Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hellen
Member
Posts: 246
Joined: 09 Oct 2019, 11:06

በአፋር ክልል ህዝቡ ወደ ጦርሜዳ እንዲዘምት ክተት ታወጀ

Post by Hellen » 03 Nov 2021, 08:51

የአፋር ክልል ነዋሪ ያለውን ማንኛውንም የነፍስ ወከፍ መሣሪያ በመያዝ እንዲዘምት ጥሪ ቀረበ
**************
ሁሉም የክልሉ ነዋሪ ያለዉን ማናቸዉንም የነፍስ ወከፍ መሣሪያና ትጥቅ እንዲሁም ተያያዥ ግብዓቶች በመጠቀም ከልዩ ኃይሉና መከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሠለፍ ሕዝቡ ከተደቀነበት አደጋ እንዲታደግ የአፋር ክልል ጥሪ አቀረበ።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሳሰቡት፤ የክልሉ ሕዝብ ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለመበተን የሚንቀሳቀሰውን ወራሪ ቡድን መግታት ይጠበቅበታል።
አሸባሪ ቡድኑ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ለመግባት ቢሞክርም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ በወረራ ከያዛቸዉ አካባቢዎች መባረሩን ገልጸዋል።
ቡድኑ በወረራ ይዟቸዉ በነበሩ አካባቢዎች መሠረተ ልማቶች በማዉደም ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ንፁሐንን በግፍ መጨፍጨፉን አስታውሰዋል።
ይህንን የቡድኑን ጸያፍና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ታሪክ በነውርነቱ የሚያስታውሰው ጥቁር ጠባሳ መሆኑን ገልጸዋል።

24/02/2014

ጠቃሚ የጤና ትምህርት
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ