Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 44430
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የግብጽ ገረዶች ብሄራዊ ምክክሩ የዉሸት ነው እያሉ ለምንድን ነው ስለ ውጤቱ 24/7 የሚጨነቁት?

Post by Horus » 17 Aug 2026, 23:59

የሶሻልና ፖለቲካ ሳይንስ መሃይሞች የብሄራዊ ምክክሩ ፋይዳማ የረጅም ግዜ መዘዝ ወይም ውጤት ምን እንደ ሆነ ሊገባቸው አይችልም ።

1
ይህ የምክክር ሂደት የፈጠረው መረጃ ወይም የፖለቲካዊ ኢንፎርሜችን ክምችት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፖለቲካ ሳይንስ መቀመሪያ መሰረት ነው

በአንድ ቃል የዚህ ምክክር ውጤት የሆነው ብሄራዊ ፖሊቲካል ዳታ ምትክ የለሽ ብሄራዊ ህብትና የእውቀት መሰረት ነው

ብሄራዊ ምክክሩ ብሄራዊ ምርምር ነበር !

ይህን የሚገነዘቡ ምሁራን ብቻ ናቸው

2
INFORMATION ORGANIZES REALITY

የዚህ ብሄራዊ ምክክር አንድ እጅግ ግዙፍ ውጤት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ጥያቄዎች ፣ ችግሮች ፣ ሃሳቦችን ለመጀመሪያ ግዜ ያደራጀና ወደ ፊት ለሰዎች ፣ ፓርቲዎች፣ ቡድኖች፣ ምሁራን ማደራጃ አይተኬው መሳሪያ ነው።

ያለ ኢአንፎርሜሽን የሰው ልጆች ለምንም ነገር አይደራጁ፣ም

ስለዚህ የምክክር ኮሚሽኑ ውጤቶች መገራጃ ሃሳቦች ናቸው

3
ይህ የምክክር ሂደት ብሄራዊ የፖለቲካ ንቃተ ህሊና የፈጠራና ተከፋዮቹንም በልዩ ልዩ መስክና ደረጃ ለመሪነት ያበቃ ኩነት ነው

4
ምክክሩ ሊፈጽም የሚችላቸውና የሚፈልጋቸውን አጀንዳዎች መስጠት ብቻ ሳሆን መንግስት የሚቃወማቸውን ብሄራዊ አጀንዳች በማርቀቁ ለራሱ ለመግስት ከፍተኛ ፈተና የሰጠ ኩነት ነው። ከዛሬ ጀምሮ መንግስት በያንዳንዱ አጀንዳ ላይ በሚይዘው አቁምና በሚወስደው እርምጃ ይለካል ፣ በሰፊው ሕዝብ!

5
ውጤቱ ምንም ሆነ ምን ይህ አገራዊ ምክክር እጅግ ታሪካዊ ነበር ፣ነው ።


ሆረስ መላከ ብርሃን