Horus wrote: ↑30 Dec 2022, 21:54
It is so pathetic from the government to jail Teddy Yo.
He has every right to experss his feelings and political views using his music.
What a bunch of insecure ሰገጤs!
They just made him a hero and made his music very popular.
PP is full of low IQ narrow fools. They are just useless bunch!
They are losing all their support from all sectors of the society.
The day Ethiopians see any sane alternative, PP will be thrown out of the window in a blink of an eye. That is for sure.
የወንዜ
ልዩ ነሽ አዎ አማላይ
በውበትሽ ሰው ገዳይ
የኔ እያሉሽ ያለከልካይ
ስንቱን አየን ባቺ ጉዳይ
እውነት እውነቱን እስቲ ልናገር
ሁሉም ይበል ባንቺ ጥንቅር
ተወል ደናል እኛ ሸገር
እንደሌለው ሆንን ሀገር
እደጊ ብዬ ብዬ ቤቴን ለቀኩልሽ
ያላቀና ጎዳና ሲጠልሽ
እትብቴን አቅረሽ ተፋሽ
ይሁና አንቺን ግን አይክፋሽ
ሰውም አይኖር ያለመሬት
መሬትም አይኖር ያለሰው
ዝም ያለው ልጅ የሸገር ሰው
ወዴት ይሆን ሄዶ የሚያርሰው
አዝማች---
የወንዜ የወንዜ የወንዜ ትርምስ
ጥያቄ ብቻ ንው መልሱ ላይመለስ
የወንዜ የወንዜ የወንዜ አራት ኪሎ
ወንበርሽ ይፋጃል ጠፋ ሁሉን ጥሎ
ያራዳ ልጅ መሆን እድለኛ
የፀዳ ነው ከዘረኛ
ለመጣው ሁሉ ለተረኛ
ማጨብጨብ ነው ለቀማኛ
ሸገር ተወልዶ ማደጉ
የቱጋ ነው አስቲ ጥቅሙ
በስጋት ቤት ማጉረምረሙ
መኖር አፈር እየቃሙ
ይባስ ካምናው ዘንድሮ
ልቤ ከቀዬው ተባሮ
በቃ እሺ ልጀምረፍ ጉዞ
ክፉ ከማይ ከዚ ብሶ
በፍቅር ስኖር ባንቺ ኮርቼ
አላውቅም ነበር ተከፍቼ
ግዜ ጌታ ነው ተገፍቼ
ስደት መረጥኩ ተገፍቼ
አስቤ አላውቅ ባህር ማዶ
ክፋት ሲበዛ ስር ስር ሰዶ
ፍቅር እኛ ጋር ኪስ ግን ባዶ
በዚም ተቀና አይስቁም ወዶ
አዝማች ------
አርንጋዴ ቢጫ ቀይ አርማችን የኛ መመኪያችን
ፍቅር መስጠት ያስተማረችን ሸገር እናታችን
ቀዬ ፈርሶ ህንፃ ቢደረደር ለይቀረፍ ችግር
ሰው አይተካ ዲንጋይ ቢራረብ ጠፍቶ መተሳሰብ
ጎበዝ ንቃ ንቃ ንቃ
ሰግጣ ስቃ ስቃ ስቃ
ከበረች ዝቃ ዝቃ ዝቃ
ሄደች ልቃ ልቃ ልቃ
ሲረኞች አንቺን ለማዋረድ
ሳያውቁሽ ከውጪ ማጎብደድ
ግን ሆነሽ የኣፍሪካችን ዘውድ
ይዘውታል ክፋትን ማላመድ
ስም አወጡልሽ የዳቦ
ዳቦሽን ሳይቀምሱ በጉቦ
ሊበላሽ ካሰበው ተርቦ
ይጠብቅሽ አምላክ አስቦ
አዝማች---
የወንዜ የወንዜ የወንዜ ትርምስ
ጥያቄ ብቻ ንው መልሱ ላይመለስ
የወንዜ የወንዜ የወንዜ አራት ኪሎ
ወንበርሽ ይፋጃል ጠፋ ሁሉን ጥሎ