Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42875
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የሲዳማ ውጤት፤ ሞኝ ከራሱ ስህተት፣ ብልህ ከሌላው ስህተት ይማራል

Post by Horus » 23 Nov 2019, 15:02

አሁን ሲዳማ ክልል ነው፤ ከዚያስ? የዚህ ውጤት ፋይዳው ምንድን ነው?

አንድ፣ አዋሳ ከተማ አንዷ የኢትዮጵያ ትልቋ ከተማ ከመባል የሲዳማ ከተማ ስለምትባል፣ የሲዳማ ገዢ መደብ ንብረት ስለምትሆን ከውጭ የምታገኘው የሌሎች ባለሃብቶች እምነትና ኢንቨስትመንት እየቀነሰ እንጂ እያደገ አይሄድም።

ሁለት፣ የሲዳማ ውጤት በደቡብ 54 ጎሳዎች መካከል ከፍተኛ የስልጣን፣ የእድገት፣ የባጀት፣ የትምህርት፣ የሰው ሃይል ፉክክር ስላስነሳ አዋሳም ሆነ ሲዳማ ያገኙት የነበረው ተፈላጊነት፣ ታማኝነት፣ የበጀትና ሪሶርስ ድርሻ እጅጉን ይቀንሳል ።

ሶስት፣ የሲዳማ ክልል መሆን ከሳይኮሎጂ እርካታ ያለፈ የኢኮኖሚም ሆነ ሌላ የእድገት ጥቅም ስለማያስከትል የህዝቡን የስራ፣ ትምህርት፣ ጤና (ዋናው የፖለቲካ አላማ) ጉዳዮችን ሊፈታ አይችልም ። እንዲያውም በሲዳማ ዉስጣዊ ገዦች መካከል ያለውን መዛረፍና ፉክቻን ኣብሶ የላቀ ኮራብሽን ያመጣል ።

አራት፣ ሲዳማ ክልል የሆነው ክልልነት ወረት በነበረበትና የመዝረፊያ፣ የመክበሪያ ዘዴ በነበረበት በዘመነ ዎያኔ ሳይሆን ፣ ክልልነት እየከሸፈ፣ እየተጠላ ውህደትና ኢንተገሬሽን እየገነነ ባለበት ሰአት ስለሆነ፣ ነገሩ ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮሀ እንደሚባለው ነው።

አምስት፣ ከዚህ በኋላ ሲዳማ ካቅመ አዳም ደርሶ ትዳር የወጣ ጎልማሳ ስለሆነ አለማም አጠፋም፣ ከበረም ደሀየም ሃላፊው፣ ተጠያቂው ራሱ የሲዳማ ገዢና ህዝብ ነው ሚሆኑት ።

ስድስት ፣ ስለሆነም ለቀሩት 53 ጎሳዎች ሲዳማ ትልቅ መማሪያ ጊኒ ፒግ ወይም ቤተ ሙከራ ይሆናል ። ክልልነት የእድገትና ብልጽኛ ቅጽበታዊ ማጂክ አይደለም ። ለደጉም ለክፉም መዘዙን በቅርብ የምናየው ይሆናል ።

ያዋሳ የሲዳማ ዋና ከተማ መሆን ለሊሎች እንደ አርባ ምንጭ፣ ወልቂጤ እዘተ ለመሳሰሉ ከተሞች መግነን መር መክፈቱ ግድ ነው።

ፖለቲካና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንደ ከረምቦላ ጨዋታ ነው ። አንዱ ጠጠር ሲመታ የቀሩት ጠጠሮች ሁሉ ይነቃነቃሉ ። የሁሉም ቦታና ሁኔታ ይናጋል፣ ይለወጣል ።