“ትግማራ” – ‘የአማራና ትግራይ አወዛጋቢ ስፍራዎች’ ሰላማዊ የመፍትሄ አማራጭ ቁልፍ ሃሳብ
Posted: 03 Mar 2026, 05:00
እኛ ኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በሰው ልጆች መካከል ፍቅር እንጂ፡ ጥላቻና ተንኮል እንዲያንሰራፋ ፍላጎታችን አይደለም።
የአማራ ህዝብና የትግራይ ህዝብ ለዘመናት በፍቅር የኖሩና የተጋመዱ ክቡር ወንድማማች ህዝቦች ናቸው። በእልህና በጥላቻ በሚመሩ በአንዳንድ ‘ፖለቲከኞች’ የስህተት ቀመር ምክንያት፡ እነዚህ ወንድማማች ህዝቦች ሳይወዱ በግድ እንዲናቆሩ ብዙ ተንኮል ተሸርቧል። እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ግን በዚህ ችግር መሃል እሳት ማቀጣጠል ሳይሆን፡ እንደ መልካም ጎረቤት መጠን መፍትሄ እናጋራለን።
እንጉታ፦
viewtopic.php?f=2&t=376412
viewtopic.php?f=2&t=376410&p=1610930#p1610930
viewtopic.php?f=2&t=376410
የአማራ ህዝብና የትግራይ ህዝብ ለዘመናት በፍቅር የኖሩና የተጋመዱ ክቡር ወንድማማች ህዝቦች ናቸው። በእልህና በጥላቻ በሚመሩ በአንዳንድ ‘ፖለቲከኞች’ የስህተት ቀመር ምክንያት፡ እነዚህ ወንድማማች ህዝቦች ሳይወዱ በግድ እንዲናቆሩ ብዙ ተንኮል ተሸርቧል። እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ግን በዚህ ችግር መሃል እሳት ማቀጣጠል ሳይሆን፡ እንደ መልካም ጎረቤት መጠን መፍትሄ እናጋራለን።
'ትግማራ' - 'የአማራና ትግራይ አወዛጋቢ ስፍራዎች' ሰላማዊ የመፍትሄ አማራጭ ቁልፍ ሃሳብ
1.) አማራና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ እያነሱ ሲናቆሩባቸው የቆዩ ስፍራዎች፡ ጽንፈኛ አስተሳሰብ ያላቸውን አስተዳዳሪዎችንና ሃላፊዎችን በሙሉ በቀጠናው ሃይሎች ትብብር አማካኝነት መቀዬር።
2.) በነዚህ አወዛጋቢ ስፍራዎች በሃላፊነት የሚቀመጡ አካላት በአባት ወይም በእናት ከአማራና ከትግራይ የሚወለዱ እንዲሆኑ አድርጎ ማዋቀር።
3.) “ሙሉ አማራ ነኝ”፣ “ሙሉ ትግሬ ነኝ” ብሎ በዘረኝነት ቆፈን የሚጋጋጥ ዜጋ፡ አንድም አወዛጋቢ ባልሆነው የክልሉ ክፍል ሆኖ መኖር፡ አሊያም አዲስ በሚመደቡት ከሁለቱ ግዙፋን ብሄሮች ወላጆች የተወለዱ ከጽንፈኛና ዘረኛ አስተሳሰብ በጸዱ የትግማራ አካላት ስር እንዲስተዳደር ማድረግ።
4.) በነዚህ አካባቢ የሚዋቀሩ የጸጥታ አካላት ሙሉ በሙሉ፡ የአማራና የትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ የጸጥታ አካላት ሙሉ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ማድረግ።
5.) ከጎረቤት ሃገር ከሱዳን ሆነ ከኤርትራ የጸጥታ ሃይሎች ጋር በዚህ ረገድ ሙሉ ትብብር ማድረግ።
6.) ነውጠኛ ጽንፈኛ አስተሳሰብ ያላቸውን አካላት አስፈላጊውን ገንቢ ትምህርት እንዲቀስሙ በማድረግ አንድም ትጥቅ ማስፈታት አሊያም ለአዲሱ የትግማራ አመራር ታዛዥነታቸውን በማረጋገጥ በበጎ የልማትና የጸጥታ ስራ ማሰማራት።
7.) የአማራ ሆነ የትግራይ ‘ከውዝግብ’ ነጻ የሆኑ ክፍሎች፡ የወንጀለኞች መደበቂያ እንዳይሆኑ፡ የትግማራ አመራር ለሚተገብራቸው ስራ ሙሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስቻል።
8.) የአማርኛና የትግርኛ ቋንቋዎች በነዚህ ስፍራዎች ህጋዊነታቸው ተረጋግጦ፡ ሁሉም የመንግሥት ጽሕፈት ቤቶች ያለ አንዳች አድልዎ እነዚህን ቋንቋዎች እንዲጠቀም ማድረግ። ትምህርትም በሁለቱ ቋንቋዎች እንዲሰጥ ማድረግ።
9.) ተንኮል ለመዝራት ጥላቻ ለማስፋፋት የሚጥሩ የውጭ ሆነ የውስጥ ሃይሎችን በተናበበ መልኩ መመከት። የአወዛጋቢ ስፍራዎች ህዝቦች፡ ችግር ሊያባብስ የሚችለውን ተንኮልና ሴራ ያነገበውን የብልጽግና ‘ሪፈረንደም’ ሆነ አላስፈላጊ ቁርቁስ ውስጥ የሚያስገባ፡ ግዜና ወቅት ያልጠበቀውን መለያዬትን የሚያበረታታውን ‘ምርጫን’ ገሸሽ እንዲሉ አድርጎ፡ ለሰላምና ለወንድማማችነት ለሚተጋው ለትግማራ አመራር ድጋፋቸውን እንዲለግሱ ብርቱ ጥረት ማድረግ።
10.) የትግማራ አመራሮች ሁሌም በአማራ እና በትግራይ ክልል ካሉ አመራሮች ሆነ ኃይሎች ጋር የሚመካከሩበትንና፡ የልማት ሆነ የጸጥታ ግስጋሲያቸውን የሚያሳዩበት ግንኙነቶችን ያለማቋረጥ በአመት ቢያንስ 4 ግዜ በየሶስት ወራት መከወን።
ለግዜው በኛ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ እይታ፡ የአማራና የትግራይ አወዛጋቢ ስፍራዎች ግዚያዊ ክስተት በዚህ መልኩ ሊቀረፍ እንደሚችል እንገምታለን። እስቲ ጎበዝ የሚጨመረውን ጨምራችሁ የሚጎድለውን አጉድላችሁ ወደ ትግባሬ አምሩ። ለዚህ ሰላማዊና ቅዱስ መፍትሄ የኤርትራ ህዝብና መንግሥት ሁሌም ከአማራና ከትግራይ ህዝቦች ጎን በመሆን የበኩሉን በጎ አስተዋጽኦ ለማድረግ ወደኋላ እንደማይል ስንገልጥላችሁ ደግሞ፡ የክልሎቹ ህዝቦች ለሚያስፈልጋቸውን የሸቀጥ የንግድ እና የመሰረተ ልማት ቁሶች፡ ኤርትራ ምጽዋን ሆነ አሰብን ክፍት በማድረግ ለቀጠናው ሰላም፡ ለነዚህ ክቡር ወንድም ህዝቦች መፋቀር የራሷን ገንቢ ሚናና አሻራ ለማሳረፍ ቆርጣ እንደተነሳችም ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
ተጻፈ ለትግማራ ትግባሬ፡ በአሳማራና አዶማራ ይሁንታ፡ በኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
እንጉታ፦
viewtopic.php?f=2&t=376412
viewtopic.php?f=2&t=376410&p=1610930#p1610930
viewtopic.php?f=2&t=376410