(1) አንድ ኢትዮጵያዊ እሴት/ ቫልዩ ሊኖረው አይችልም፤
(2) አንድ የኢትዮጵያ አጀንዳ ሊኖረው አይችልም፤
(3) አንድ የሚያደርግ የፖለቲካ ፍልስፍና፣ ርዕዮት፣ ንድፈ ሃሳብ ሊኖረው አይችልም፤
(4) አንድ ሚሽን/ተልዕኮ ሊኖረው አይችልም፤
(5) አንድ ግብ፣ እስትራተጂና ስነምግባር ሊኖረው አይችልም፤
(6) አንድ ውሁድ ፓርቲ ሊያደራጅ አይችልም፤
(7) ብልጽግና የጎሳ ቡድኖች ግምባር እንጂ ውሁድ ፓርቲ አይደለም፤
(8) ብልጽግና አንድ ወጥ ውሁድ ፓርቲ የሚያደርገው ሕጎችና ደምቦች ሊኖሩት አይችልም፤
(9) ስለሆነም የፓርቲውን ስራዎች ማስፈጸም አይችልም ። ብልጽግና ብሄራዊ አጀንዳ ፐርፎርም ማድረግ አይችልም፤
(10) የጎሳ ፖለቲካ ስርዓት ፈርሶ በግለሰቦች አባልነት እስካልቆመ ድረስ ብልጽግና ማለት የጎሳ ናኡስ ከበርቴና የጎሳ የቢሮ ከበርቴ መሬት መነገጃ፣ ባጀት መዝረፊያ፣ ጉቦ መሰብሰቢያ ኢመደበኛ የጎሳ ካርቴል ሆኖ ይቀጥላል ።