Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጎሳ ወይስ የዜጋ ፌዴሬሽን ?፤ የፓርቲዎች አሰላለፍ ግልጽ እየሆነ ነው ? አንድም ታሪካዊ ተልዕኮ የሌላቸው የጎሳ ስልጣን ነጋዴዎች ቀውስ !!!!

Post by Horus » 09 Jan 2020, 14:27

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአንድ ሺ አንድ ቃላት ይተረካል እንጂ በመሰረቱ ያሉት ፖለቲካዎች ሁለት ናቸው ፤ አንዱ የዜጋ ፖለቲካ ነው ፣ ሌላው የጎሳ ፖለቲካ ነው ። በዚህ መሰረት

እስከ ዛሬ ውጥንቅጡ የወጣው ወስብስቡ የፓርቲዎች ብዛትና አሰላለፍ ቀስ በቀስ ቅርጽ መያዝ ጀምሯል ።

አንድ፣
በጎሳ ክልሎች ላይ ቆሞ ዜግነትን አስከብራለሁ የሚለው ያቢይ ፓርቲ ብልጽግና ይባላል።

ሁለት፣
በዜግነት ላይ ቆሞ የጎሳ መብት አስከብራለሁ የሚለው ፓርቲ ኢዜማ ይባላል።

የጎሳ ፌዴሬሽን ወይም የጎሳ ፖለቲካ አክራሪዎች በሶስት ተመድበው፣
የኦሮሞች ጥምረት በነጃዋር መራራ እየቆመ ነው ።
የአማሮች ጥምረት በነአብን ይልቃል እየቆመ ነው።
የትግሬዎች ጥምረት በነእወሃት እየቆመ ነው ።

ሌሎች ጥቃቅኖቹ አንድ ሌላ ዜጋ ነክ ጥምረት ለያቆሙ ይችላሉ ።

ይህ ነው እየጎላ ያለው ስ እ ል !!!


Last edited by Horus on 10 Jan 2020, 02:06, edited 8 times in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ወይስ የዜጋ ፌዴሬሽን ?፤ የፓርቲዎች አሰላለፍ ግልጽ እየሆነ ነው

Post by Horus » 10 Jan 2020, 01:35

በአሮጌ ፎርሙላ ላይ የቆመው የጎሳ አጀንዳ በትልቁ ነው የሚሸነፈው ማለትም በሚቀጥለው ግንቦት ። በእርግጠኝነት ፉክክሩ በብልጽ ኛ እና በኢዜማ መካከል ነው። ለምን ቢባል ለኢትዮጵያ መፍትሄ ፕሮግራም ያላቸው እነዚህ ብቻ ናቸው ።

እርግጥ ነው በመቶ፣ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች፣ ከደብረጽዮን እስከ ልደቱ፣ ከጃዋር እስከ ማርጃሮ ሁሉም ስልጣን ይመኛሉ ።

ህዝቡ ግን አሁንም በዘር ፖለቲካ የደረሰበትን ስቃይና የኑሮ መቃውስ የረሳ አይደለም ።

በግንቦቱ ምርጫ አዲስ ሃሳብና አዲስ መፍትሄ ያቀረቡ ብቻ ናቸው ድምጽ የሚያገኙት ።

ማንም ሰው በግንቦት ምን እንደ ሚሆን የሚተነብይ የለም ።

አሸናፊ የሚሆኑት በመሰረቱ ሰው ምን እንደ ሚፈልግ በውል የሚያቁት እንጂ ነጋ ጠባ በገንዘብና በዘር የሰኩርት አይሆኑም ።

ስለዚህ ትልቅ የፖለቲካ እውቀት ችግር አለብን !!!
Last edited by Horus on 10 Jan 2020, 02:03, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ወይስ የዜጋ ፌዴሬሽን ?፤ የፓርቲዎች አሰላለፍ ግልጽ እየሆነ ነው ? ታሪካዊ ሚና የሌላቸው የጎሳ ስልጣን ነጋዴዎች ቀውስ !!!!

Post by Horus » 10 Jan 2020, 02:02

ጥያቄ አለኝ ?

አንድ የኦሮሞ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ጎሳ ፖለቲከኛ ብልጽግና ከያዘው ፕላን ሌላ ላንድ ኦሮሞ፣ ላንድ አማራ፣ ላንድ ትግሬ የሚፈይደው ምን ነገር አለ? በቃ!!

እነዚህ በሙሉ ተሸናፊ የተበላ እቁብ ናቸው !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 39792
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የጎሳ ወይስ የዜጋ ፌዴሬሽን ?፤ የፓርቲዎች አሰላለፍ ግልጽ እየሆነ ነው ? አንድም ታሪካዊ ተልዕኮ የሌላቸው የጎሳ ስልጣን ነጋዴዎች ቀውስ !!!!

Post by Horus » 10 Jan 2020, 02:47

የጎሳ ፓርቲ ስልጣን ቢወስድ ምን እንደ ሚሰራ ይህን የዎያኔ ትግሬዎች ዘረፋና ባዲሳባ ስላልቸው ፎቆች እየወጣ ያለውን ሃቅ ተከታተሉ !!

ገና ብዙ ጉድ ይዎጣል !!!


Misraq
Senior Member
Posts: 16523
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: የጎሳ ወይስ የዜጋ ፌዴሬሽን ?፤ የፓርቲዎች አሰላለፍ ግልጽ እየሆነ ነው ? አንድም ታሪካዊ ተልዕኮ የሌላቸው የጎሳ ስልጣን ነጋዴዎች ቀውስ !!!!

Post by Misraq » 14 Oct 2025, 01:21

ሁሬሳ ግንቦት ሰባት ውስጥ ሆኖ የአማራን ኪስ በሚያወልቅበት ወቅት የከተበው። አማራ የዜጋ ሌቦችን ወግዱልኝ ካለ በኋል ድርቀት የመታቸው በሙሉ ብልፅግና ውስጥ ለተላላኪነት ገብተዋል። ሁሬሳን ጨምሮ

Post Reply