Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42909
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by Horus » 11 Mar 2022, 03:35

ለምን?
(1) አንድ ኢትዮጵያዊ እሴት/ ቫልዩ ሊኖረው አይችልም፤
(2) አንድ የኢትዮጵያ አጀንዳ ሊኖረው አይችልም፤
(3) አንድ የሚያደርግ የፖለቲካ ፍልስፍና፣ ርዕዮት፣ ንድፈ ሃሳብ ሊኖረው አይችልም፤
(4) አንድ ሚሽን/ተልዕኮ ሊኖረው አይችልም፤
(5) አንድ ግብ፣ እስትራተጂና ስነምግባር ሊኖረው አይችልም፤
(6) አንድ ውሁድ ፓርቲ ሊያደራጅ አይችልም፤
(7) ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ግምባር እንጂ ውሁድ ፓርቲ አይደለም፤
(8) ብልጽግና አንድ ወጥ ውሁድ ፓርቲ የሚያደርገው ሕጎችና ደምቦች ሊኖሩት አይችልም፤
(9) ስለሆነም የፓርቲውን ስራዎች ማስፈጸም አይችልም ። ብልጽግና ብሄራዊ አጀንዳ ፐርፎርም ማድረግ አይችልም፤
(10) የጎሳ ፖለቲካ ስርዓት ፈርሶ በግለሰቦች አባልነት እስካልቆመ ድረስ ብልጽግና ማለት የጎሳ ናኡስ ከበርቴና የጎሳ የቢሮ ከበርቴ መሬት መነገጃ፣ ባጀት መዝረፊያ፣ ጉቦ መሰብሰቢያ ኢመደበኛ የጎሳ ካርቴል ሆኖ ይቀጥላል ።

Last edited by Horus on 13 Mar 2022, 02:41, edited 1 time in total.

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by kibramlak » 11 Mar 2022, 04:13

ሆረስ
ብልፅግና ሲዋቀርም በጎሳ ነበር አሁንም የጎሳ ነው ፣ ኢሀዴግ የጎሳ ሆኖ እንደትተፈጠረ የጎሳ እንደሆነ ወደ ብልፅግና ተሸጋገረ

አሁን ብልፅግና አመራር ያሉትም በጣም ምግባረ ብልሹ እና ባለጌወች ናቸው
ከእነዚህ ባለጌወች የተሻለ ነገር ይመጣል ብለህ አትጠብቅ፣ ያው እንደፈረደብን አንድ ቀን ህዝባዊ ማዕበል ይመጣና ይበላቸው ይሆናል፣ ሌላ ተመሳሳይ ይከተልና ተመሳሳይ አዙሪት

ኢሀዴግ የ1997ቱን የምርጫ እድል በላው፣ ሴረኛው አብይ ያለፈውን ምርጫ ለእኩይ አላማ ተረማመደበት ፣፣ ይህ ሁሉ የሚያሳይህ ከጎሳ አንጎላሞች ምንም የተሻለ ነገር አይወጣም

Horus
Senior Member+
Posts: 42909
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by Horus » 11 Mar 2022, 04:36

ክብራምላክ፣
ዛሬ ብልጽግናዎች የጉባኤ አጀንዳ ሲያረቅቁ ተነሱ፣ ተገመገሙ ከተባሉት ጉዳዮች የሚከተሉት ይገኙበታል ።

(1) ያለፉ (የድሮ) ስኬቶችን መደምሰስ፤ የድርጅቱ አባላትና መሪዎች በድርጅቱ ታሪክ ላይ ተመሳሳይ ግምገማ የላቸውም ማለት ነው ። ይህም ማለት ስኬት ወይም ውድቀት መለኪያ መስፈርት ሲጀምርም አልነበራቸውም ነው፤ ፒፒ የተግባር ስርዓት የለውም።
(2) የፓርቲው አባላት ትኩረት አንድ በሚያደርጉ ነገሮች ላይ ሳይሆን በሚለያዩን ነገሮች ላይ ነው ብለዋል። ስለዚህ ፓርቲው አንድ ውሁድ ድርጅት ሳይሆን የተለያዩ ክልል ድርጅቶች ፌዴሬሽን ወይም ግምባር ነው። ይህ የፒፒ ቁጥር 1 ችግር እና መፍረሻው ጉዳይ ነው። ስለሆነም ፒፒ አንድ ፓርቲ አይደለም ልክ እንደ ኢሃዴግ ግምባር ነው።
(3) ተግባራዊ እስትራተጂ ወይም ዘዴ የለውም ብለዋል ማለት ፓርቲው ፐርፎርም ማድረግ አይችልም፣ ስራዎችን መፈጸም አይችልም ማለት ነው።
(4) ግለሰብ መሪዎች ከፓርቲ ሕግ በላይ ወይም ካገር ህግ በላይ ሆነው አምባ ገነን ሆነዋል ይላል። እራሳቸውን ካገር ጉዳይ በላይ አድርገው ያያሉ ይላል። ይህም ማለት ፓርቲው ህግ የለውም፣ በህግ አይገዛም ። ኢመደበኛ ድርጅት ነው ማለት ነው ።
(5) የፓርቲው ተልኮ ያልተሳካው ለምንድን ነው? በፓርቲው ተልኮ ላይ አባላቱ አይስማሙም ወይም ፓርቲው ሚሽን የለውም ማለት ነው።
(6) ፓርቲው ፍጹም ኮራፕት የሌቦች ስብስብ ነው ይህ የኤቲክስ ብቻ ሳይሆን የአላማ፣ የሚሽን የቪዝን እጦትና አንድ አለመሆን ነው።
(7) ፓርቲው ለምንድን ነው አንድነት የሌለው? የኢትዮጵያ አጀንዳ ሳይሆን የጎሳና የግል ጥቅመኞች ስብስብ ስለሆነ ነው ፤ አባላቱ የጎሳ እንጂ የኢትዮጵያ ወኪሎች አይደሉም ።
እነዚህ እጅግ ግዙፍ የችግሮች ዝርዝር ነው ። አሁን ከዚህ ተነስተ ምን እንደ ሚወስኑ እንጠብቅ! እሁድ ሁሉንም እናውቃለን።

እኔ በዚህ ሁሉ ምንም ብዥታ የለኝም ። የዚህ ሁሉ መፍቻ ቁልፉ ሕገ መንግስቱን ለሪፎርም አቅርቦ እንዴት ወደ ዘመናዊ የዜጎች ፖለቲካ ሲስተም እንደ ምንሄድ እንመካከር የሚል ሃሳብ ሲያነሱ ብቻ ነው ብርሃን የሚፈነጥቀው ። እስከዚያ የኛ ሃላፊነት ድመቷን ድመት ብለን መጥራት ነው ።

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by kibramlak » 11 Mar 2022, 04:53

ሆረስ፣
የተባሉት ነጥቦች ትክክል ናቸው፣ ዋንኛ መልሱም ይታወቃል አንተም ብለኸዋል
የኦሮሞ ጎሰኞች በኦሮምያ ስም የሚዘርፍት ፣ የአማራ ገረዶች በታዛዥነት የሚያገኙት ጥቅማጥቅሞች የጎሳ ስርአት ለውጥ ስለሚያስቀርባቸው እላይ የተነሱትን ጥያቄ እንዴት እንደሚመልሱት እና በተፃራሪ የቆመ እስተሳሰባቸውን እንዴት እንደሚያክሙት ግን አላውቅም፣፣ ማየትና መደነቅ ነው ፣ እነ ሲረኛው አያልቅበትም የሚለው አያጣም፣፣ መሬት እሚነካ ሳይሆን ለሜድያ ኮንሳምፕሽን የሚሆን ብቻ ይዘው ቢመጡ እመነኝ ህዝቡ ጫፍ ላይ ደርሳል ሌላ ህዝባዊ ማዕበል ለማንሳት ትንሽ ምክንያት ነው የሚፋልገው ፣፣ እንደምታውቀው ትልልቅ ህዝባዊ ነውጦች የሚፈጠሩት በትንሽ ምክንያት ነውና ፣፣ የታመቀ ብሶትን ለማፈንዳት ትንሽ ጉልበት ብቻ ነው የሚበቃው
Horus wrote:
11 Mar 2022, 04:36
ክብራምላክ፣
ዛሬ ብልጽግናዎች የጉባኤ አጀንዳ ሲያረቅቁ ተነሱ፣ ተገመገሙ ከተባሉት ጉዳዮች የሚከተሉት ይገኙበታል ።

(1) ያለፉ (የድሮ) ስኬቶችን መደምሰስ፤ የድርጅቱ አባላትና መሪዎች በድርጅቱ ታሪክ ላይ ተመሳሳይ ግምገማ የላቸውም ማለት ነው ። ይህም ማለት ስኬት ወይም ውድቀት መለኪያ መስፈርት ሲጀምርም አልነበራቸውም ነው፤ ፒፒ የተግባር ስርዓት የለውም።
(2) የፓርቲው አባላት ትኩረት አንድ በሚያደርጉ ነገሮች ላይ ሳይሆን በሚለያዩን ነገሮች ላይ ነው ብለዋል። ስለዚህ ፓርቲው አንድ ውሁድ ድርጅት ሳይሆን የተለያዩ ክልል ድርጅቶች ፌዴሬሽን ወይም ግምባር ነው። ይህ የፒፒ ቁጥር 1 ችግር እና መፍረሻው ጉዳይ ነው። ስለሆነም ፒፒ አንድ ፓርቲ አይደለም ልክ እንደ ኢሃዴግ ግምባር ነው።
(3) ተግባራዊ እስትራተጂ ወይም ዘዴ የለውም ብለዋል ማለት ፓርቲው ፐርፎርም ማድረግ አይችልም፣ ስራዎችን መፈጸም አይችልም ማለት ነው።
(4) ግለሰብ መሪዎች ከፓርቲ ሕግ በላይ ወይም ካገር ህግ በላይ ሆነው አምባ ገነን ሆነዋል ይላል። እራሳቸውን ካገር ጉዳይ በላይ አድርገው ያያሉ ይላል። ይህም ማለት ፓርቲው ህግ የለውም፣ በህግ አይገዛም ። ኢመደበኛ ድርጅት ነው ማለት ነው ።
(5) የፓርቲው ተልኮ ያልተሳካው ለምንድን ነው? በፓርቲው ተልኮ ላይ አባላቱ አይስማሙም ወይም ፓርቲው ሚሽን የለውም ማለት ነው።
(6) ፓርቲው ፍጹም ኮራፕት የሌቦች ስብስብ ነው ይህ የኤቲክስ ብቻ ሳይሆን የአላማ፣ የሚሽን የቪዝን እጦትና አንድ አለመሆን ነው።
(7) ፓርቲው ለምንድን ነው አንድነት የሌለው? የኢትዮጵያ አጀንዳ ሳይሆን የጎሳና የግል ጥቅመኞች ስብስብ ስለሆነ ነው ፤ አባላቱ የጎሳ እንጂ የኢትዮጵያ ወኪሎች አይደሉም ።
እነዚህ እጅግ ግዙፍ የችግሮች ዝርዝር ነው ። አሁን ከዚህ ተነስተ ምን እንደ ሚወስኑ እንጠብቅ! እሁድ ሁሉንም እናውቃለን።

እኔ በዚህ ሁሉ ምንም ብዥታ የለኝም ። የዚህ ሁሉ መፍቻ ቁልፉ ሕገ መንግስቱን ለሪፎርም አቅርቦ እንዴት ወደ ዘመናዊ የዜጎች ፖለቲካ ሲስተም እንደ ምንሄድ እንመካከር የሚል ሃሳብ ሲያነሱ ብቻ ነው ብርሃን የሚፈነጥቀው ። እስከዚያ የኛ ሃላፊነት ድመቷን ድመት ብለን መጥራት ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 42909
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by Horus » 11 Mar 2022, 11:39

ኢትዮጵያን በጎሳ የሚከፋፍል ሕገ መንግስትና መንግስት ባለበት አገር አንድ ወጥ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ብልጽግና ይኖራል ማለት በምድርና መልካምድር መሃል ያለውን ትስስር አለ ማወቅ ነው ። ባንድ ቃል ባሜሪካ ካርታ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመዘዋወር መሞከር ነው ። ምድሩና ካርታው አንድ ካልሆኑ ካርታው ዋጋ የለውም።

ብልጽግና ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያ የሚል ቃል እንኳ በስሙ ላይ የለም ። ሌላው ቀርቶ እራሱን የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ብሎ የማይጠራ ድርጅት ነው ።

አሁን አራት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ እweስናለሁ ብለዋል፤ ( የሰላም መጥፋት፣ የኑሮ ውድነት/ድህንት፣ የተደራጀ 1 ሚሊዮን የፓርቲ አባላት ሌብነት እና አገሪቱን ያፈረሰው የዘር ክፍፍልና የዘር ፖለቲካ) በአንድ ቃል ይህ ድርጅት ከመፍረስ የሚያድነው የጎሳ ፖለቲካ ማጥፊያ አጀንዳ ሲያቀርብ ብቻ ነው ።

viewtopic.php?f=2&t=291128&sid=67478083 ... ddc7df2b89

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by kibramlak » 11 Mar 2022, 13:52

Horus wrote:
11 Mar 2022, 11:39
ኢትዮጵያን በጎሳ የሚከፋፍል ሕገ መንግስትና መንግስት ባለበት አገር አንድ ወጥ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ብልጽግና ይኖራል ማለት በምድርና መልካምድር መሃል ያለውን ትስስር አለ ማወቅ ነው ። ባንድ ቃል ባሜሪካ ካርታ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመዘዋወር መሞከር ነው ። ምድሩና ካርታው አንድ ካልሆኑ ካርታው ዋጋ የለውም።

ብልጽግና ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያ የሚል ቃል እንኳ በስሙ ላይ የለም ። ሌላው ቀርቶ እራሱን የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ብሎ የማይጠራ ድርጅት ነው ።

አሁን አራት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ እweስናለሁ ብለዋል፤ ( የሰላም መጥፋት፣ የኑሮ ውድነት/ድህንት፣ የተደራጀ 1 ሚሊዮን የፓርቲ አባላት ሌብነት እና አገሪቱን ያፈረሰው የዘር ክፍፍልና የዘር ፖለቲካ) በአንድ ቃል ይህ ድርጅት ከመፍረስ የሚያድነው የጎሳ ፖለቲካ ማጥፊያ አጀንዳ ሲያቀርብ ብቻ ነው ።

viewtopic.php?f=2&t=291128&sid=67478083 ... ddc7df2b89
የኦሮሞ ጎሰኞች ኢትዮጵያ እሚል ቃል እንዲኖር ስላልፈለጉ ይመስለኛል፣፣ ይህ የሚያመለክትህ የኦሮሞ ጎሰኞች ለኦሮሙማ እንጅ ለኢትዮጵያ ሰርተውም አለማወቃቸውን ነው (በስም ከመጠቀም ውጭ)፣፣ አዲሳባ የኦሮምያ ናት እያሉ በአደባባይ የሚለፈልፉ ጀንፎዎች በተዘዋዋሪ ፀረ ኢትዮጵያ እንደሆኑ መናገራቸውን እንኳን የተገነዘቡ አይመስልም፣፣ ለአንድ ሀገር የቆመ የአንድን ሀገር ዋና ከተማ ካልወሰድኩ ቢባል በኢትዮጵያ ብቻ መሆን አለበት፣፣

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by Za-Ilmaknun » 11 Mar 2022, 14:54

(7) ፓርቲው ለምንድን ነው አንድነት የሌለው? የኢትዮጵያ አጀንዳ ሳይሆን የጎሳና የግል ጥቅመኞች ስብስብ ስለሆነ ነው ፤ አባላቱ የጎሳ እንጂ የኢትዮጵያ ወኪሎች አይደሉም ።

Hopefully it won't take another 30 years to change this :mrgreen:

Abere
Senior Member
Posts: 15496
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by Abere » 11 Mar 2022, 15:21

ብልጽግና ማለት ጎሳ ነው፥ ጎሳ ማለት ደግሞ ብልጽግና ነው። ብልጽግና የጎሳዎች ንዑስ ስብስብ ነው። ለምሳሌ የኦነግ አንዱ ስውር ስያሜ የሆነው ኦደፓ-ብልጽግና ሙሉ በሙሉ ራዕዩ ኦሮሞ መሆን ብቻ ነው - ማንኛውንም የማጭበርበርያ ዘደ ተጠቅሞ ቢችል ሌሎች ጎሳዎችን ቁማር በልቶ መኖር ነው እንጅ አገራዊ እና ህዝባዊ አጀንዳ ወይም ራዕይ የለውም። ሰውን በሰውነቱ በመመልከት ብቻ ሁሉን ዜጋ ሊያሳትፍ የሚችል ርዕዮት የለውም። የመጨረሻው የፓለቲካ ራዕይ ማማ አባ ገዳ መሆን ነው። ሌሎችም እንድሁ ነው። The question is not about the PP party, because PP is inherently a tribal party. It should be how can ban tribal parties in Ethiopia including PP itself first. A lot of innocent people thinks enlisting as an opposition party and working with the PP by advocating ideology based political party will change the country. But this is very unlikely. It is like pouring liquid into a container so that it will take after the shape of that container. There are 9 or 10 ethnic regions and it impossible to give a big shock and demolish them by abiding PP- ethnic constitution. There has to be a revolution coming from outside of the customary so-called opposition parties that shatters these ethnic apartheid regions and trash the illegal constitution. Ethiopia needs a radical change. Don't waste your time by either praising or condemning PP. It should be dissolved, if possible peacefully. My prayer is all about how dissolving all these ethnic thug parties peacefully.

Horus
Senior Member+
Posts: 42909
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by Horus » 11 Mar 2022, 15:32

የብልጽግና ፕሬዝዳንት አቢይ አህመድ በመክፈቻ ንግግሩ ፓርቲው 11 ሚሊዮን አባላት አሉት አለ። ትላንት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያባላት ቁጥር 10.1 ሚሊዮን ነው ብላ ነበር። ወያኔ 7 ሚሊዮን ነብረው ተባለ ።

የዚህ ቁጥር ትርጉም ምንድን ነው?
(1) የብልጽግና አባል መሆን ብቸኛው የመንግስት ስራ ማግኛ መንገድ ፣ ጉቦ መብሊያ፣ መስረቂያ ዘዴ ስለሆነ ሰው ሁሉ ቢመዘገብ ምን ያስገርማል? ይህ 11 ሚሊዮን ሁሉ አንድም የኢኮኖሚ ቫልዩ ሳያመርት የቢሮ ከበርቴ የሆነ ሕዝብ ነው ። በዚህ ቁጠር እንኳ ሄደን ያገሪቱ ሕዝብ 10% የቢሮ ከበርቴ መሆኑን እናረጋግጣለን ።

(2) እነ አቢይ አህመድ በ11 ሚሊዮን የቢሮ ከበርቴ ሁሉን ነገር መቆጣጠራቸውን እንጂ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ራሽናል ቢሮክራሲ በሕግኛ ደምብ የሚመራ ግዙፍ የተቋም ባህል በሌለበት አገር የፓርቲ አባል መብዛት ዋናው የሌብነት እና የዝርክርክነት፣ የድርጅታዊና የማኔጅመንት ቀውስ ምንጭ እንደ ሆነ አላወቀውም ። ዝም ብላችሁ ጠብቁ የሚቀጥለው የ6 ወር ግምገማ ይህን የምለውን ይዞ ብቅ ይላል።

(3) አላማውን ተግባራዊ ማድረግ ያቃተው ያፈጻጸም መሰረታዊ ችግር ያለው ድርጅት ውህደት፣ የችሎታ ስልጠና እና የአላማ አንድነት እንጂ መፍትሄው ያባላት ቁጥር ማጋበስ አይደለም ! ውጤቱን ጠብቁ !

Horus
Senior Member+
Posts: 42909
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት እስካለ ድረስ 'ብልጽግና' በፍጹም አንድ ፓርቲ ሊሆን አይችልም

Post by Horus » 11 Mar 2022, 16:59

ደረጀ ሃብተወልድ ፈራ ተባ እያለ ምን እየነገረን ነው?

Post Reply