"የለማ ቡድን የሚባለው ስብስብ በኦህዴድ/ኦዴፓ በኩል ሃገሬን አስመልሳለሁ ያለውን ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ እምነትም ሳያገኝ፤ ኦዴፓ/ኦህዴድ እንደ ኦነግ ካልሆነ ደስ የማይላቸውን የኦሮሞ ብሄርተኞችንም ሳያስደስት ከሁለት ያጣ ሆኖ ይቀራል፡፡ በዚህ መሃል ያለው ትልቁ አደጋ ሃገራችን ወደማትወጣበት የእርስበርስ እልቂት እና መፈራረስ የማምራት እድሏ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ተበጥብጣ እና ፈርሳ ኦሮሚያ እንደ ገነት በሆነ ሰላም መኖር የምትችል የሚመስላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች ደግሞ ይህ የሚያሳስባቸው ነገር አይደለም፡፡ የራሳቸው ጎሳ ሰዎች የፈደራል "ስልጣን ላይ ወጥተው የሚያደርጉትን ነገር ትቂት ጊዜ ወስዶ ለማየት ትዕግስት የሌላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች ኦሮሞ ስልጣን በያዘ ዘመን ሃገር ፈረሰ የመባሉ የታሪክ ተወቃሽት አማርኛ በኦሮሚያ ክልል ከሶስተኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርትቤቶች ይሰጥ መባሉ የሚያሳስባቸውን ያህል እንኳን ከቁብ የሚያስገቡት ቁምነገር አይመስልም፡፡ እንዲህ ባለው አድሮ ቃሪያ የፖለቲካ አካሄድ ተዋናዮች የገመድ ጉተታ ውስጥ የተሰነቀረው የሃገራችን እጣ ፋንታ ከመቸውም ጊዜ በላይ አሁን አሳሳቢ ነው
በሃገራችን የጎሳ ፖለቲካን በማስኬድ በኩል እድሜ ጠገቡ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ሲሆን ስኬታማው ደግሞ ህወሃት መራሹ የትግሬ ብሄርተኝነት ነው፡፡ማንኛውም የዘውግ ብሄርተኝነት ትግሉን የሚጀምረው አስቀያሚ የጠላት ምስል በመሳል ነው፡፡ የትግሬ እና የኦሮሞ ብሄርተኞች ደግሞ በያሉበት ሆነው የፖለቲካ ሸራቸውን ወጥረው የጠላት ስዕል ስለው ሲጨርሱ የሚመጣው ምስል ተመሳሳይ ነው:- ሰባት ቀንድ ያለው፣ ጨካኝ እና ጨቋኝ የአማራ ምስል! በዚህ የተነሳ ሁለቱም የአማራ የሆነ ነገርን ሁሉ እኩል ይጠላሉም; ይፈራሉም፡፡ ይህ የኦሮሞ እና የትግሬ የጎሳ ፖለቲከኞች ዞረው ዞረው የሚገጥሙበት ሁነኛ መገናኛቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው የኦሮሞ ብሄርተኞች የዛሬ ሳምንት ዘቅዝቆ ገርፎ ጥፍራቸውን ከነቀለው ህወሃት ይልቅ ከዛሬ አንድ መቶ አመት በፊት በኦሮሞ የጦር ጀነራሎች ጭምር ታጅቦ ግዛት ለማስፋፋት የዘመተው ምኒሊክ የበለጠ ክፉ መስሎ የሚታያቸው፡፡
የኦሮሞ ብሄርተኞች በህወሃት ላይ አንጀታቸው አይጠናም፡፡ ተገላቢጦሹ ግን ለህወሃት አይሰራም፡፡ህወሃት ከስልጣን አምሮቱ በተቃራኒ ቆሞ፣ የማይፈልገውን ሲሰራ ላገኘው ኦሮሞ ቀርቶ ትግሬም የሚራራ አንጀት፣ ይቅር የሚል ልብ የለውም፡፡ተገልብጦ መገረፍ ያለበት የበላው በአፉ እስኪመጣ ተዘቅዝቆ ይገረፋል፣ ጥፍሩ መነቀል ያለበት ይነቀላል፣ ጀርባው መተልተል ያለበት ይተለተላል-ህወሃት እንዲህ ነው! ለኦሮሞ ብሄርተኞች ግን ዋናቸው አማራን በመጥላት መተባበሩ ላይ ነው፡፡ ከዛ በመለስ ላለው ነገር ቂም የለም!በማዕከላዊ፣ በዝዋይ፣ በሸዋሮቢ፣ በቂሊንጦ እስርቤት የተደረገባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ አማራን ለማሸመድመድ በሚደረገው ትብብር ያካክሱና የበደል እዳ ይሰርዛሉ፡፡ ከእነሱ ጋር የማይሰረዝ የበደል ዕዳ ያለበት “ባለ ሰባት ቀንዱ አማራ” ብቻ ነው፡፡ ይህ ነገር ለትግራይ መራሹ ባልንጀራቸው ህወሃት አይሰራም"
https://ethiothinkthank.com/2019/09/06/ ... -it-poses/
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: "የኦሮሞ ብሄርተኞች በህወሃት ላይ አንጀታቸው አይጠናም.."
"ህወሃት ዘረፋውን ህጋዊ የሚያደርግበትን ስልጣኑን እስካልተጋፋው ድረስ ሰባት ቀንድ አድርጎት ከኖረው አማራው ጋርም ቢሆን ተባብሮ የበላይነቱን የማፅናቱ ትርጉም ያለው ስራ ላይ ይበረታል፡፡ ለዚህ እማኝ መጥራት ካስፈለገ የህወሃቱ አቶ መለስ ሌላው ቀርቶ ከገዛ የጎሳ መሰሎቻቸው ህወሃቶች ዘንድ የተጋረጠባቸውን የመሰንጠቅ አደጋ ለማምለጥ አማሮቹን ብአዴኖች ብርቱ ምርኩዝ አድርገው ነበር፡፡አቶ መለስ ይህን አደጋ ለማምለጥ በህወሃት ስብሰባ ውስጥ በአዴኖችን እንደ ህወሃት አባል ስብሰባ ውስጥ አስገብተው እስከማስቆጠር የሚደርስ አይን አውጣ አካሄድ ሄደው እንደነበር የስንጥቃቱ ተሸናፊ ቡድን ፊት አውራሪ አቶ ገብሩ አስራት በአንድያ መፅሃፋቸው ገልፀውታል፡፡
አማራን በመጥላቱ ረገድ የኦሮሞ እና የትግሬ ብሄርተኞች ተመሳሳይ ውስጣዊ ባህሪ ቢኖራቸውም ከኦሮሞዎቹ በተለየ የህወሃቶች ፍላጎታቸውን የማስፈፀም ስትራቴጅ ቆሞ ቀር አይደለም፡፡አስፈላጊ ሲሆን ራሱን አማራን ተጠቅመው አማራውን ለመቅበር ይሰራሉ፡፡ ይህ ከትጥቅ ትግሉ ዘመን ጀምሮ ባደረጉት የስትራቴጅ ለውጥ የሚመሳከር ሃቅ ነው፡፡ ትጥቅ ትግሉን ሲጀምሩ ለትግራይ ዝናብ አጠርነት ሳይቀር አማራውን ሊወቅስ የሚቃጣው ማኒፌስቶ ፅፈው፣ አማራ ባለበት ሃገር ትግራይ አትኖርም ብለው ትግራይን ሊገነጥሉ ተዋጉ፡፡ በኋላ ትግራይን በሙሉ ከደርግ ነፃ ምድር አድርገው የመገንጠሉን ነገር ሲያስቡት የትግራይ ብቻ ጌታ ከመሆን ይልቅ የኢትዮጵያ ጌታ ቢሆኑ የተሻለ የጌትነት ትርጉም እንደሚሰጥ ተረድተው ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ሆነ፡፡"
ይህ ጉዞ የሚደረገው ደግሞ “የባለ ሰባት ቀንዱን” አማራ ደጃፍ እያለፉ ብቻ መሆኑን ስለተረዱ ተረካቸውን ቀየሩ፡፡ አማራ ሲሉ ድፍን አድርገው ጠላት ያደረጉትን አማራ ሸንሽኖ በተለያየ ቅርጫት የሚያስቀምጥ ተረክ አመጡ፡፡ አዲስ አበባ እስኪደርሱ ሶስት አይነት የአማራ አመዳደብ አመጡ፡፡ አንደኛው ጭቁን አማራ እና የአማራ ገዥ መደብ የሚል ነበር፡፡ ቀጣዩ ደግሞ የአማራ ጨቋኝ መደብ መፀነሻው የሸዋ አማራ እና ሌላው አማራ የሚል ሆነ፡፡ የመጨረሻው ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነትን የሚቀበል ተራማጅ አማራ (ለህወሃት ጌትነት አጎንባሽ) እና የማይቀበል ትምክህተኛ አማራ ተብሎ ምድር ላይ ሊፈልጉት የሚያስቸግር የአማራነት ቅርጫ በመለስ ዜናዊ ምናባዊ አለም ተሳለ፡፡ ይህ ስዕል ዋነኛ አላማው አማራን ራሱን ተመርኩዞ አማራውን የመቅበር እና በመቃብሩ ላይ የትግሬ ስርወ-መንግስት መመስረት ነው፡፡ በመለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ የተደረገው ፖለቲካዊ እርምጃ ሁሉ የሚመሰክረው ይህንኑ ነው፡፡"