ በታም የተሻለ የመስለኛል ። ለምን ቢባል እነዚህ የበጃጅ ባለቤቶች ምን ያህል ነዳጅ ወድ እንደሆነ ስለሚረዱ ይህ ቴክኖለጂ ግልበጣ ከመጣላቸው በሙሉ ወድ ኤሌትሪክ በጃጅነት የቀየራሉ ብዬ አስባለሁ ። በጃጁም ሀይል እንዲኖረው የኤትሪክ ሞትሩን ጉልበት በጥፍ ጨምረን የሶላሩን ፓወር ደግሞ በእጥፍ አሳድገን ከ፹ ዋት ወድ ፩፷ ዋት ብንሳደገው የበጃጅ ተሳፋሪዎችም በደስታ ተሳፈረው በጃጁዋም ያለምንም ማቃሰት ተራራውን ቁልቁለቱን በመወረድ ግልጋሎት ተስጣለች።

እንግዲህ አስቡን ይህ ስራ በተግባር ላይ ቢውል ኢትዬዽያ ፫መቶ ሚሊዬን ነዳጃ የምታመጣውን አስቀረች ማለት ነው። ግን ይህ ሊሆን አይችልም የነዳጅ ሚኒስተር ግቦ ስለሚበላ ከነዳጅ ነጋዴዎች ጋር በተሀምርም ነዳጁን አያስቆምም። ለዚህም ዘዴው ድምፅ ሳይስሙ ከነዳጅ በጃጅ ወድ ኤሌትሪክ በጃጅ ግልበጣውን ተደብቆ ማረጉ ይምረጣል ።

እኔ ብዙ ኢትዬዽያኖች የኤሌትሪክ በጃጅ ስራን ስሊ ስምቻለሁ ። መኪንናም ወድ ኤሌትሪክ መኪና መቀየሩን ዘመቻ እራሱ ለመቶ ሺህ ውጣቶች የስራ እድል ይፈጥራል ። ታድያ ምን ያዛን ይህንን ከማረግ ።። ቀላሉ መልስ ገንዘብ ነው የያዘን ወጣት ዲዛይን ከሚል ፫ ሚሊዬን ብር እፈልጋለሁ ብሎዋል ታድያ የጉራጌ ዞን ሰዎች ፫ሺህ ዎቹ ብቻ አንድ ሺህ ብር እንቨስት ቢያረጉ እኮ ይህ ክምፓኒ ተመስረት ማለት ነው። እነዚህ እንቨስተሮች በአጭር ግዜ ገንዘባቸውን በመቶ እጅ ይሳድጉት ነበር ። እንዴ ከተጀመረ ማለቅያ የለው። አንዴ ሰዎች ውጤቱን ካዩ በመላ ኢትዬዽያን የኤሌትሪክ በጃጅን በመላክ ጉራጌ በእጥፍ በድርብ ታድግ ነበር ወድ ከተማማ መስደድ ይቀር ነበር።

ሆረር ስለእራሱዋን ችላ ለምትሄደው መኪና እኔም ግምት አለኝ። ታስታውስ እንደሆነ በልጅነታችን የባህርዛፍ ቀጠል መሀሉ ላይ ብስተን ስንሮጥ ቅጠሉዋ ትሸከረከር ነበር። ታድያ መኪናው ሲሄድ አንት እንዳልከው በንፋስ የሚሽከረከር ፋን ይኖረል ይህ ፋን ደግሞ ኤሌትሪክ ያመነጫል ባትሪውንም ይሞላ መኪናው በሄደ ቁጥር ባትሪው ይሞላል ማለት ነው። ልክ የባትሪ መሙያ ጫማ እንደስራው በሄደ ቁጥር ባትር ሀይል እንደሚያመነጭ መኪናው በሄድ ቁጥር ሀይል ያመነጫል ።

አሁንም ቢሆን አዳዲስ መኪናዎች ፍሬን በያዙ ቁጥር ኤሌትሪክ ያመነጫሉ በዚህም ጋዝ ቆጣቢ ይሆናል ። አይዲያው አለ ግን እኔ በደፈናው ይህ ነገር ይስራል ብዬ ለማመን ያቅተኛል በጣም ከኔ ጭቅላት በላይ ነው ። እስማየው በተግባር ተትርግሞ እስክማየው በጉጉት እጠብቃለሁ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ። አንድ ሰው የዛሬ ፴ አመት በስልክ በቪድዬ እየተያየን እናወራልን ብለን አላምንም ነበር ታዲያ ይህ ምን አላት ። ያ ገገማው አቶ ፀሐይ እንደለመደው ይህ ቢሆን ኖሮ ለምን ትላልቆቹ የመኪና ካምፓኒ አይስሩትም ነበር ይለናል። ታድያ ለዚህ መልሱ ለምን ኤሌትሪክ መኪና አልስሩልንም እንደዚያ ከሆነ ። የመኪና ካምፓኒዎች በጋዝ የሚነዳ መኪና ብዙ ውጪ ስላለው አትራፊ ነው ግን የኤትሪክ መኪና ከስሩ አንዴ ከሽጥት በኋላ ምንም የሚያገኙት ጥቅም ስሌለሌ ለምን በለው ነው ጥቅማቸውን የሚያጡት ። አሁንም የለጋዝ ያለ ኤሌትሪክ መኪና መስራት አቅቶቸው አይደለም ግን ነዳጅ ማለት እኮ ከመኪናዋ ዋጋ በላይ የሚያውጣ ገንዘብ ሊቀርባቸው ይችላል ። እስቲ አስቡት በየሳምንቱ ፵ ብር ለጋዝ ካወጣቹ በወር ወደ መቶ ስልሳ ይመጣል በትንሽ ግዜ ውስጥ ከመኪናዋ በላይ ዋጋ ጋዝ አውጥቶ ቁጭ ነው የሚለው። ይህንን ሁሉ ነው አስቀራለሁ የሚለን ይህ ብላቴና።

ታድያ ለዚህ ልጅ ጎ ፈንድሚ እንደማቋቋም ስድቡን ምን አመጣው ። ለምንስ ብዙ ሰው በዚህ ልጅ ፈጥራ አልተደነቀም።

እንዳልኩት ወሬያችንን ትተን እንቨስትመት ትረስት አቋቅመን ይህንን ልጅ ብቻ አይደለም አንድ ሺህ በላይ የፈጠራ ባሌበቶች አሉ ሁሉንም መርዳት ይቻላል እኛ ገንዘብ በገንዘብ እንሆናለን ። የፖለቲካ ድርጅቶችንን ከመደገፍ እንዲህ አይነቱን ገድል ብንደግፍ ድካማችን ፍሬ አፍርቶ ለማየት ምንም ግዜ አይፈጅብንም ።

አንድ ድርጅት በመቶ ሺህ ብር የዛሬ ፳ ዓመት የተቋቋመ ዛሬ በቢሊዬን ነው የሚያወሩት ። ጥያቄዬ እዚህ ውጭ አገር የምንኖር በዚህ ፳ አመት ምን ስራን የከስረ ፓሪቲ ከመደገፍ በስተቀር። ያ ሁሉ ገንዘብ ለዚህ አይነቱ እንቪስትመት ቢውል የት እንደርስ ነበር። እሺ አገራችንን ነፃ ለማውጣት ልትሉ ትችላላቹ ግን አሁንም ለምን የፖለቲካ ድርጅት እንደአሽን ታፈላላቹሁ። ሌላው ቢቀር እንቪስትመትም ጎን ለጎን ቢራመድ እላለሁ። ደህና ስንብቱ

ማረምያ

በወረዳው መንገድ ትራንስፖርት በተቋቋመው የበጃጅ ማህበር አማካኝነት በቅናሽ ዋጋ የነዳጅ አቅርቦት እየቀረበላቸው እንደሚገኝ ተጠቁሟል ። በአሁኑ ስዓት ፪፭ ሊትር ቤንዚል በ፮፪፭ ብር የባጃጅ ማህበሩ እያቀረበላቸው መሆኑን ከትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ቡድን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ይህም በሊትር ፪፭ ዋጋ እየገዙ ይገኛሉ።

ይህ ማለት በቀን እስከ ፮፶ ብር የጠፋሉ ማለት ነው ለነዳጅ ይህን እንግዲህ በአመት አስቡት ፪፻ ሺህ በላይ ብር ውሃ በላው ማለት ነው ግን ሁለት መቶ ሺህ ብር ለነዳጅ ከማወጣት በሃያ አምስት ሺህ ብር ወደ ኤሌትሪክ በጃጅን መቀየር አይሻልም ወይ ። ኤሌትሪክ ኢትዬዽያ ውስጥ ይቆራረጣል እንዳንል ሶላር ፓወር አለውና ጥቅሙ የጎላ ነው ባይ ነኝ

Horus
Senior Member+
Posts: 40166
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Horus » 23 Apr 2020, 15:30

Ethoash,

ያልከው ሁሉ ትክክል ነው ። እኔ ይህን ልጅ አንተ ፕሮሞት ያደረከውን ያክል አላደረኩትም፣ ቪዲዮዎቹን ከማስተዋወቅ ያለፈ ማለቴ ነው። ፈጠራና ኤንትርፕሬንወርሺፕ እንደ ምትወድ አቃለሁ ። ግሩም አስተያየት ነው የመለስክለት፣ ለጸሃይ ።

ጸሃይ ለገንዘብ ስትል ነው ልጁን ምታዳንቀው ይለኛል ። እኔ ልጁን ልክ እንዳንተው በቪዲዮ ነው የማውቀው ። ህጻን ሆኖ ሲያወዳድሯቸው የሚያሳይ ቪዲዮ የዛሬ 3 አመት አካባቢ ለጥፌ ነበር ። ሌላ ስለልጁ አንድም ነገር አላቅም ። እኔ ግን ስኬታማ ሰዎች ያስደንቁኛል ፣እናም ዝም ብዬ ተነስቼ ፕሮሞት አደርጋቸዋለሁ ። ይሀው ነው።

ስለፈጠራና ቀረጻ (ዲዛይን) ያልከው ትክክል ነው ። አንዱ ትልቁ የዲዛይን መርህ ቀላል (ሲምፕል) መሆኑ ነው። አንድ ነገር በትክክል የሚከናወነው በቀላል ክህሎት ወይም እስኪል የሚተገበር ሲሆን ነው።

እኔና አንተ ስለኢቬንሽን በዚህ መልክ እንድንወያይ ያረገን ይህ ልጅና የቀሩት ባነሱት ፈጠራ ሳቢያ ነው ። ይህ ነው እንግዲህ ተጽ ዕ ኖ መፍጠር ማለት ።

የልጁ ቁሳዊ ፍልስፍናዎች ቀናቸው ጠብቀው ወደ መፈብረክ የሚወርዱ ይመስለኛል፣ ነጋዴው ክፍል እየነቃ ሲሄድ ማለቴ ነው ።

የወደፊቱን አለም ስናየው የሃይል ምንጮች ወደ ጸሃይ፣ ነፋስ፣ ኤሌክትሪክ እና ኑክሊየር እየዞሩ ስለሆነ ልጁ ደሞ ገ ና በዚህ እድሜው ነገሩን በልቶታል።

እኔ ሌላ ክልል ውስጥ ያሉት ልጆች ምን ላይ እንደሚያቶክሩ አልተከታተልኩም ፣ ግ ን ያገሪቱ የነገ ቢል ጌቶች እነሱ ናቸው ።

የጸሃይ ጸሃይማ ጠልቃለች ፣ እሱን እርሳው !

Horus
Senior Member+
Posts: 40166
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Horus » 23 Apr 2020, 17:22

Ethoash,

ኢዘዲን ካሚል የሰራውን መተንፈሻ የሰየመው ዎራፎ በሚባል የእሳት አየር መንፊያ መሳሪያ ሜታፎርነት ነው ። ዎራፎ የጉራጌ ብረት አቅላጮች (እስሜልተርስ)፣ ጠጋኞች (ዌልደርስ) ብረት ጠራቢና ሽካቾች (ቀጭቃቾች) ከማረሻ እስከ ቢላ፣ ከጦር እስከ ብረት አፈሙዝ፣ ከማንደጃ እስከ ምጣድ ሚያመርቱበት ከፍየል ወይ በግ ቆዳ የሚሰራ ለሺ ዘመናት ሲተላለፍ የመጣ ቴክኖሎጂ ነው ። በጥንታዊ ግብጽና ቻይና ምን እንደ ሚመስል ስ ዕል ቢኖር ጥሩ ነበር።

ልጁ ዎራፎ ኦክሲጂን በመስጠት የእሳቱን ህይወት ያጠነክራል ያለው አገላለጽ እጅግ ወብ ነው ። የቤሎስ ወይም ያውሮፓ ዎራፎ ታሪክ ከስር ተከታተል ።

https://en.wikipedia.org/wiki/Bellows

AND, HERE IS THE CLASSIC POLIO ERA VENTILATOR - THE IRON LUNG WHICH HAS JUST MADE A COME BACK DUE TO COVID19!!

https://en.wikipedia.org/wiki/Iron_lung

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Ethoash » 27 Apr 2020, 00:12

Horus wrote:
23 Apr 2020, 17:22
Ethoash,
ልጁ ዎራፎ ኦክሲጂን በመስጠት የእሳቱን ህይወት ያጠነክራል ያለው አገላለጽ እጅግ ወብ ነው ። የቤሎስ ወይም ያውሮፓ ዎራፎ ታሪክ ከስር ተከታተል ።



Horus
Senior Member+
Posts: 40166
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Horus » 27 Apr 2020, 00:55

Ethoash wrote:
27 Apr 2020, 00:12
Horus wrote:
23 Apr 2020, 17:22
Ethoash,
ልጁ ዎራፎ ኦክሲጂን በመስጠት የእሳቱን ህይወት ያጠነክራል ያለው አገላለጽ እጅግ ወብ ነው ። የቤሎስ ወይም ያውሮፓ ዎራፎ ታሪክ ከስር ተከታተል ።


ትክክል !!!

እስቲ ይህን ያዩ ያገር ቤት ወይም ያዲሳባ የሰራተኛ ሰፈር ልጆች የጉራጌ ዎራፎን ስ ዕል እንደሚለጥፉልን ተስፋ እናርግ !!!

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: የ19 አመቱ ጂኒየስ ኢዘዲን ካሚል በቀን 800 ቬንቲሌተር ፣ ወራፎ፣ መስራት እንደ ሚችል ገለጸ

Post by Ethoash » 28 Apr 2020, 07:02

Horus wrote:
27 Apr 2020, 00:55

እስቲ ይህን ያዩ ያገር ቤት ወይም ያዲሳባ የሰራተኛ ሰፈር ልጆች የጉራጌ ዎራፎን ስ ዕል እንደሚለጥፉልን ተስፋ እናርግ !!!
አንተ ይህ ዎራፎ በጣም አስገርሞሀል። እኔ ደግሞ ለመጀመሪያ ግዜ ይህንን ዎራፎ የስራው ስው ለአቶ ህፃን አማክሮት ቢሆን ኖሮ እንዴት አቶ ህፃን ይመልስለት ነበር ብዬ ስፈላስፍ ይህንን መረጃ አገኘሁ።

አቶ ህፃን መልስ እንደሚከተለው ነው።

ምን አልከኝ በፍየል ስልቻ ብረት አቀልጣለሁ አልከኝ። ስልቻውን ብቻ በእጅ በመጫን አልከኝ ። ምን አይነቱ ደፋር ነህ ። ነጮቹ ያልሞከሩትን አንተ መዳፈርህ በጣም በጣም የሚገርም ነው ። እንደውም ደህና ስልቻ አታበላሽ።


ታዲያ እንደዚህ አይነቱ ስዎች በበዙበት ለምን ድሀ አንሁን። እኔ ሁሌ የምምልበት የቢዝነስ ዘይቤ አለ ። አሜሪካኖችንና ነጭችን አብታም ያረገው። ሼር ውይም እክሲዬን አማልጋሜትድ ተብሎ ይጠራል። አምሳ ሎሚ ለአንድ ስው ሽክሙ ነው ለአምሳ ሰው ጌጡ ነው እንደሚባለው ። የዚህን ልጅ ፈጠራ ተግባራዊ ለማረግ ፍቱን ምድሀኒት አክሲዬን መመስረት ነው።

ታድያማ ይህ እክስዬን ዘዴ ጉራጌ ከጥንቱ ጀምረውት ነበር ን ስሙን አሳምረው እቁብ ፤ እድር በለውታል እነዚህ ሲያሜዎች ጉራጌኛ ከሆኑ ትነግረናለህ። እቅብንናን እድርን ማዘመን ነው ፤ ውይም ይዘታቸውን ጠብቆ በቴክኖለጂ ታግዘው መካበት ያለባቸው ብህሎቻችን ናቸው ። ወደፊት የጉርጌ ባንክ ሲቋቋም እድርናን እቁብን ማካተት አለባቸው ።


እንግዲህ ተመልከት ከንዘብ ፈልገህ ንግድ ለመጀመር ባንክ ቤት ሄደህ ብድር ከምትጠይቅና የባንክ እዳ ከፋይ ከምጦን እቁብህን ጥለህ ሲወጣልህ ተጠቃሚ ብትሆን ፤ የባንክ ወለድ አትከፍልም ነበር ።

በቀደም ለት ሐይሌ ባለሀብት አትበሉኝ ባለ እዳ በሉኝ እያለ ሲሞግት ነበር እውነቱን ነው።

ግን ሐይሌ ወይ የእክሲዬን ዜዴ ወይ የእቁብን ዜዴ ቢጠቀም ለዚህ ሁሉ እዳ ባይጋለጥ ነበር ለማለት ነው። የሐይሌ መወደቅ ወይም መክስር ሐይሌን ብቻ አይደለም የሚጎዳው በስሩ የሚገኙትን ከመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ስራቶኞችንም ጭምር ነው ።

የሀይሌ ብቻ አይደለም የካፒታል ችግር ኤልያስንን አመልጋ ዘርሮ የጣለው የባንክ እዳ ነው። አንደኛ ብድሩን ለመልቀቅ ጉቦ ከመፈለግ ።ሌላው ደግሞ ነገሮችን በማዘይገት ኪሳራ ውስጥ መጣልና ትርፋቸውን ከመስብስብ በቀር ምንም ደንታ ስለምይስጣቸው ብትወድቅ ብትነሳ ምንም እያገባቸውም ንብረት ህን ሸጠው ነው በመቅብርህ ላይ የሚዘባበቱት ይህንን ያህል ትርፍ አገኘን እያሉ ግን ስንት ፋብሪካ እንዳዘጉ አይነግሩህም ። ከዚህ ሁሉ አገር በቅል እቁብ እያለልን ምን ከባንክ ጋራ ምን ግብ ግብ እንገጥማለን

ባንኮች ይጥፉ እያልኩ ሳይሆን ተፎካካሪያቸውን ማግኘት አለባቸው እያልኩ ነው።


በመጀረሻም ይህ ታዳጊ ፈጣሪ ፈጠራው ተግባራዊ እንዲሆን እቁብ መጀመር አለበት ፤

በጃጁን ወደ ኤሌትሪክ የሚቀይር ፋብሪካ በቋቋም ብቻ ጉራጌን በጣም አብታሟ ክልል ያረጋት ነበር ከጋዝና ከውርቅ በላቀ። ያለን ወርቅ እንደመዳብ ቆጥረን ይህንን ልጅ ተስጥዖ በዋዛ በፈዛዛ ብናስቀረው ጌታችንን ማማረር የለብንም ባይ ነኝ ነጋቲ ቡላ።

እንደው ለመሆኑ አቶ ፀሐይ አማርኛ ማንበብ አቅቶት ነው ወይስ ምን ነክቶ ት ነው እንዲህ የጠፋው። በስላ ያርግለት

Post Reply