1
ይህ የምክክር ሂደት የፈጠረው መረጃ ወይም የፖለቲካዊ ኢንፎርሜችን ክምችት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፖለቲካ ሳይንስ መቀመሪያ መሰረት ነው
በአንድ ቃል የዚህ ምክክር ውጤት የሆነው ብሄራዊ ፖሊቲካል ዳታ ምትክ የለሽ ብሄራዊ ህብትና የእውቀት መሰረት ነው
ብሄራዊ ምክክሩ ብሄራዊ ምርምር ነበር !
ይህን የሚገነዘቡ ምሁራን ብቻ ናቸው
2
INFORMATION ORGANIZES REALITY
የዚህ ብሄራዊ ምክክር አንድ እጅግ ግዙፍ ውጤት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ጥያቄዎች ፣ ችግሮች ፣ ሃሳቦችን ለመጀመሪያ ግዜ ያደራጀና ወደ ፊት ለሰዎች ፣ ፓርቲዎች፣ ቡድኖች፣ ምሁራን ማደራጃ አይተኬው መሳሪያ ነው።
ያለ ኢአንፎርሜሽን የሰው ልጆች ለምንም ነገር አይደራጁ፣ም
ስለዚህ የምክክር ኮሚሽኑ ውጤቶች መገራጃ ሃሳቦች ናቸው
3
ይህ የምክክር ሂደት ብሄራዊ የፖለቲካ ንቃተ ህሊና የፈጠራና ተከፋዮቹንም በልዩ ልዩ መስክና ደረጃ ለመሪነት ያበቃ ኩነት ነው
4
ምክክሩ ሊፈጽም የሚችላቸውና የሚፈልጋቸውን አጀንዳዎች መስጠት ብቻ ሳሆን መንግስት የሚቃወማቸውን ብሄራዊ አጀንዳች በማርቀቁ ለራሱ ለመግስት ከፍተኛ ፈተና የሰጠ ኩነት ነው። ከዛሬ ጀምሮ መንግስት በያንዳንዱ አጀንዳ ላይ በሚይዘው አቁምና በሚወስደው እርምጃ ይለካል ፣ በሰፊው ሕዝብ!
5
ውጤቱ ምንም ሆነ ምን ይህ አገራዊ ምክክር እጅግ ታሪካዊ ነበር ፣ነው ።
ሆረስ መላከ ብርሃን