Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

በባሌ ጥቃት አድራሾች እንመለሳለን በማለታቸው መንግሥት በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ!

Post by Hameddibewoyane » 28 Oct 2019, 00:24

ሰሞኑን ጥቃት ለመድገም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ፍርሃት የነገሰ ቢሆንም አዳማ/ናዝሬት ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈጸም በድብቅ ጥቃት አድራሾችን ወደ ከተማው የሚያስገቡ የጽንፈኛው አደራጆች አሉ የሚል ስጋት ያለ ሲሆን በባሌ ሮቤ በግልጽ አርብ እለት ጥቃት አድራሾች ሰኞ ተመልሰው ለመምጣት ያቀረቡትን ዛቻ መንግስት በቀላሉ እንዳያየው የመብት ተሟጋቹ ተቁዋም ጠይቁዋል።
ያንብቡት ሼር ያድርጉት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ

አስችኳይ መግለጫ 27 October 2019

አስቀድሞ ማስጠንቀቅ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ

በባሌ ሮቤ ባለፈው አርብ እለት በግልጽ በጥቃት አድራሾቹ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት ከሰኞ ጀምሮ ሊያካሂዱት ያስታወቁትን የጅምላ ጭፍጨፋ እንዳይፈጸም መንግስት የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት።

በዛሬው ቀን እሁድ ጭምር ዜጎች ሃይማኖት እና ዘር ተኮር ሃይማኖትን መሰረት ያደረገን በህይወታቸው ላይ ያነጣጠረን ጥቃት በመፍራት በቤተክርስቲያን ተጠልለው ይገኛሉ የተቀሩት ቤታቸውን ቆልፈው በጭንቀት እያሳለፉ ነው። ለድረሱልን የስልክ ግንኙነት ለማድረግ ለመደውል ስልካቸውን ብዙዎቹ መሙላት አልቻሉም ሱቆች ዝግ ናቸው።

ጥቃት አድራሾቹ ከሌላ አካባቢ እንዲሁም ከአካባቢው ለመጡ ሽማግሌዎች ለሰላም የአሻፈረኝ መልስ ነው የሰጡት።

በባሌ ሮቤ በዚህ ሳምንት ባለፉት ቀናት በነዋሪዎች ላይ ዘር እና ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ ተካሄጿል።
በአካባቢው የገባው የጥበቃ ሃይል በቁጥር ከጥቃት አድራሾቹ በትጥቅም በቁጥርም በጣም ስለሚያንስ
ስጋቱ ጨምሮዋል።

ይህንን በባሌ ሮቤ በጥቃት አድራሾች አርብ ዕለት ማስጠንቀቂያ የተሰጠበትን የሰኞ እንመለሳለን ቀጣይ ዘር እና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ እንዳይካሄድ የዜጎች ህይወት እንዳይጠፋ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን አስቀድሞ ማስጠንቀቅ ተቀብሎ ከግምት በማስገባት የዜጎችን ህይወት ለመታደግ እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ

ሥዩም ሀብተማሪያም

ጀርመን

Ethiopia Human Rights Committee
Tel.: + 49 160 43 57 232
E-Mail: [email protected]
Germany