Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3982
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የደም ስንዴ [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 29 Jul 2023, 05:06

የደም ስንዴ[ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

ራሻ ሰፈረች ስንዴ ለአፍሪካ
መቼም ሰርታ አታውቅም አንድ ቀን ፋብሪካ! :mrgreen:

ኤርትራን በናፓልም እንዳልደበደበች፡
ያኔ ደርጎቹንም እንዳላማከረች፡
ስንዴ ልስጥ እያለች ጉራ ቸበቸበች። :lol:

ልዑላዊት ሃገር የወረረው ፑቲን፡
ቤተስኪያን በስሙ ያሰዬመው ፑቲን፡
ዩክሬን ሃገር ገብቶ የወረረው ፑቲን፡
‘ፉርሽ ሪፈረንደም’ ያደረገው ፑቲን፡
ጻድቅ ነው ይሉናል የማያንስ ከፑሽኪን፡
ይቅረጹለት ሓዉልት እኛ ምን ኣገባን። :lol:

ባምሳ ሽሕ ቶን ስንዴ አፍሪካን ሊደልል፡
ምንም ኣላፈረም ይህ የራሻ ጠብደል። :mrgreen:

የደም ስንዴም ኣለ የደም ስንዴ ለካ፡
በሚሳይል ታጭዶ፡ በድሮን ሲለካ፡
ተራሻ ተጭኖ ሚደርስ ተኣፍሪካ።
:mrgreen: