በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ማህበራዊ ፈላስፋ (ሶሺያል ፊሎሶፈር) እንደሌለ ሁሉ አንድም የባህል ሊቅ የለም !
ይህን ለማለት ያስገደደኝ የማነበውና የማየው ሁሉ ወይ የፖለቲካ ብሽሽቅ ወይ ደሞ ሁሉም ነገር የህይል ፉክከር መሳሪያ ለማደግ መሞከር ነው። ባህል ተበልው ሰው የሚንጋጋላቸው ክንውኖች ሁሉ አንድም ሰው ምን እንደ ሆኑ ከሶሺያ ሳይኮልጂም ሆነ ከፖለቲካል ሳይኮሎጂ ጋር አገናዝቦ የሚገጽ ሰው የለም፤ ማለትም ከሚሰለፉት ሁሉ ማለት ነው። እኔ ከማየው አብዛኛው በዘልማድ የሚከወን ጋጋታ እንጂ በውስጡ ይህ ነው ሚባል የእምነት ፍልስፍና፣ ወይ የባህል ዘይቤና ክህሎት ወይ ሌላ ማህበራዊ እሴትም ሆነ ንድፈ ሃሳብ አላይበትም ። እኔ ማየው ዝም ብሎ የፖለቲካ ርኩቻ ነው። ያ ደሞ የሚከናወነው በኢሬቻም በገዳም አይደለም፣ በፖለቲካ አደረጃጀት ነው ።
Re: በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ማህበራዊ ፈላስፋ (ሶሺያል ፊሎሶፈር) እንደሌለ ሁሉ አንድም የባህል ሊቅ የለም !
ለምሳሌ ዛሬ ያይሁት ነገር አለ። ዛፉ ይሳማል፣ መሪቱም ይሳማል ። ይህም ማለት ዛፉ እንደ ቤት እግዚአብሄር ሆኖ የመንፈስ ማደሪያ ነው ማለት ነው ። ያ ከሆነ ደሞ በአሉ ቢያንስ ሃይማኖታዊ በበዛ መንፈሳዊ መሆኑ ነው። ያ ግ ን በተግባር አይታይም ።የሚታየው እንደ መንግስቱ ዘመን የፖሊታከ ወጠጤነት ነው። ማህበራዊ በአል ነው እንዳይባል ደሞ ያደባባይ ተይንት ነው ። ያም ሆነ ያ አንድ እምነትም ሆነ ባህል እውነተኛ ለመሆን ብዙ ዘመን መደጋገም ሳልለበት እና ከጊዜው ጋር እየተከለሰ ስለሚሄድ ለእኔ ይህ ሁሉ የጃዋር እንቶኔ ግርግር ነው ።