Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4545
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል

Post by Meleket » 30 Aug 2024, 09:56

ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል
ገና ከጠዋቱ፣ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከስደት እንደተመለሱ፣ ኤርትራና ሶማሊያን ወደ ኢትዮጵያ ለማቀላቀል የመጀመሪያው ሥራዬ ነው ብለው በተነሱ ጊዜ፣ ራስ ካሣ እነዚህ ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሆነወ ኣልታዩዋቸውም። ራስ ካሣ የሚያስቡትን ለጃንሆይ ኣልደበቁም። አስተያየውም የተመረኮዘው በሚከተሉት ነጥቦች ላይ እንደነበረ ይነገራል።

. . . ጥንታዊ ታሪክና የግዛት ደንበርን እነበረበት ለመመለስ ብርቱ ጥረት ማድረግ ተገቢ ቢሆንም፣ ለአገር ጥቅም ለሚታሰቡት ሥራዎች ሁሉ ቅደም ተከተል መስጠት ያስፈልጋል። በጠላት ወረራ ምክንያት የተለየነው አገርና ሕዝብ፣ ከአምስት ዓመት በኋላ ስንመለስ ያገኘነው፣ መልኩንና ኣኳኋኑን ለውጦ ነው። በተለይ ይኸ በአርበኝነት ጫካ ሳይገባ፣ ለስደት እውጭ ሳይወጣ የኖረው ሕዝብ፣ በጣልያን የአስተዳደር ዘመን ድሮ ያላየውን ከልማዱ ውጭ የሆነ አንዳንድ ነገሮችን ቀምሷል። አሁን ኣፍ አውጥቶ አይናገረው እንጂ፣ በአስተዳደር በኩል ቢሆን፣ በዳኝነትና በኑሮም ኣኳኋን ቢሆን፣ በጣልያን ዘመን ለእኔ የሚጠቅም ነገር ነበር ብሎ፤ በልቡ የሚያስብ ብዙ ሰው መኖሩ የማይታበል ነው። አሁን እንደምናየው፣ ከእንግዲህ ወዲህ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደ ጥንቱ አንድ አድርጐ፣ በሥልጣን ለመግዛት ብዙ ችግር መኖሩ የሚካድ አይደለም። . . . በዚህ ሁሉ ነገር ላይ፣ በአለንበት በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት ዋና የመጀመሪያ ሥራ መሆን ያለበት፣

1ኛ/ በጠላት ምክንያት የተበላሸውን ያገር ልማድና አስተዳደር እቦታው መመለስ፣
2ኛ/ የአገሩ አንድነትና የንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣን እንዳይናጋ መሠረት እንዲጨብጥ ማድረግ፣
3ኛ/ ዳኝነት ሳይጓደል ክርስቲያንነትንና ሥርዓትን ማጥበቅ፣
4ኛ/ ሕዝቡን ማሠራትና የአገሩ ሀብት እንዲዳብር ማድረግ ነው።

. . . አሁን በእጃችን ያለው የኢትዮጵያ ግዛትና ሕዝብ፣ አንድነቱ በማይላላ አኳኋን ሲጠብቅ፣ በአንድ ንጉሠ ነገሥት ሥልጣንና በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ከጫፍ እስከ ጫፍ በትክክል የሚገዛ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ አገሩም ለምቶ ጥጋብ ሆኖ፣ የመንግሥቱ ቋት ሲሞላ፣ በመጀመሪያ ሀማሴኖች፣ ቀጥሎም እንደ ኣኳኋኑ ታይቶ ሱማሌዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መጠየቅ፣ ወይም እነሱ እንምጣ ቢሉ መቀበል፣ የተገባ ነው። እንደዚህ ከሆነ፣ መንግሥትም አገሮቹን ተረክቦ ለማስተዳደር፣ ሕዝባችንም የጥንት ወንድሞቹንና ወገኖቹን ተቀብሎ ለማላመድ የሚከብድ አይሆንም። ይኸ ሁሉ ሳይደራጅና በተለየም የአገሩ ሀብት ሳይዳብር፣ ግዛት ቢሰፋ፣ የሕዝብ ቁጥር ቢጨምር፣ አሁን ያለውን ችግር የበለጠ ከማባባስ በስተቀር የሚጠቅም ነገር የለም። . . . እየተደጋገመ የሚነገረው፣ ኢትዮጵያ ፣ የፈረንጆቹን ሥልጣኔ በቶሎ ለማግኘት ያልቻለችው፣ በባሕር በር እጦት ምክናይት ነው እየተባለ ነው። ሕዝባችንን ለማሠልጠን ዋና ቁልፉ የባሕር በር ከሆነ፣ በእንግሊዞች እርዳታ፣ አሰብ ከወሎ ጋር እንዲሆን ለምን ከአሁኑ ኣይደከምበትም? . . . አሁን ባለው ችግር ላይ ሌላ፣ ተጨማሪ የአስተዳደር ጣጣ ለመሸከም ከመቸኮል፣ ይኸው ሁሉ በእርጋታ ቢታሰብበት ይሻላል። . . . “ [በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ 1941-1963 እ.ኤ.ኣ. ገጽ 293-294 በዘውዴ ረታ]

viewtopic.php?f=2&t=346583

Abere wrote:
18 Jul 2024, 08:28
.. ..
አዎ! አሰብ የኢትዮጵያ ነው። ሻዕብያ ይህን ያውቃል? በደንብ። አሰብ የወሎ ክፍለ-ሀገር አካል እንጅ የኤርትራ መቸ ሁኖ ያውቃል። .. .. ..
sarcasm wrote:
18 Jul 2024, 07:47
ዓሰብ የኤርትራ እንዳልሆነ ኢሰያስ ያውቃል። ዓሰብን እንደምንይዝም ያውቃል። . . . ወለጋ ሰላም እንዲሆን፤ ትግራይ፤ ሸዋ ሰላም እንዲሆን፤ ዓሰብ ላይ አነጣጥረህ ግባ! - የጠ/ሚ አቢይ ዮትዩበር ስዩም ተሾመ
ሲጠቃለል፦ ለማወራረጃነት ያህል “ኧረ እንዲያው ይመኙሻል/2/” ዬሚለውን የጉራጌው የመሓሙድን ዜማ ጋብዘናል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Abere
Senior Member
Posts: 13839
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል

Post by Abere » 30 Aug 2024, 10:07

Meleket,

መልካም ዕለተ-ዓርብ። በጥላሁን ገሰሰ ዘፈን እስኪ ፈታ በል። ከዩክሬን እስከ ግብጽ፤ ኢትዮጵያ ኳትነሃል። << ያሰብኩት ተሳካ ያለምኩት ደረሰ! >>

ለሁሉም ጊዜ አለው - የተሰረቀ ይመለስ ግድ ነው እና!

Meleket
Member
Posts: 4545
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል

Post by Meleket » 30 Aug 2024, 11:13

ወዳጃችን Abere ጥሌ ጐበዝ ድምጻዊ ነበር፡ ነፍሱን በመንግስተሰማይ ያኑርልን።

ዕለተ ዓርብን ስታነሳ መቼም ትዝ ዬሚለን የኤርትራችን መዲና አስመራ በታጋዮቻችን ቁጥጥር ስር ዬነበረችበት ግዜ ነው። ስንቱን የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ቅዘን በቅዘን አድርገው እንደ እንትን እዬነዱ ሲነጉዱ። ህዝባችን ደግሞ ምን ይል ነበር መሰለህ “ክኣትዉ ቀራናት ኪወጽኡ ጓዕማማት” ይላቸው ነበር ምስኪኖቹን ትርጉሙ
ሲገቡ እየፎከሩና እያቅራሩ ጀብደኞችና ጀግኖችን መስለው ሲወጡ ደግሞ ተደፍጥጦ የተጨፈለቀ ማንቆርቆሪያ መስለው ወጡ እንደማለት ነው።

ኣቦ ትዝታ ቀሰቀስክብን እኮ “አውጊሓትልና እታ ዓርቢ ምሸት” ሲባል ትዝ ኣለን።

ዓሰብ ላይ ከተነዱት መካከል እስቲ 10 አለቃ ነገራን ወይም አጎትህን ፎቶው ውስጥ ለማግኘት ሞክር ወዳጃችን፡ ብለናል እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Prisoners of war in Assab, Eritrea [Photo by Habtom Berhe, from the Greg Marinovich collection]

Meleket
Member
Posts: 4545
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል

Post by Meleket » 13 Sep 2024, 11:20

Meleket wrote:
11 May 2022, 09:25
ቤነገራችን ላይ ግጥሙ፡ ለ'ጋዜጠኛው ቴድሮስ ጸጋዬ" ወልጋዳ ምልከታ የተገጠመ ነበር፡ እስቲ ኣጣጥሙ፡ በኤርትራዊ ኣማርኛ የተጣፈ ነው! :mrgreen:
Meleket wrote:
11 May 2022, 04:23
'በአንከላኛ'ና በከበደ ሚካኤልኛ የገጠምነውን እናጋራ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። "ኣንከላኛ' ደግሞ ምንኛ ነው እንዳትሉ! :mrgreen:
Meleket wrote:
12 Aug 2018, 08:53
ርእዮት - ግርድፍ ግጥም

አንድ እናት ነበረች ልጆች የነበሯት፣
እጅግ ውብ የሆነች እንከን የማይወጣት።

ያለም ነገር ሆኖ እርጅና መጥቶ፣
ልጆች ስታሳድግ እንግልቷ በዝቶ፣
ብዙ ስቃይ አየች የማያልቅ ተወርቶ።
ግን አልሰነፈችም በማድረጓ ጥረት፣
አንድ ልጇን ዳረች መርቃ በክብረት።

ያለም ነገር ሆኖ የጤናዋ ጉዳይ፣
ለልጆቿ ስትል እሷ ስትሰቃይ፣
ከእለት ወደ እለት መሻሻል ሳያሳይ፣
ከእርጅናው ጋራ አባሰባት ስቃይ።

እንዲህ እንዲህም ሲል ያይኗን ብርሃን አጣች፣
ልጆቿ ሲያብቡ እሷ ግን ገረጣች።
ይህንን ታዝባ ባለ ትዳር ልጇ፣
እናቷን መርዳቷን አረገች ግዳጇ።

እናቷን ስትመራ በመንገዷ ሁሉ፣
ለመመረቅ ነበር እንዲያው በጥቅሉ።

እናትየዋ ግን የእናት ነገር ሆኖ፣
ልጆቿን ስትመግብ አንድ ልጇ ጨክኖ፣
አንድ ሃሳብ አመጣ አወላግዶ አጢኖ፣
ካወቅኩ ባይ ልጇ በቀረበ ‘መላ’፣
በሰላሙ ሰፈር ተንኮል እንዲያጠላ፣
እንዲህ እንዲህ አላት በነገር ፍተላ።

“ልጄ በመሆንሽ ራሴ የወለድኩሽ፣
የምልሽን ስሚ እንዲያው አትቅለስለሽ።

ይህ ያይኖችሽ ብርሃን ከኔ የወረስሽው፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ ቁርጥሽን እወቂው።

ይህን ሃቅ አጢነሽ ተንግዲህ በኋላ፣
ማንኛውም ስራሽ እኔን ማያጉላላ፣
እንዲሆን አድርጊ እኛ እንዳንጣላ!

እንዲያውም ይህ ዓይንሽ ሁሉን ምታይበት፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ እንዳሻኝ ምሆንበት፣”
ብላ እንድታስብ ያቺ ምስኪን እናት፣
አወቅኩ ባይ ልጇ በአንክሮ መከራት።

ባለትዳር ልጇ የመላች በትዕግስት፣
መረጠች ለናቷ እውነቱን ልትነግራት።

“እማማ እናታለም ወላጄ ውቢቱ፣
ይህን ሃቅ ስሚኝ እንዲያው ባዛኝቱ።

ድሮ ዓይኖች ነበሩሽ ምን ምን የመሰሉ፣
“በፌደሬሽን” ወቅት ላንቺ የተተከሉ፣

ያያቸውን ሁሉ እንዲያው ሚያማልሉ፣
እኛን በማሳደግ ውለታን የዋሉ።

የአምላክ ስራ ሆኖ ስለጠፉ አሁን፣
እንዴት ታልሚያለሽ ጌታን ለመኮነን?

ባለም አደባባይ ክሶችን መስርተሽ፣
እንዴት ልትዘልቂው ነው ፈጣሪን ሞግተሽ?
ያይንሽንስ ብርሃን እንዴት ልትመልሽ?

የተጠቃሚነት መብቱ ይገባኛል፣
የራስ ባልሆነ ዓይን እንዴትስ ይቻላል?

ይልቅ ጠባይ አርገሽ ከኔ ከልጅሽ ጋር፣
በብርሃኔ ልምራሽ እንኑር በፍቅር።

አንቺም ዋዛ አይደለሽ ብዙ ሃብቶች አሉሽ፣
ይህ የዓይኔ ብርሃን አይቀርም ሳይጠቅምሽ።

እንዲህ እንዲህ አርገን እየተጠቃቀምን፣
በፍቅር መኖር ነው ለኛ የሚበጀን።

ያለሽ አንድ አማራጭ ዓይንሽ እንዲበራ፣
እሱ ራሱ መጥቶ ተዓምር ካልሰራ፣
ሌላ መላ የለም ሚሆን በፉከራ፣
ጭቃውን አብኩቶ አይንሽን ነካክቶ፣
እሱ ካልዳበሰሽ ተሰማይ መጥቶ፣
የትም አያደርስሽ ሽለላ ቀረርቶ።

ተከባብሮ መኖር እያለ አንድ መላ፣
ተጋግዞ መኖርም እያለ አንድ መላ፣
እስቲ ዕድል አንስጠው ተንኮል ለሚያሰላ፣
አዋቂ ነኝ ለሚል ለማንም ቱልቱላ፣
ሌተቀን ለሚያልም እኛኑ ሊያባላ።

እኔና አንቺ ሁሌም ከልብ ስንፋቀር፣
እምንሰራው ሁሉ እንደሚሆን ተአምር፣
መሰሪ ዲያብሎስን እንደሚያደርግ ኩምትር፣
በምን አማርኛ ለመግለጽ ልሞክር!!!!!!!
ፍንጭ፦ ይህ ጽሑፍ ዓላማው፣ የሰው ገንዘብ ሚመኝን ክፉ መካሪ መሰሪን ለመገሰጽ ነው።

Meleket
Member
Posts: 4545
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል

Post by Meleket » 05 Jun 2025, 10:47

Meleket wrote:
30 Aug 2024, 11:13
ወዳጃችን Abere ጥሌ ጐበዝ ድምጻዊ ነበር፡ ነፍሱን በመንግስተሰማይ ያኑርልን።

ዕለተ ዓርብን ስታነሳ መቼም ትዝ ዬሚለን የኤርትራችን መዲና አስመራ በታጋዮቻችን ቁጥጥር ስር ዬነበረችበት ግዜ ነው። ስንቱን የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ቅዘን በቅዘን አድርገው እንደ እንትን እዬነዱ ሲነጉዱ። ህዝባችን ደግሞ ምን ይል ነበር መሰለህ “ክኣትዉ ቀራናት ኪወጽኡ ጓዕማማት” ይላቸው ነበር ምስኪኖቹን ትርጉሙ
ሲገቡ እየፎከሩና እያቅራሩ ጀብደኞችና ጀግኖችን መስለው ሲወጡ ደግሞ ተደፍጥጦ የተጨፈለቀ ማንቆርቆሪያ መስለው ወጡ እንደማለት ነው።

ኣቦ ትዝታ ቀሰቀስክብን እኮ “አውጊሓትልና እታ ዓርቢ ምሸት” ሲባል ትዝ ኣለን።

ዓሰብ ላይ ከተነዱት መካከል እስቲ 10 አለቃ ነገራን ወይም አጎትህን ፎቶው ውስጥ ለማግኘት ሞክር ወዳጃችን፡ ብለናል እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Prisoners of war in Assab, Eritrea [Photo by Habtom Berhe, from the Greg Marinovich collection]
sarcasm wrote:
25 Jan 2022, 20:15

Misraq
Senior Member
Posts: 15388
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል

Post by Misraq » 05 Jun 2025, 14:53

አበረ ደቡቤ ነው። በግልጽ ተናግሮታል ይህን ፎረም ሲቀላቀል። የኦሮሞና የጉራጌ ድቅል ነኝ ብሏል።

Meleket
Member
Posts: 4545
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለወሎዬው Abere እና ለጉራጌው ስዩም ተሾመ፣ ራስ ካሣ የሚከተለውን የአደራ ደብዳቤ ልከውላችኋል

Post by Meleket » 07 Jun 2025, 02:47

እንዲያ ከሆነማ ያለ ጥርጥር ኣጐቱን ከምርኮኞቹ ውስጥ ፈልፍሎ ሊያገኛቸው ይችላል፡ ምክንያቱም ከምርኮኞቹ ከፊሎቹ ኣማርኛን ኣቀላጥፍው መናገር የማይችሉ፡ ቅላጺያቸው ተደቡብ መሆኑ ቁልጭ ብሎ የሚታወቅ ነበርና!
Misraq wrote:
05 Jun 2025, 14:53

Post Reply