Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39972
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የመደመር ድክመት፤ አማራና ኦሮሞ እኩል ስልጣን ከተከፋፈሉ የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ይፈታል የሚሉ መሃይሞች ናቸው ! ማንኛው ጎሳ የበላይ ያለሆነበት ኢትዮጵያ ነው ሚሰራው በቃ !

Post by Horus » 22 Oct 2019, 00:36

ኦሮሞ መደመርን ከገዳ ጋር ሊያያዝ ይሰብካል። ይህ ደሞ ራሱ መሃይምነት እንጂ ኢትዮጵያዊነት አይደለም ። የኢትዮጵያን ችግር አይፈታም ።

መደመር የብልጽግና ፓርቲ ር ርዮትና እስትራተጂ ነው እንጂ ምንም አይደለም ። ፓርቲው የራሱን ሃሳብ ለኢትዮጵያ ማቅረቡ በጣም ጥሩ ነው።

ግን ኢትዮጵያ ዛሬ እስከ ዛሬ ያልነበረ አዲስ ቲኦሪ ፈጠረች የሚሉ ካሉ መሃይሞች ናቸው።

ለምሳሌ አቢይ ስለ አገር በቀል ሃሳብ ብዙ ብሏል ። ግን እስከ ዛሬ አንድም የ84ቱ ባልላዊ ሰርአቶች እንዴት መደምር ውስጥ እንደገቡ ተናግሮ አያቅም ። ገዳን ግን ጠቅሷል ! ይህ ነው እጅግ አሳሳቢ ነገር !!! መደመር የገዳ መስበኪያ እንዳይሆን ማለት ነው !!

መደመር ጥሩ የፖለቲካ እስትራተጂ ነው ! በቃ !!! አቢይ ህሳቡን ባግባብ ለሕዝቡ ማቅረብ እንጂ እንደ ማኦ፤ እንደ ኪም ኢል ሱንግ ጣኦታዊ ከልት ምልክት እስኪሆን ዝም ብሎ ማየቱ ግዙፍ ስህተት ነው ። እውቀትና ስክነት በሌለበት ቲፎዝች ብዙ ናቸው ። መሪዎችም ቀስ በቅስ ሲመለኩ ይጣፍጣቸዋል ፣ ስልጣን ያባልጋል፣ ፍጹም ስልጣን ፈጽሞ ያባልጋል ። ይብቃ !!!

ያቢይ ስህተት ማለትም ብዙ ነገር በትክክል እየሰራ እያለ ቢሆንም ማለት ነው። ስለመደመር ሲያስተምር ከገዳ ስራት ራቅ ብሎ መቆም ነበረበት ። ገዳና ዘመናዊ ፖለቲካ አደባልቆ መናገር ወይ አጉል ስብከት ወይም ሰው መናቅ ነው።

ያማራና የኦሮሞ ፖለቲኮስ ህሳቤም እንዲሁ ። አማራና ኦሮሞ ለስልጣን ሌት ተቀን እንደ ሚፏከቱ ሁሉም ያቃል። ስለሆነም አቢይ ከጅምሩ ይህን ማየት አለበት ። አማራም እንዱሁ ። ግን ሁለቱ የህን እርስ በርሳቸው ለራሳቸው ሃይል ሲፏከቱ ሌላው ዳር ላይ ቆሞ ለነሱ እንዲያጨበጭብ ይሻሉ ። ይህ ድንቁርና ነው።

ስለዚህ አቢይ ይህን ቀስቅሶ ያንን ማሸንፍ ሳይሆን፣ አማራም ይህን ቀስቅሶ ያንን ስልጣን ከኦሮሞ ለመጋራት ሳይሆን ለዚች አገር አንድ ስርአት ለመፍጠር መሻት አለባቸው ። አለያ ምንም አይመጣም፣ ማንም ምንግዜም አያሸንፍም ። አትልፉ !!!!
Last edited by Horus on 22 Oct 2019, 02:26, edited 3 times in total.


TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የመደመር ድክመት፤ አማራና ኦሮሞ እኩል ስልጣን ከተከፋፈሉ የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ይፈታል የሚሉ መሃይሞች ናቸው ! ማንኛው ጎሳ የበላይ ያለሆነበት ኢትዮጵያ ነው ሚሰራው በቃ !

Post by TGAA » 22 Oct 2019, 01:48

የኦዲፒ በአሁኑ ሰአት በአብዛኛው በነጀዋር ስር ወድቋል ፡፡ የቄሮን አስተባብሮ ህግ እንዲጥስም የሚያደርገው ኦዲፒ ነው፡፡ አሁን እንደሚሰማውም ከሆነ ለማ መገርሳ ሳይቀር የመከላከያ ሚኒስተር ሆኖም የሚደረገውን ሁሉ እያወቀ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥቧል ወይም ህግ እየተጣሰ ንግድም ሆነ ነጻ ዝውውር እንዳኖር እያደረገ ያለው በኦዲፒ ከለላ የሚሰጠው የጀዋር ቄሮ መሆኑ እየታወቀ ሀገሪቱ በሜጫና በቀጠና እንዲተዳደር በዝምታ ድጋፋቸውን እያደረጉ ነው የሚገኙት ፤ ህዝቡ እራሱን ለመከላከል መዘጋጀት አለበት ፤ ኦዲፒ በጣት የሚቆጠሩም ቢሆኑ በህግ በላይነትና በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ሁሉ እራሳቸውን ነጥለው መቆም አለባቸው ፤ ለኦዲፒ ወንጀል ከለላ መስጠታቸውን አቁመው የጀዋርን የውስጥ አርበኞች ማጋለጥ አለባቸው ፤ ተወደደም ተጠላ ይህ የውብድና በኢትዮጵያ ህዝቦች እርምጃ ይሰክናል ፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 39972
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የመደመር ድክመት፤ አማራና ኦሮሞ እኩል ስልጣን ከተከፋፈሉ የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ይፈታል የሚሉ መሃይሞች ናቸው ! ማንኛው ጎሳ የበላይ ያለሆነበት ኢትዮጵያ ነው ሚሰራው በቃ !

Post by Horus » 22 Oct 2019, 02:00

እኔ አማራ አይደለሁም፣ ለአማራ አልሰብክም። ግን አብይ ይህን ሁሉ ሲለ ያማራን የእምነት ሃይል ከመደመር ጋር አለማየቱ የሱን አገር ወለድ ሃሳብ ስብከት ድክመት ፍንትው አርጎ ያሳያል !!!


Horus
Senior Member+
Posts: 39972
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የመደመር ድክመት፤ አማራና ኦሮሞ እኩል ስልጣን ከተከፋፈሉ የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ይፈታል የሚሉ መሃይሞች ናቸው ! ማንኛው ጎሳ የበላይ ያለሆነበት ኢትዮጵያ ነው ሚሰራው በቃ !

Post by Horus » 22 Oct 2019, 02:53

ለምሳሌ አቢይ የኢትዮጵያ መኖር አለመኖር በኢህ አዴግ መፍረስና መኖር አይወሰንም ማለት እጅግ ትክክል ነው።


kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: የመደመር ድክመት፤ አማራና ኦሮሞ እኩል ስልጣን ከተከፋፈሉ የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ይፈታል የሚሉ መሃይሞች ናቸው ! ማንኛው ጎሳ የበላይ ያለሆነበት ኢትዮጵያ ነው ሚሰራው በቃ !

Post by kibramlak » 22 Oct 2019, 06:09

Horus,

I agree with you that his medemer concept (even if its not new) is a replica of a government based on oromo control (embrace) leadership. Unless its made ethnic neutral, its doomed to fail miserably. However, with new administrative map and this medemer idea, tribalists may have difficulties to spew ethnic hatred. On top of that, as Rwanda did, all ethic based calling of any sort must be prohibited by law. Thus, I will see light at the end of the tunnel if at least the following three are combined:
1) medemer (thought based politics)
2) new administrative regions (ethnic neutral)
3) outlaw any reference to ethnic calling of any sort

Horus
Senior Member+
Posts: 39972
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የመደመር ድክመት፤ አማራና ኦሮሞ እኩል ስልጣን ከተከፋፈሉ የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ ይፈታል የሚሉ መሃይሞች ናቸው ! ማንኛው ጎሳ የበላይ ያለሆነበት ኢትዮጵያ ነው ሚሰራው በቃ !

Post by Horus » 22 Oct 2019, 12:22

ክብራምላክ፤

በትክክል። የሃሳብ ፖለቲካ፣ ኢጎሳዊ ክልል እና የጎሳ ፓርቲ ሕገወጥ መሆን ከተረጋገጠ ግማሹ የኢትዮጵያ ችግር ተፈታ ማለት ነው።

ነገር ግን ያሁኑ የጥገና ለውጥ የሚመራው በራሱ በጎሳው ፓርቲና መንግስት ስለሆነ ራሱ ለውጡ የሚለውጠው ለዋጮቹን ነው ። ይህን መሰል ራስን መለወጥ ወይም ራስን መግደል ከባድ ሂደት ነው ። እዚህ ላይ የሚደረበው ሰዎቹ ሁሉ የጎሳ ነጻ አውጪና የዘር አቀንቃኞች ናቸው። ይህ ባለ ሁለት ሰይፍ ችግር ነው ነገሩን ሁሉ ወጥሮ የያዘው ። ይህ ሁሉ መሃል ነው አቢይ መደመር አዲስ አገር በቀል ርእዮት ነው የሚለው ። ይህን ለማለት ቢያንስ አንድ ትልቅ በምርምር እና በኢክስፐርቶች የተቀመረ አስማሚ ከሁኩም ይጎሳም ሆነ ታሪካዊ ያስተዳደር ስርአቶች ተጨምቆ የተቀመረ ሞዴል ማሰራት ነበረበት ።

ባካባቢው ያሉትም ምሁራን ዝም ብለው እሱ ያለው ጀስቲፋይ ከማድረግ እናም ነገሩን ወደ ፕሮፓጋንዳነት ከመሳብ ይልቅ መሰረት ወዳለው ታሪካዊ፣ ፍልስፍናዊ፣ ነድፈ ሃሳባዊ፣ እስትራተጃዊና ተግባራዊ ወጥ የሆነ ህሳቤ ቢያዘነብሉ ነው ላቢይም ለኢትዮጵያም የሚጠቅሙት እለለሁ።

Post Reply