**************
ሁሉም የክልሉ ነዋሪ ያለዉን ማናቸዉንም የነፍስ ወከፍ መሣሪያና ትጥቅ እንዲሁም ተያያዥ ግብዓቶች በመጠቀም ከልዩ ኃይሉና መከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሠለፍ ሕዝቡ ከተደቀነበት አደጋ እንዲታደግ የአፋር ክልል ጥሪ አቀረበ።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሳሰቡት፤ የክልሉ ሕዝብ ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለመበተን የሚንቀሳቀሰውን ወራሪ ቡድን መግታት ይጠበቅበታል።
አሸባሪ ቡድኑ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ለመግባት ቢሞክርም አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ በወረራ ከያዛቸዉ አካባቢዎች መባረሩን ገልጸዋል።
ቡድኑ በወረራ ይዟቸዉ በነበሩ አካባቢዎች መሠረተ ልማቶች በማዉደም ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ንፁሐንን በግፍ መጨፍጨፉን አስታውሰዋል።
ይህንን የቡድኑን ጸያፍና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ታሪክ በነውርነቱ የሚያስታውሰው ጥቁር ጠባሳ መሆኑን ገልጸዋል።
24/02/2014
ጠቃሚ የጤና ትምህርት
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ