ራሻ ሰፈረች ስንዴ ለአፍሪካ
መቼም ሰርታ አታውቅም አንድ ቀን ፋብሪካ!
![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)
ኤርትራን በናፓልም እንዳልደበደበች፡
ያኔ ደርጎቹንም እንዳላማከረች፡
ስንዴ ልስጥ እያለች ጉራ ቸበቸበች።
![Laughing :lol:](./images/smilies/icon_lol.gif)
ልዑላዊት ሃገር የወረረው ፑቲን፡
ቤተስኪያን በስሙ ያሰዬመው ፑቲን፡
ዩክሬን ሃገር ገብቶ የወረረው ፑቲን፡
‘ፉርሽ ሪፈረንደም’ ያደረገው ፑቲን፡
ጻድቅ ነው ይሉናል የማያንስ ከፑሽኪን፡
ይቅረጹለት ሓዉልት እኛ ምን ኣገባን።
![Laughing :lol:](./images/smilies/icon_lol.gif)
ባምሳ ሽሕ ቶን ስንዴ አፍሪካን ሊደልል፡
ምንም ኣላፈረም ይህ የራሻ ጠብደል።
![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)
የደም ስንዴም ኣለ የደም ስንዴ ለካ፡
በሚሳይል ታጭዶ፡ በድሮን ሲለካ፡
ተራሻ ተጭኖ ሚደርስ ተኣፍሪካ።
![Mr. Green :mrgreen:](./images/smilies/icon_mrgreen.gif)