Mereja.Forum
Skip to content
Search
Advanced search
Quick links
Unanswered topics
Active topics
Search
The team
FAQ
Login
Board index
Ethiopian News & Opinion
Search
Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Email topic
Print view
1 post • Page
1
of
1
Ejersa
Member
Posts:
3978
Joined:
05 Nov 2019, 10:39
የኢህአዴግን ውህደት የሚቃወሙት እነማን ናቸው? Abeba Tekalign
Report this post
Quote
Post
by
Ejersa
»
07 Nov 2019, 19:32
የኢህአዴግን ውህደት የሚቃወሙ ስልጣናቸውን በብቃት፣ በአቅም እና ለህዝብ ባላቸው ተቀባይነት አግኝተነዋል ብለው የማያምኑ፣ ውህደት ከመጣ ብቃት መመዘኛ ስለሚሆን ስልጣኔን አጣለሁ የሚል ስጋት ያለባቸው ነው ፡፡
የኢህአዴግ የውህደት ሃሳብ አሁን የመጣ አይደለም፡፡ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ጉባኤ በተዘጋጀባቸው መድረኮች ሁሉ ሲነሳ የነበረ ነው፡፡ በወቅቱ “ጊዜው ገና ነው” ከማለት ውጪ ውህደት አያስፈልግም የሚል ተቃውሞ ተነስቶ አያውቅም፡፡
እንደአሁኑ ፌዴራሊዝምን ይደፍቃል፣ ይጨፈልቃል የሚል ሃሳብ አልነበረም፡፡
“አሁን ውህደቱን የሚቃወሙ እና በጥርጣሬ የሚያዩ ፓርቲዎች በፊት ውህደቱን ይደግፉት ነበር ።
የውህደቱ ተቃዋሚዎች በብቃት፣ በአቅም እና ለህዝብ ባላቸው ተቀባይነት ስልጣን አለማግኘታቸው የሚያሳስባቸው ናቸው፡፡
ብዙ የፌዴራል አገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየው አንድ ፓርቲ በምርጫ ተፎካክሮ ካሸነፈ በፌዴራል ሥርዓት ስር ያሉ የክልል መንግስታትንም ያስተዳድራል።
የኢህአዴግ ውህደት አሃዳዊ ሥርዓትን ያመጣል፤ ብዝሀነትን ይጨፈልቃል የሚለው ስጋት ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ አንጻር አብሮ የሚሄድ አይደለም፤ ተቀባይነትም የለውም።
ኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ሲሆን በየክልል መንግስታት ውስጥ ቅርጫፎች ይኖሩታል።
ውህደቱ ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩን ያሰፋል እንጂ አሃዳዊ ሥርዓት የሚያመጣ አይደለም ።
በሌላ በኩል ኢህአዴግ አምስቱ አጋር የሚላቸውን ፓርቲዎች በምንም ሚዛንና ምክንያት ያልተወያዩባቸውን ፖሊሲዎች እንዲፈጸሙ ግዴታ እንደሚጥልባቸው ገልጸው ይህ አካሄድ ኢህአዴግ አግላይ ድርጅት እንደሆነ ያሳያል ብለዋል።
በዚህም የተነሳ አጋር ፓርቲዎችን በአገሪቱ ጉዳይ ላይ ተሳታፊ ለማድረግ በውህደቱ እንዲካተቱ ማድረግ አስፈላጊና ተገቢም ነው ።
Top
Post Reply
Email topic
Print view
1 post • Page
1
of
1
Return to “Ethiopian News & Opinion”
Jump to
Ethiopian News & Opinion
Open Forum