Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11562
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Guess who is back?

Post by sarcasm » 08 Feb 2026, 20:36

አሁንስ ማንን ግማሹ በገብሪኤል ግማሹን በሚካኤል ይቀብራል?

Please wait, video is loading...

Meleket
Member
Posts: 4931
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Guess who is back?

Post by Meleket » 09 Feb 2026, 04:49

sarcasm wrote:
25 Jan 2022, 20:15
Please wait, video is loading...

viewtopic.php?f=2&t=346583&p=1501373#p1501373

Meleket wrote:
30 Aug 2024, 10:56
ታሪክም እማደል እየጻፍን ያለነው መልክ መልኩን እስቲ እናስይዘው https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=349277
Meleket wrote:
30 Aug 2024, 09:56
ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል
ገና ከጠዋቱ፣ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከስደት እንደተመለሱ፣ ኤርትራና ሶማሊያን ወደ ኢትዮጵያ ለማቀላቀል የመጀመሪያው ሥራዬ ነው ብለው በተነሱ ጊዜ፣ ራስ ካሣ እነዚህ ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሆነወ ኣልታዩዋቸውም። ራስ ካሣ የሚያስቡትን ለጃንሆይ ኣልደበቁም። አስተያየውም የተመረኮዘው በሚከተሉት ነጥቦች ላይ እንደነበረ ይነገራል።

. . . ጥንታዊ ታሪክና የግዛት ደንበርን እነበረበት ለመመለስ ብርቱ ጥረት ማድረግ ተገቢ ቢሆንም፣ ለአገር ጥቅም ለሚታሰቡት ሥራዎች ሁሉ ቅደም ተከተል መስጠት ያስፈልጋል። በጠላት ወረራ ምክንያት የተለየነው አገርና ሕዝብ፣ ከአምስት ዓመት በኋላ ስንመለስ ያገኘነው፣ መልኩንና ኣኳኋኑን ለውጦ ነው። በተለይ ይኸ በአርበኝነት ጫካ ሳይገባ፣ ለስደት እውጭ ሳይወጣ የኖረው ሕዝብ፣ በጣልያን የአስተዳደር ዘመን ድሮ ያላየውን ከልማዱ ውጭ የሆነ አንዳንድ ነገሮችን ቀምሷል። አሁን ኣፍ አውጥቶ አይናገረው እንጂ፣ በአስተዳደር በኩል ቢሆን፣ በዳኝነትና በኑሮም ኣኳኋን ቢሆን፣ በጣልያን ዘመን ለእኔ የሚጠቅም ነገር ነበር ብሎ፤ በልቡ የሚያስብ ብዙ ሰው መኖሩ የማይታበል ነው። አሁን እንደምናየው፣ ከእንግዲህ ወዲህ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደ ጥንቱ አንድ አድርጐ፣ በሥልጣን ለመግዛት ብዙ ችግር መኖሩ የሚካድ አይደለም። . . . በዚህ ሁሉ ነገር ላይ፣ በአለንበት በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት ዋና የመጀመሪያ ሥራ መሆን ያለበት፣

1ኛ/ በጠላት ምክንያት የተበላሸውን ያገር ልማድና አስተዳደር እቦታው መመለስ፣
2ኛ/ የአገሩ አንድነትና የንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣን እንዳይናጋ መሠረት እንዲጨብጥ ማድረግ፣
3ኛ/ ዳኝነት ሳይጓደል ክርስቲያንነትንና ሥርዓትን ማጥበቅ፣
4ኛ/ ሕዝቡን ማሠራትና የአገሩ ሀብት እንዲዳብር ማድረግ ነው።

. . . አሁን በእጃችን ያለው የኢትዮጵያ ግዛትና ሕዝብ፣ አንድነቱ በማይላላ አኳኋን ሲጠብቅ፣ በአንድ ንጉሠ ነገሥት ሥልጣንና በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ከጫፍ እስከ ጫፍ በትክክል የሚገዛ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ አገሩም ለምቶ ጥጋብ ሆኖ፣ የመንግሥቱ ቋት ሲሞላ፣ በመጀመሪያ ሀማሴኖች፣ ቀጥሎም እንደ ኣኳኋኑ ታይቶ ሱማሌዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መጠየቅ፣ ወይም እነሱ እንምጣ ቢሉ መቀበል፣ የተገባ ነው። እንደዚህ ከሆነ፣ መንግሥትም አገሮቹን ተረክቦ ለማስተዳደር፣ ሕዝባችንም የጥንት ወንድሞቹንና ወገኖቹን ተቀብሎ ለማላመድ የሚከብድ አይሆንም። ይኸ ሁሉ ሳይደራጅና በተለየም የአገሩ ሀብት ሳይዳብር፣ ግዛት ቢሰፋ፣ የሕዝብ ቁጥር ቢጨምር፣ አሁን ያለውን ችግር የበለጠ ከማባባስ በስተቀር የሚጠቅም ነገር የለም። . . . እየተደጋገመ የሚነገረው፣ ኢትዮጵያ ፣ የፈረንጆቹን ሥልጣኔ በቶሎ ለማግኘት ያልቻለችው፣ በባሕር በር እጦት ምክናይት ነው እየተባለ ነው። ሕዝባችንን ለማሠልጠን ዋና ቁልፉ የባሕር በር ከሆነ፣ በእንግሊዞች እርዳታ፣ አሰብ ከወሎ ጋር እንዲሆን ለምን ከአሁኑ ኣይደከምበትም? . . . አሁን ባለው ችግር ላይ ሌላ፣ ተጨማሪ የአስተዳደር ጣጣ ለመሸከም ከመቸኮል፣ ይኸው ሁሉ በእርጋታ ቢታሰብበት ይሻላል። . . . “ [በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ 1941-1963 እ.ኤ.ኣ. ገጽ 293-294 በዘውዴ ረታ]

https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=346583

Abere wrote:
18 Jul 2024, 08:28
.. ..
አዎ! አሰብ የኢትዮጵያ ነው። ሻዕብያ ይህን ያውቃል? በደንብ። አሰብ የወሎ ክፍለ-ሀገር አካል እንጅ የኤርትራ መቸ ሁኖ ያውቃል። .. .. ..
sarcasm wrote:
18 Jul 2024, 07:47
ዓሰብ የኤርትራ እንዳልሆነ ኢሰያስ ያውቃል። ዓሰብን እንደምንይዝም ያውቃል። . . . ወለጋ ሰላም እንዲሆን፤ ትግራይ፤ ሸዋ ሰላም እንዲሆን፤ ዓሰብ ላይ አነጣጥረህ ግባ! - የጠ/ሚ አቢይ ዮትዩበር ስዩም ተሾመ
ሲጠቃለል፦ ለማወራረጃነት ያህል “ኧረ እንዲያው ይመኙሻል/2/” ዬሚለውን የጉራጌው የመሓሙድን ዜማ ጋብዘናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።
የታሪክ ጨዋታዉ ፊሽካ እንደተነፋ ከመቅጽበት ኤርትራ 2 ጎሎችን አስመዝግባለች ጎልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል! በርካታ ኢትዮጵያዉያን የትግራይ ተወላጆችም፡ የኤርትራ ቲፎዞ በመሆን፡ ኤርትራ በብልጽግና ላይ ባስቆጠረችው ግብ ተደስተው በመጨፈር ላይ ይገኛሉ። “ባሕርና፡ እቲ ሓፋሽ ሕዝብና” የሚል ብርቅ ዜማቸውን ባስተጋቡበት ወቅትም፡ ጋዜጠኛው አርአያ ተስፋማርያምም በብስጭት በመብከንከን ሚይዘውና ሚጨብጠው ጠፍቶት በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚገኘው ከጋዜጠኛው ቴዎድሮስ ጸጋይ ጋር በቁጭት ሲብሰለሰሉና በነገር-ስራ ላይ ተጠምደው ሲፍጨረጨሩ ተስተውለዋል።

Post Reply