ጉባኤው ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ከኣዲስ ኣበባ የተጠሩ ብዙ ተሳታፊዎች የሚገኙበት መሆኑ ብቻ ሲሆን ይህም የለውጥ ሃይሉ የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ በቅርብ ግዜ ቅስቀሳ ለመጀመር በመወሰኑና ለዚህም ኣዲስ ኣበባ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንደሚጀምር በመታወቁ የኣዲስ ኣበባው ግንባር የለውጥ ሃይሉን እንዳይደግፍ ለማግባባትና ትግራይ ውስጥ ያለው ካድሬም እንዳይከፊፈል በከባድ ለማስጠንቀቅ ያለመ ነው።
ጨዋታው ያለቀ ቢሆንም ቅሉ መልካምን መመኘት ባህላችን በመሆኑ እስኪ ይቅናቹ እንበላቸው"
