“ምርጫ ተደረገም አልተደረገም የአዲስ አበባ ጉዳይ አልቋል!”እስክንደር ነጋ : “..አብይ ኢትዮጵያን ወዶ ሳይሆን ኢህአዴግ ለማዳን ነው ” ዶክተር አበበ ካሳሁን
እስክንድር ነጋ ከ ethio 360 media ጋር ባደረገው ውይይት “ምርጫ ተደረገም አልተደረገም የአዲስ አበባ ጉዳይ አልቋል! ነዋሪዋ የኢንጂነር ታከለን አስተዳደር በክብር መሸኘትና የኢህአዴግ አገዛዝ አዲስ አበባ ላይ ሙሉ በሙሉ መሸነፉን መንገር ነው የሚጠበቅበት:: እዚህ ላይ ማጭበርበር እንፈፅማለን የሚል አካሄድ ካለ ግን: ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ከኢትዮጵያውያን የሚኖረው ምላሽ የከፋ ይሆናል::
ኢህአዲግ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ሀገር አቀፍ መሸነፍ አለበት::ይህንን ለማድረግ ብዙ ሥራ ይጠይቃል:: ”
እስክንድር ስለ እስረኞችም ይህን ብሏል:
“ንፁሃን ዜጎች በፀረ ሽብር ሕጉ እንዲከሰሱ የተደረገው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ባስተላለፉት ቀጥታ ትእዛዝ ነው:: .. ጠቅላይ ሚንስትሩ ሰሞኑን በሱዳን እስር ቤት የነበሩትን ወገኖች አስፈትተው መምጣታቸው ተሰምቷል:: ይህ የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም:እሳቸው በሚመሩት አገር በእሳቸው ፊርማ ንፁሃን ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ባለበት የጠቅላይ ሚንስትሩን አካሄድ ጥያቄ ውስጥ የሚቀት ነው::
...አሁን አገሪቱ ውስጥ ያለው እውነታ ግን ከትላንቱ ምንም ያልተሻለኛ ጭራሽ በባሰ መልኩ እየቀጠለ ያለ ነው:: አሁን ላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ ነው::”
====== = = = = = = = = = = = = = = = = == = = = = = == = = = = = == = = = == = =
ዶክተር አበበ ካሳሁን ከአስራት ሜድያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ይህን ብለዋል:
““ኢህአዲግ ከመፈራረሱ በፊት በህዝባዊ አመፅ ሊመታ ይችላል :: ..አብይ ኢትዮጵያን ወዶ ሳይሆን ኢህአዴግን ለማዳን ነው:: እኛ ኢህአዲግን ልናስወግድ ስንታገል ኢህአዲግ ቅርፁን ቀይሮ ነፃ አውጭ ሆኖ ብቅ አለ:: የኢትዮጵያ ጠላት ግለሰቦች አይደሉም : ኢህአዴግ ነው::
ኢህአዴግ መርህ ፀረ አማራ ነው::
በአብን ላይ የሚወስዱት እርምጃ ከአማራ ጋር እያቃረናቸው የሚመጣና መጨረሻ ላይ የአማራን ሕዝብ ወደ ሕዝባዊ አመፅ የሚያስገባው ነው የሚሆነው::
የአማራ ወጣት መደራጀት አለበት : እንደ አንድ አማራ መንቀሳቀስ አለብን::
https://www.youtube.com/watch?v=I8PHjiYaJ_Y
”
Last edited by Abaymado on 24 Aug 2019, 01:43, edited 2 times in total.
-
Halafi Mengedi
- Senior Member+
- Posts: 47504
- Joined: 30 May 2010, 23:04
Re: “ምርጫ ተደረገም አልተደረገም የአዲስ አበባ ጉዳይ አልቋል!”እስክንደር ነጋ : “ኢህአዲግ ከመፈራረሱ በፊት በህዝባዊ አመፅ ሊመታ ይችላል :: ..አብይ ኢትዮጵያን ወዶ ሳይሆን ኢህአዴግ
Stop mentioning your delusional Ethiopian talking points, no ethnic will rally with Amhara let alone to assemble as Ethiopians. You can do what ever you want as Amhara but talking Ethiopians is deceiving your coward gut.