Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4514
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

የ“ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ኤርትራ!”ካድሬዎች ውድቅ ፍልስፍና - ክፍል 1 እና 2 - ብርቅ ታሪካዊ ሓቆችን የያዘ ጽሑፍ

Post by Meleket » 01 Aug 2019, 02:27

የሻዕብያንና የወያኔን ግንኙነት በተመለከተ ካነበብናቸው ጽሑፎች እጅግ ሚዛን የደፋው አንዱ ይህ ነው። ጸሐፊው ሚዛናዊ ሰው ሆኖ በመገኘቱ ባለበት “ሐሊብ ስተ” ብለነዋል! :mrgreen:

“ድንክ ነህ እንዳትባል፣ ረዥሞቹን ኣሳጥር” የወያኔ ካድሬዎች “የተሞከረ” ፍልስፍና 1ኛ ክፍል

ማሕሙድ ሳልሕ እንደጻፈው - July 20, 2019

ብዙ ሰዎች
ወያነን የሚቃወም ነገር ለምንድነው የምትጽፈው? ለምን ግዜህን በሌላ ጠቃሚ ነገር ላይ አታውልም?
ይሉኛል። እኔ ከወያኔ አንጻር ጽፌ አላውቅም። ህዝቤን ሃገሬንና ታሪኬን የሚያንቋሽሽ ግልጽ የማጠልሸት ዘመቻ ሲካሄድ ግን ተገቢውን መልስ መስጠት እንደሚገባኝ አውቃለሁ። የትግራይ ህዝብንና ትግሉን ለአንዲት ቀንም እንኳን ትሁን ሰድቤ ወይ ዘልፌ አላውቅም። ዛሬም በተደጋጋሚ የወያነ ካድሬዎች የሐሰት ታሪክና ጉራን ስለተመለከትኩና ስለሰማሁ ተገቢውን መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ። ሐቅ የሚያቅለሸልሸው ሰው ካለ ከወዲሁ ይህን ጽሁፍ ከማንበብ እንዲገታ እመክረዋለው።

የምትለውን ለማጤን ማንበባችንን እንቀጥላለን የምትሉት ደግሞ በሉ እንግዲህ በትዕግስት ተከታተሉኝ። አስቀድሜ ይህችን ቪዲዮ የላከችልኝን የጽሑፌ ተከታታይ ላመሰግናት እወዳለሁ። በሁለተኛው ክፍል፣ ይህችን ቪዲዮ እንደ ምሳሌ ወስጀ፡ አጠቃላይ ማሕበራዊና ስነ-ልቦናዊው ልዩነታችን ያስከተለውን ባህርያዊው የአስተሳሰብና የአመለካከት ትፍጊያችን በብልሃት ካልተለየ፡ ምን ያህል ብዙዎችን ሊያወናብድ እንደሚችል ለማሳየት እሞክራለሁ። የተለያዩ ኅብረተሰቦች ሁኑ እንቅስቃሴዎች፣ እንዲሁም ሰራዊት፣ ያ ያለፉበትና የቀሰሙት የተለያየ የተሞክሯቸው ውጤት፡ የተለያየ የተሞክሮ ልማድና ብቃት ልዩነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ለምሳሌ አይደለም ሻዕብያና ወያኔ ይቅርና፣ በተለያዩ የሻዕብያ የጦር ክፍሎች መካከል ሳይቀር ትንንሽ የልምድና የብቃት ልዩነቶች ነበሩ። ወታደር ሲባል በተፈጥሮው ትምክህተኛ ነው። በሁለት የተለያዩ ሰራዊቶች ማለትም በሻዕብያና በወያኔ መካከል ያለውን ልዩነት ወደ ጎን ትተን፣ በወገን ማለትም በሻዕብያ የተለያዩ ተዋጊ ክፍሎች ማለትም በተለያዩ ብርጌዶችና በክፍለሰራዊቶች መካከል እንዲሁም በተለያዩ የድጋፍ ሰጪ ክፍሎች መካከል የነበረው የብቃትና የልምድ ልዩነት አንዱ ካንዱ ቢለያይ ከነባራዊው ሁኔታ ኣኳያ የሚታይ ባህርያዊ ክስተት ተደርጎ ይወሰድ ነበር። ይህን የመሰለው ባህርያዊ ልዩነት በጋራ መስራት ስትጀምር ብቻ ነው፡ እርስበርስ መተማመን እየተፈጠረ፡ አንዱ ካንዱ ልምድ እያካበተና እየተወያየ ሊስተካከል የሚችለው። የወያኔ ሰራዊት በተመለመለበት የጦርነት ስልት ብቁ ነበረ። የህወሃት ታጋዮችም ጎበዝ ተዋጊዎች ነበሩ። በእርግጥ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ መጥፎ ተዋጊ የሚባል ህዝብም አላጋጠመኝም። ጦርነት ግን ከግላዊ ድፍረት ባሻገር የሚጠይቀው ጉዳይ አለ። ጥናቶችን፣ የስራ ውጥኖችን መንደፍ፣ በጦርነቱ ውስጥ የሚሳተፉ የሰራዊት ክፍሎችን ብቃት ግምት ውስጥ ያስገባ አደረጃጀት፣ ተዋጊውን አካል የሚደግፉ ሃይሎችና የተቀላጠፈ የሎጂስቲክ መስመር እንዲሁም ችግርን የመቋቋም ብቃትና (stamina) ልምድ ያካበተ አመራር . . . ወዘተ ያስፈልገዋል። ይህን ዋንኛ ሃሳቤን እንደሚከተለው አቀርበዋለው።
—————-

ነሐሰ 2018፡ “የመለስ ዜናዊ አቋም በኤርትራ ኣኳያ” በሚል ርእስ የትህነግ ስራ አስፈጻሚ ኣካል አባል በሆነው በጌታቸው ረዳ፡ የተሰጠውን ወልጋዳና የተዛባ ንግግር የሚያጋልጥ “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ኤርትራ” http://www.meskerem.net/%E1%88%85%E1%8B ... %88%8D.pdf “ በሚል አርእስት ባሰፈርኩት ጽሑፌ ነቅፌው ነበር። ጌታቸው በንግግሩ ህዝባዊ ወያነ ትግራይ ከህዝባዊ ግንባር በላይ ለኤርትራ ህዝብና ለኤርትራ ህዝብ ጉዳይ እንደታገለ ያለ አንዳች ማቅማማትና ይሉኝታ ገልጿል። በዚህ ብቻም አልተገታም፡ ”ይሁና! ይህማ አመላቸውም እማይደል” ባልን ነበር። ጌታቸው ግን (መለስና ካድሬዎቹ በመገቡት መሰረት እንጂ እሱ እንደሆነ ወርዶበት በትግሉ ወቅት አልነበረም)የኤርትራ ህዝብን አብዮት በክዳት አጠልሽቶታል ከሶታልም፣ የኤርትራ ህዝብ ድርጅቶች በተለይም ህዝባዊ ግንባር በኤርትራ ህዝብ ጉዳይ ላይ ቁማር እንደተጫወተና ከደርግ ጋር የሰላም ውይይት ያደርግ እንደነበረ አስመስሎ ለፍልፏል። ውሸት የምትመገብ ከሆንክ፣ ሃይልህንም ሆነ ወኔህን ከውሸት ነው የምታገኛቸው። ያኔ እህል ምንም ትርጉም የለውም። ያም ሆነ ይህ፡ ወያኔዎች ከህዝባዊ ግንባር ይልቅ ለኤርትራ ህዝብ ታግለናል እያሉን ስለሆኑ
በሉ እንግዳዉኑስ ፡ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ኤርትራ እንበላችኋ!
ብያችው ነበር ።
ጽሑፏን ደግሜ ስለማመጣት እንድታነቧት እማጠናችኋለሁ። በነገራችን ላይ ወያኔዎች የኤርትራን ጉዳይ አምነንበታል ብለው ሲሉ ሁሌም ከራሳቸው መንታ አስተሳሰብ አኳያ እንደሚሄዱ መዘንጋት አይገባም። የአንዲት እራሷን ያቀናች (assertive)፡ ሙሉ በሙሉ የራሷን ጉዳይ በራሷ የመወሰን ፖለቲካዊ ነጻነት ያላት ኤርትራ መምጣት፡ በመሰረቱ ወያኔዎች እንደ ስጋት (threat) ይቆጥሩት እንደነበር፣ ከህዝባዊ ግንባር ጋር ከተጋገዙት ይልቅ ከህዝባዊ ግንባር ጋር የተጎሻሸሙትና ከህዝባዊ ግንባር አንጻር የሰሩት እንደሚበዛ በዚያች ጽሁፌ ተንትኘው ነበር። ሁለተኛዋን ክፍልም ለመጻፍ አስቤ ነበር፡ ነገር ግን ከሰላሙ ሂደት አኳያ ለሰላሙ ዕድልን መስጠት መርጫለሁ። ወያኔ የትግራይ ህዝብ፡ ሻዕብያም የኤርትራ ህዝብ መሆናቸውን በተለያዩ ጽሑፎቼ አበክሬ ገልጫለሁ። በተጨማሪም፡
አስተማማኝ ሰላም ሊፈጠር ከሆነ፡ የሁለቱ ወገኖች ፖለቲካዊ ኃይሎች ሰላም ሊያደርጉ ይገባል
ብየም ጥሪየን አስተላልፌ ነበር።

አሁንም ቢሆን እምነቴ ከዚህ አይለይም። ሰላም በፍላጎትና በምኞት ብቻ አትገኝም። ሰላም የሚደረገው በሁለት እኩዮች መካከል ነው። ከዓማጺ(ዓመጸኛ) ጋር ሰላም የሚደረግ ሆኖ አይሰማኝም። ስለሆነም፡ ማንኛዉም የሰላም ሙከራ፡ የዚህ ሁሉ ጥላቻ ምክንያት የሆነው የወያኔዎች የወሰን ድንበር ኮሚሽንን ብይን አሻፈረኝ ባይነትንና የአልጀርሱን ስምምነት በተመለከተ ወያኔዎች ያላቸውን የተንጋደደና የተወላገደ አተረጓጎም የሚከረክምና የሚያስተካክል ሊሆን ይገባል። ስለሆነም፡ ይህ ፖለቲካዊ ውሳኔ በመሆኑ፡ ከዚህ ጽሑፍ አቅም ውጪ ስለሆነ ወደ ዋንኛ የመነሻ ጉዳያችን እንመለስ።

ባለፉት ወራቶች፣ በርካታ የትህነት ወያኔ ነባር ታጋዮች ስላለፈው የትግል ህይወት ልምዳቸው ሲገልጹ ቆይተዋል። ብዙ ክፍሎች ያሏቸው ዶክመንተሪዎችንም አሰራጭተዋል። መቸም ሳሕል መድረስ እንደ ትልቅ ጉዳይ ስለሚታይ፡ በቃለ ምልልስ (መጠይቅ) ይቀርቡ የነበሩት በርካታ የትህነግ ወያኔ ነባር ታጋዮች ሳሕል ድረስ መሄድን እንደ የክብር ሽልማት (badge of honor) ስለሚቆጥሩትም ሊሆን ይችላል፡ ሳሕል የሚለው ቃል ሲነሳ ታስሮ እንደቆየ ቡችላ ያቅበጠብጣቸዋል። በሻዕብያ ታጋዮች በኩል ብዙ ስለማይወራለትም ሊሆን ይችላል፡ ወያኔዎች ባዶ ነጻ ሜዳ ስላገኙ ታሪካችንን ሲያንቋሽሹና ሲያራክሱ እያየናቸው ነው። ይህ ደግሞ በቀላሉ የሚታይ ጕዳይ ሊሆን አይገባም። ጭራሹኑ አንዳንድ ኤርትራውያን፡ የወያኔዎቹን ታጋዮች እየጠቀሱ
ጀነራል እከሌ(እንቶኔ) እንዲህ ብሏል አይደል
እያሉ ሲከራከሩ ተስተውለዋል። ስለሆነም ምን ይደረጋል፡ እኔ በማውቀው በኩል ያለውን ታሪክ ለመመለስ እገደዳለሁ።

ደሞክራሲን በተመለከተ የሚሉትን ወደ ጎን ትቸ በወታደራዊ ዲስኩራቸው ላይ አተኩራለሁ። እግረመንገዴን ግን ይህን ለመግለጽ እወዳለሁ፦ የወያነ ደሞክራሲ ኢትዮጵያን በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብን ምን ዓይነት ደረጃ ላይ ጥሏቸው እንዳለ እያየን ነው። ስለሆነም፡ ብዙ ሐተታ አያስፈልገውም። ዛሬ በኢትዮጵያ፡ ወያነ የሚቆጠረው እንደ እከክ ነው። ትግሬዎች ባላደረጉት ነገር በሃገራቸው ውስጥ እንዳሻቸው ሊንቀሳቀሱ አይችሉም። ከትግራይ ክልል ውጭ፡ ቋንቋቸውንም ቢሆን በተዘጋ ግቢ ውስጥ ብቻ ነው የሚጠቀሙባት። ወያኔ በትግራዮች ክብር ላይ ይህን የመሰለ ሁኔታን ነው የፈጠረው። ይህም የነሱ የራሳቸው የግላቸወ ጕዳይ ስለሆነ ሃገሬንና ታሪኬን ወደሚመለከተው አርእስት ልመልካችሁ እስኪ። ለዛሬ የወያኔ ካድሬዎች የሻዕብያን ወታደራዊ ስልትና አስተሳሰብን (doctrine) በተመለከተ የሚፈላሰፉትን እስቲ ላተኩርበት። በሁለተኛው ክፍል ከወያኔዎቹ ውስጥ አንዱን እንደ ምሳሌ ወይ አብነት ወስጄ፡ ከወያኔ ጋር ስላደረግነው መተጋገዝ፡ በሻዕብያ ታጋይ ዓይን እይታ ለመግለጽ እሞክራለሁ። በብርቱውና ቀውጢው ግዜ ከጎናችን ሆነው ለተዋጉትና ለተሰዉት የትህነግ ወያኔ ጀግና ታጋዮችን ያለኝ አክብሮት፡ እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ለሻዕብያ ታጋዮች የነበረውን ፍቅርና ከኤርትራ ህዝብ ጋር ሆኖ ላሳየው አይበገሬነት አክብሮቴን ልገልጽ እሻለሁ። ችግራችን ከጠማማዎቹና ወልጋዳዎቹ ከወያኔ መሪዎች ጋር ነው እንጂ፡ ከትግራይ ህዝብና ከትግሉ ጋር ምንም አይነት ችግር አልነበረንም የለንምም።

“የሻዕብያ ስትራቴጂ ስህተት ነበርን?”

የውጊያ ስልትና ስትራቴጂ (doctrine) በዋነኛነት የሚመረኮዘው ከአቅምህና ከጠላትህ አቅም አኳያ ነው። ያ የወያኔን እንቅስቃሴ ይከላከል፡ የሻዕብያን ደግሞ ይገጥም የነበረው ጠላት ምንም እንኳ በአንድ ፕረሲደትና በአንድ ጠቅላይ ስታፍ ስር ይተዳደር የነበረ ቢሆንም፡ ደርጉ በትግራይ አስቀምጦት የነበረው ኃይል፡ የወያኔን አቅም የሚገታ ኃይልን ብቻ ነው። እስከ 1988፡ በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ እዝ የሚባል ነገር አልነበረም። ከዚያ ወዲህ እዝ የሚባለው ክፍል ሲቋቋምም በሻምበል እንዲመራ ነው የተደረገው፡ እሱም ሻንበል ለገሰ አስፋው። ይህን እያቀረብኩት ያለሁት ለማንቋሸሽና ለማጣጣል ብዬ አይደልም። ነገር ግን በኤርትራና በትግራይ ውስጥ የነበረው ውጊያ ወይ ጦርነት የተለያየ እንደነበረ ለማሳየት ነው። ኤርትራ ውስጥ በአስሮች የሚቆጠሩ የደርግ ጀነራሎችና የሶቪየት አማካሪዎች የሚመሩት በሁለት አገሮች መካከል እንደሚካሄድ የተዋጣለት መደበኛ ውጊያ ወይ ጦርነት (conventional warfare) ይካሄድ ነበር። ትግራይ ውስጥ ግን ቀላል የሽምቅና ተንቀሳቃሽ ውጊያ ነበር የሚካሄደው።

እስቲ በመጀመሪያ የነጻነት ውጊያ ስልቶችን የእድገት ደረጃ በጥቂቱ እንቃኝ

የሽምቅ (ደባይ) እንቅስቃሴዎች ወይም የትጥቅ ትግሎች ልክ እንደ ህይወታውያን ይወለዳሉ፣ ድክድክ ይላሉ፣ ይጎብዛሉ እንዲያ እያሉም ያድጋሉ ይጎለብታሉ። የመጀመርያው ደረጃ የትጥቅ ትግል ወይ የነጻነት ድርጅቶች የትግል ስልት የሽምቅ ውጊያ ነው። አጀማመራቸው ላይ፣ አናሳዎች ስለሆኑ ኃያልና ብርቱ ጠላትን ለማጥቃት ያለሙ ስለሆኑ፡ በሰው ኃይል ሆነ በተኩስና ውጊያ ዓቅማቸው ገና ደካማዎች ስለሆኑ፡ የግድ ይህን የሽምቅ ውጊያ ስልት ለመጠቀም ይገደዳሉ። ይህም ማለት የተለያዩ የጠላት የጦር ካምፖችን በማጥናት ድንገተኛ ጥቃትን መፈጸም፡ ኮንቮዮች ላይ ጥቃት ማድረስ እንዲሁም አንዳንድ ወሳኝ ሰዎችን መጥለፍ ወይ መግደልና የወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ አውታሮችን ማደባየት . . . ወዘተ ያጠቃልላል። ይህ ጥቃት ድንገተኛና ከመቅጽበት ጥቃትን በመፈጸም መሰወርን የሚጠይቅ የትግል ስልት ነው። ሁሌም በህዝብ መካከልና ከአካባቢው ጋር መመሳሰልን የሚጠይቅ ተንቀሳቃሽና ቀለል ያለ መደራጀትን የሚጠይቅ የውጊያ ስልት ነው። ይህ አይነት ስልት አንድ ግዙፍ ጠላትን አንተ በሚመችህና በፈለግክበት ግዜና ሁኔታ ለማቋሰል የምትጠቀምበት የትግል ስልት ነው። በአንድ ውጊያ ስትራቴጂካዊ ጉዳትን የማያስከትል ነገር ግን ቀስ በቀስ ተደማምሮ የጠላትን ሞራል የሚያዳክም ስልት ነው።

ቀጥሎ የሚከተለው ተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልት ነው። ይህኛውም የኣቅም ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከሽምቅ ውጊያ ጋር ተመሳሳይ ስልት ነው። ነገር ግን ከሽምቅ ውጊያ የተሻለ አቅምና ሃይል ያለበት ስለሆነ፣ እርስበርስ የተዛመዱ ወይ የተገናኙ ነገር ግን የተለያዩ ዒላማዎችን ለማጥቃት የሚያስችል በዛ ያሉ የሰራዊት ክፍሎችን የሚያሳትፍ ነው። አደረጃጀቱም ከሽምቅ ውጊያ ሰፋና ረቀቅ ያለ ነው። ከሽምቅ ውጊያ የተሻለ የድጋፍ ኃይሎችም ያሉት ነው። በተንቀሳቃሽ ውጊያ ደረጃ የደረሰ ኃይል፡ የሽምቅ ውጊያም የስትራቴጂው አካል ሆኖ ይቀጥላል። የመጨረሻው ደረጃ ደግሞ ቋሚ የውጊያ ወይ የጦርነት ስልት ነው። ቋሚ ውጊያ በሁለት የእኩልነት ወይ ተመጣጣኝ አቅም ባላቸው ኃይሎች መካከል የሚካሄድ የውጊያ ስልት ነው። ይህ ዓይነት የውጊያ ስልት የነጻነት ትግል እንቅስቃሴ ጎልብቶ፡ ነጻ ያወጣው መሬትና ያስመዘገበው ድልን አስከብሮ ወደ ሌላ በርካታ ድሎች በሚያማትርበት መድረክ የሚመረጥ የትግል ስልት ነው። ውጊያው ወይ ጦርነቱ እጅግ እልህ አስጨራሽና ፉክክር የበዛበት ከባድ ውጊያ ስለሚሆንም አብዛኛውን ግዜ ቋሚ የውጊያ ግንባሮች መመስረት የዚህ ዓይነት ከፍተኛ ደረጃ የውጊያ ስልት ዋንኛ ባህሪ ነው። ይሁን እንጂ የደፈጣና የተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልቶችም ያካተቱ ኦፕሬሽኖችን እንደ እስትራቴጂነትም ይጠቀምባቸዋል። እንግዲያዉስ ይህን የመግቢያ ቍምነገር ካካፈልኩ ዘንድ ወደ ዋናዉ አንኳር ምጉቴ ልግባ። ተከተሉኝ።

ህዝባዊ ግንባር፡ በቋሚ ምሽጎች ውስጥ ከመጠመድ ይልቅ ከህዝቡ ጋር ሊደባለቅ ይገባል፡ የሽምቅና ተንቀሳቃሽ ውጊያዎችን ማካሄድ ይገባዋል
ይሉ ነበር የወያኔ ካድሬዎች።
ይህቺ እየተደጋገሙ ከሚወሱት የወያኔ ካድሬዎች ንግግር አንዷ ነች። ሳሕልን በተመለከተ ሲናገሩ ይህችን ሳይጠቅሱ አያልፉም። ግን ምን ያህል እዉነት ነች? እስቲ የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት።
አንድ የነጻነት ትግል ከቋሚ የውጊያ ስልት ወደ ሽምቅና ተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልት እንዲቀየር የሚያደርገው ወሳኝ ነገር አቅሙ ነው። ሲዳከም ብቻ ነው ወደ ኋላ የሚመለሰው።

ወያነ ሲመሰረት (1975) ህዝባዊ ሓይልታት (ህግሓኤ)፡ ወደ የተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልት ደረጃ አድጎ ነበር። ወያነ በጋንታ (በመቶ) ደረጃ ሲንቀሳቀስ (1977) የኤርትራ ድርጅቶች ሻዕብያና ጀብሃ በብርጌድ ደረጃ ተደራጅተው፡ የኤርትራ ትልልቅ ከተሞች ከአስመራ ዓሰብና ባረንቱ በስተቀር ኤርትራ ነጻ ወጥታ ነበር። ስለሆነም፡ ወያኔ በ1988 ደርሶበት የነበረው የአደረጃጀት አቅምና ደረጃ፡ የኤርትራ አብዮት በ1977 ደርሶበት ነበር። ህግሓኤ፡ አስር ዓመቶች ወደኋላ የሚመለስበት አንዳችም ምክንያት አልነበረውም።

ከሶብየት ህብረት ጣልቃ ገብነት አኳያ (19780)፡ ስልታዊ ማፈግፈግ እንደታወጀም፡ ህዝባዊ ግንባር እየተዋጋ ነው ያፈገፈገው። ዔላበርዕድ፡ ገንፈሎም፡ ማዕሚደንና ሌሎች በርካታ ቦታዎች ላይ ጠላትን ድባቅ እየመታና እየደመሰሰ ነው የመጨረሻ ይሆነኛል ወዳለው የመከላከያ መስመሩ የደረሰው። ከዚያ መስመር ተገፍቶ ቢሆን ኖሮ ወደ ተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልት ከመውረድ በስተቀር ሌላ አማራጭ ባልነበረው ነበር። ነገር ግን ለአስሮች አመታት የመከላከያ መስመሩን አጽንቶና ጠብቆ ባለማስደፈር፡ እጅግ ትጉ ፈጣንና የተራቀቀ ደጀንን መሰረተ። ውጊያው በሁለት እርስበራሳቸው በሚተዋወቁ ተቀናቃኞች መካከል ይካሄድ ስለነበረ፡ ሁለቱም ተቀናቃኝ ወገኖችም ጠንቅቀው በሚያውቁትና ባጠኑት የመልክዓምድር (terrain) ቅርጽ ስለተካሄደ፡ እጅግ ኃይለኛ ነበር። ህዝባዊ ግንባር ኃይለኛ ጠላት ስለገጠመውም፡ የግድ ከችግሩ በድል ለመውጣት መማርና መላን መፍጠር ነበረበት። ይካሄድ በነበረው ውጊያ የማረካቸው የተለያዩ ብዛት ያላቸው መሳሪያዎች፡ የተኩስና የውጊያ ኣቅሙንና ብቃቱን እንዲያደልብ አድርገውታል። ከባድ ውጊያ ይካሄድ ስለነበረም ኃይለኛና የተራቀቀ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎችን (የከባድ ብረት፡ መካናይዝድ፡ የአየር መቃወሚያ፡ የወታደራዊ መሃንዲስና የስለላ እንዲሁም የኮሚኒኬሽን . . . )ድጋፍ ሰጪ ክፍሎች የግድ ያስፈልጉት ነበር። ሰራዊቱም የግድ መታጠቅ መመገብ መታከምና መልበስ ይገባው ስለነበረ ፈጣንና የተዋጣለት የሎጂስቲክ መስመሮችን ተቋሞችንና መጓጓዣ መሳሪያዎች እንዲሁም ጋራጆች . . . ወዘተ ያስፈልጉት ነበር። ይህን ሁሉ የሚያስተዳድር መሪ አካልና የጽሕፈት ቤቶችም እንደሚያስፈልጉ የታወቀ ነው። ባጭሩ ደጀን ያስፈልግ ነበር። ስለሆነም ፡ ህዝባዊ ግንባር ደጀንን የፈጠረ፡ አንዳንድ ወያኔዎችና የወየኑ የሻዕብያ ታጋይ ነበሮች እንደሚሉት፡ የህዝባዊ ግንባር አመራር ኣካል በምቾት ለመኖር የፈጠረው ሳይሆን፡ ህዝባዊ ግንባር እንዲያደርገው የተገደደ፡ የውጊያው ወይ የጦርነቱ ባህሪ የፈጠረው ክስተት ነው። የህዝባዊ ግንባር ደጀን የወታደራዊ እዝ ብቻ አልነበረም። የሁሉም ህዝባዊ አደረጃጀቶችና የዲፕሎማሲያዊ ተልእኮዎች መናሀሪያ፡ ለህዝብ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች መነሻም ነበር። ከትልልቅ ከተሞች በስተቀር፡ የኤርትራ መሬትና ህዝብ በህዝባዊ ግንባር ይተዳደር ስለነበር፡ ደጀኑ እውቅናን እንዳላገኘ መንግስት (defacto) ሆኖ ነው የሰራዉ።

እንግዲያዉኑስ ቋሚ ውጊያ ማካሄድ፡ ጠላትን ከአጥቂነት ወደ ‘መሳ’ነት ወይ ወደ ተከላካይነት እንዳወረደው ያሳያል። የጠላት ዓቅም መዳከሙንና በአንጻሩ ደግሞ የህዝባዊ ግንባር ዓቅም መጎልበቱንና መዳበሩን ነው የሚያሳይ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ ወያኔ እንደሚለው፡ ህዝባዊ ግንባር የተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልትን ከማድረግ አልተገታም፡ ዋንኛ የጠላትን ዓቅም በሳሕል ተራራዎች ላይ ስለያዘው፡ ከጠላት ወረዳ ውስጥ ተልእኮ የመፈጸም ኣቅሙና ዕድሉን አስፍቷል። ህዝባዊ ግንባር ብቋሚነት በጠላት ወረዳ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የህዝባዊ ሰራዊት ሃይሎችና የዞባዊ ሰራዊት ሃይሎች ነበሩት። የጠላትን ምሽግና ካምፖች መደምሰስ በየዕለቱ የሚደመጡ ዜናዎች ነበሩ። የመሃንዲስ፡ የኮሚኒኬሽን፡ የጀማሂር (ህዝባዊ አደረጃጀት)፡ የትምህርት ክፍልና የህዝባዊ ክሊኒክ ክፍሎች ስራቸውን አቋርጠው አያውቁም። በየግዜውም የህግሓኤ የጦር ሰራዊት ክፍሎች ከሳሕል የግንባር ይዞታቸው ወደ ደጋማው ክፍል እየወጡ የጠላትን ካምፖች ረጋግጠው ይመለሱ ነበር። ቋሚ የተባለው ግንባርም ቢሆን ብዙ ጊዜ ተደምስሷል፡ ተደማሷልም። ስለሆነም፡ ወያነ፡ ያ የማያውቀውን የትግራይ ህዝብ ለማደናገር፡ በተግባር በተጨባጭ ሁኔታ ያላገኘውና ያልነበረውን ዓቅም እንደነበረው አስመስሎ በማጭበርበርና በማደናገር ለመተወን እንጂ ዲስኩሩ የከንቱ ከንቱ ነው።

ሁሉ ግዜ የምትገርመኝ ደግሞ “ወደ ህዝባችሁ ለምን አትወጡም” የምትል አባባላቸው ናት። የሳህል ህዝብ የህዝባዊ ግንባር አይደለም እንዴ? የማርያና የዓንሰባ ህዝብ የኤርትራ ህዝብ ኣይደለም እንዴ!? በቋሚ ግንባሮች ውስጥ ተወስኖ ቢኖርም እንኳ፡ ህግሓኤ በህዝቡ መሀል አልነበረም እንዴ? ወያኔ ለመሆኑ “የኤርትራ ህዝብ” የምትለው ማንን ነው እንዴ? ለመሆኑ ኤርትራን ታውቃታለችን?
አንዳንዴ የሚሟገትህ ሰው ወይ አካል ዓቕም ስለሚያስገድድ እንጂ ዛሬ ይህን በመሰለ ጉዳይ ላይ ጊዜያችንን ባላጠፋን ነበር።

በመጨረሻ፡ ወያኔ፡ ስለ ቀይኮከብ ዘመችቻ ማውራት ደስ ነው የሚለው። ለሻዕብያ ታጋይ ግን የቀይዀከብ ዘመቻ ወይም ስድስተኛው ወረራ ከብዙ ወረራዎች አንዱ ነው፡ ወያኔ እጇን በቀይኰከብ ዘመቻ ከማስገባቷ በፊት ሻዕብያ አስቀድሞ አምስት ትልልቅ ወረራዎችን አክሽፎ ነበር። ትልልቅ የመልሶ ማጥቃት እርምጃዎችንም ወስዶ ነበር፡ ከወያኔ በኋላም ሁለት ሌሎች ትልልቅ ከቀይኰከብ ወረራ እጅግ የከፉ ወረራዎችንም አክሽፎ፡ በቋሚ ምሽጎች ተፋጦት የነበረውን የጠላት ግምባር ደረማምሶና ደማሶ የከረን ‘ጻዕዳን’ በሮች ማንኳኳት ጀምሮ ነበር። ያኔ ነው ወያኔ ለዓመታት አሸልቦት ከነበረው እንቅልፉ መንቃት የጀመረው።

ከናደው እዝ መደምሰስ በኋላ፡ የድል ንፋስ ከከረን ግንባር ወደ ትግራይ መንፈስ ሲጀምር፡ ወያነ “ሻዕብያ ነጻነትን ሊያመጣ ይችልም” እያለ የስም ማጥፋት ዘመቻ ያካሂድበት የነበረውን ድርጅት ሻዕብያን፡ ሳይውል ሳያድር፡ በራዲዮው “እንኳ ደስ አላችሁ” ለማለት ተሯሩጧል። የናደው እዝ መደምሰስ የወያኔን የትብብር መንፈስ አንቀሳቅሷል። ከሻዕብያ ጋር ተጋግዞ የሽሬ ከተማን ነጻ ካወጣ በኋላ ወታደራዊ ብቃቱ በመጠኑ መቀየር ጀመሯል። ወያኔ የሚመካበት ትርጉም ያለው ጦርነት 604ኛ ኮርን ለመደምሰስ የተካሄደው ውጊያ ነው። ይህም ከሻዕብያ ጋር ሆኖ የተካሄደ ውጊያ ነው። የሻዕብያ ታጋይን ግን ምን ያህል ኮሮችን ደምስሰሃል ብለህ አትጠይቀውም። ስንቱን ቆጥሮ ሊዘልቀው!

በመግቢያ እንደገለጽኩት፡ የትህነግ ታጋዮችን ለማንቋሸሽ አይደለም፡ ሁለቱን ድርጅቶች ገጥሞ የነበረው የጠላት አሰላለፍ ልዩነት ስለነበረው ነው። የዚህ ጽሁፍ እንደገለጽኩት ብዙዎች ታሪካችንን ሲያቆናጽቡ የታዘብኳቸው የትህነግ አመራሮች በመሆናቸው፡ በቀጣዩ ክፍል ከነሱ ውስጥ አንዱን እንደ አብነት አንስቼ፡ ‘ምንድን ነው እንዴ ይህን ያህል የሚያስለፈልፋችው?’ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እሞክራለሁ። ሁለቱም ህዝቦች ብዙ የሚያቀራርባቸው ነገር እያለ የታሪክ አደጋና ያጋጣሚ ነገር ሆኖ እዚህ ደረጃ ወርደናል። በኛ ልፋት ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ የሚሹትን ግን “እንዲህማ በፍጹም አይደረግም” ልንላቸው ይገባል።

ድንክ ሰው ድንክነቱን አምኖ ሂወቱን ተመስገን ብሎ ቢኖር አያሳፍርም።

ይህ የራሴ የግል አመለካከት ነው። ህዝባዊ ግንባርን ወክየ አይደለም የጻፍኩት።

ክብር ለሰማእቶቻችን!

ሓምሌ 2019


viewtopic.php?f=2&t=190670&sid=3159e8ad ... 20fb4f0be8
Last edited by Meleket on 02 Aug 2019, 03:01, edited 1 time in total.


Meleket
Member
Posts: 4514
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የ“ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ኤርትራ!”ካድሬዎች ውድቅ ፍልስፍና 1ኛ ክፍል - ብርቅ ታሪካዊ ሓቆችን የያዘ ጽሑፍ

Post by Meleket » 02 Aug 2019, 02:53

ክፍል ሁለት
ባለፈው ክፍል፡ የወያኔ ካድሬዎች በህዝባዊ ግንባር ወታደራዊ ስትራቴጂ ላይ ሲፈላሰፉ የሚያነሷቸውን ተደጋጋሚ ነቀፌታዎችን አንስቻለሁ፡ አባባላቸው ሁሉ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግና ለጉራ የሚያወሱት እንጂ ምንም ዓይነት ተጨባጭ መረጃ የሌለው እንደሆነ ለመግለጽ ሞክሪያለው። በዋነኛነት የተከተልኩት ስትራቴጂ ደግሞ በኤርትራና በኢትዮጵያ ውስጥ ይካሄድ የነበረውን የውጊያና ጦርነት ባህርይ በመግለጽ፡ አንባቢ የራሱ ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ መተዉ ነበረብኝ። ወያነ፡ ትግራይ ውስጥ ይንቀሳቀስ የነበረውን ቀላልና የተሰበጣጠረ ህልውና የነበረውን ጠላት የሚገጥም ቀላልና ተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልትን ይጠቀም ነበር። ህዝባዊ ግንባር ደግሞ ኤርትራ ውስጥ ከዕለት ወደ ዕለት በየመድረኩ እየተፏፏመና እየበረታ እየጎለበተም ይሄድ የነበረን የውጊያና የጦርነት ደረጃን እንደየመልኩና መድረኹ የሚገጥም የራሱን የውጊያ ወታደራዊ ስትራቴጂ እየተከተለ ለነጻነት በቅቷል። ስለሆነም፡ ህዝባዊ ግንባር ለወያኔ ምክርን ቢለግስ ያምርበታል እንጂ አያስጠላበትም። ሆኖም ህግሐኤ ለወያኔ ወታደራዊ ምክሮችን ይሰጥ ነበር። ለምን ቢባል ህግሐኤ (ሻዕብያ)፡ ወያኔ ትከተለው የነበረውን የደፈጣና የተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልት አስቀድሞ አልፎበታልናን ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን፡ ወያኔ ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የውጊያ ስልቶች፡ ከዋንኛና ቀንደኛ የቋሚ ውጊያ ስልቱ በተጨማሪ እንደ ደጋፊ የውጊያ ስልት እስትራቴጂነት በተግባር ህግሐኤ ይጠቀምባችውም ነበር። የወያኔ ካድሬዎች ግን ገና ያልደረሱበትንና አቅማችው ስላልሆነው ስለማያውቁት የቋሚ የውጊያ ስልት ዲስኩር ሲደሰኩሩ በፍጹም አያምርባቸውም።

በዚህ ቀጣይ ክፍል፡ የወያኔው ታጋይ አቶ ይስሃቅ አበራ ስላነሳቸው ጉዳዮች፡ ወደ ፍጻሜዎቹ በምናብ ተመልሸ እስኪ ልመልከታቸው።

መጀመርያ ግን አንዳንድ መንደርደርያ ነጥቦችን ላስቀምጥ፦

1. የእስትራቴጂ ጉዳያችን፡ በመግቢያ አስቀድሜ እንደጠቀስኩት፡ በኤርትራና በትግራይ ውስጥ የነበረው የጠላት ኃይል አሰላለፍና የጦርነቶቹ ክብደትና መራራነትም የተለያየ እንደነበረ፡ ትግራይ ውስጥ ከነበረው የጠላት ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ህወሓት (ትህነግ) ተንቀሳቃሽና የደፈጣ የውጊያ ስልትን ትጠቀም ነበር። ሻዕብያ ደግሞ ኤርትራ ውስጥ የነበረውን ዋንኛ የኢትዮጵያ ሰራዊት ዓቅም የሚጋተር ወታደራዊ ስትራቴጂን ይከተል ነበር።

2. የብቃት ደረጃ፡ የትህነግ ብቃት ትግራይ ውስጥ ይካሄድ ለነበረው ውጊያ ብቁ ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ አብዮት ኤርትራ ውስጥ እየተካረረና እየከበደ እየተራዘመም ይሄድ የነበረውን ውጊያና ጦርነት የሚጋተር ብቃትን ደልቦና አንጾ ነበር።

3. የጋራ የትብብር ወታደራዊ ተልእኮዎች (joint operations)፡ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በጋራ የመስራት አስፈላጊነት ሲመጣ፡ የአተገባበር ባህል ችግሮች እንዲሁም የብቃት አለመጣጣም ቢያጋጥም አይገርምም፡ ምክንያቱም ባህርያዊና የሚጠበቅም ነውና። የተለያዩ ሃገሮች ሰራዊቶች በጋራ ወደ አንድ ዓውደ-ውጊያ ከመግባታቸው በፊት ብቃታቸውንና የአተገባበር አካሄዳቸውን የሚያወሃህድ በተለያዩ ደረጃዎች የሚደራጅ ልምምድ (war games) ያደርጋሉ። ከዚህም በኋላ ምንም እንኳ የጋራ እዝ ቢቋቋምም፡ ሰራዊቶቹ ግን አስቀድሞ የነበራችውን የአስተዳደር ሰንሰለት ጠብቀው፡ አስቀድመው በሚያውቋቸው አለቆቻቸው ስር ሆነው፡ የየራሳቸው ተልእኾ ተሰጥቷቸው፡ ጦርነቱ ወይ ውጊያ ውስጥ የገባው ሕብረ-ሰራዊት ጋር በተለያዩ ማእዘኖች እየተሳሰሩና እየተወሃሃዱ ስራቸውን ይቀጥላሉ። በስድተኛው ወረራ ወይም በቀይዀከብ ዘመቻ ወቅት ግን፡ የወያነ ሰራዊት ለአጭር ጊዜ የእዝ ሰንሰለታቸውን አቅበው ይሆናል እንጂ ብዙም ሳይቆዩ ወዲያውኑ ነው ከሻዕብያ ሰራዊት ጋር እንዲቀየጡና እንዲደባለቁ እንዲወሃሃዱም የተደረጉት።ለዚህም ምክንያት ነበር። ተንቀሳቃሽና የደፈጣ ውጊያ ስልትን የለመደው የወያኔ ሰራዊት በቋሚ ምሽግ ውስጥ ሆኖ ለመዋጋትና ውጊያውንም ለመልመድ ግዜ ያስፈልገው ነበር። ከዚህ አኳያ ሲታይ፡ ከትግራይ ለመጡት የህወሃት (ትህነግ) ሰራዊት ልዩ ትኩረት መሰጠቱ በወታደራዊ አካሄድ ሲታሰብ የተለመደ አሰራር ነው። አቶ ኢሳቕ እንዳለው፡ ከመተማመንና አለመተማመን ጋር የሚያያይዘው አንዳችም ነገር የለም። በህዝባዊ ግንባር የጦር ክፍሎች መካከልም ቢሆን የልምድ ልዩነቶችና የአቅም መዛነፎች ወይ አለመጣጣሞች የሚታዩበት ወቅትም ነበር። በማጥቃትና ተንቀሳቃሽ (maneuvering warfare) የጦርነት ስልት የተዋጣላቸው የጦር ክፍሎች ነበሩን። ሌሎች ደግሞ የጠላትን ቀንደኛ የመተላለፊያ መስመር ወጥረው የሚጠብቁና የሚይዙ፡ የመድፍና የአየር ድብደባን ለመቋቋም ብቃቱ የነበራቸው፡ የመከላከያ ምሽግን በደንቡ የመስራትና የመከላከያ መስመሮችን የማስተካከል ብቁ ልምድና ችሎታን ያካበቱ የጦር ክፍሎችም ነበሩን። በጠላት በኩልም በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ ወታደራዊ ብቃቶች የታነጸና የተመለመለ በተራራ ውጊያ፡ በጸረ-ሽምቅ ውጊያ፣ በአየር ወለድ እንዲሁም በኮማንዶና የመሳሰሉት ብቃቶች የተመለመለ ሰራዊት ነበር። በአንደኛው የጽሑፌ ክፍል እንደገለጽኩት፡ ወታደር በተፈጥሮው ትምክህተኛ ስለሆነ፡ ሁሌም የራሱ የጦር ክፍልን ከሌሎች የበለጠች አድርጎ የማግዘፍና የመናገር ዝንባሌ አለው።

4. በተጨማሪም፡ በኤርትራዉያን መካከል (በዋነኛነትም በከተሜው ትግርኛ)ና በአንዳንድ የትግራይ ህዝብ ክፍሎች ላይ የነበረው የመናናቅ ስሜትም አልፎ አልፎ ይንጸባረቅ ነበር። በተለይም “ኤርትራዉያን ይንቁናል” የምትለውን ስሜት ከትግራይ ተሸክመው ያመጧት ስሜታቸው ስለሆነች፡ ይህ በአእምሯቸው ቀርጸውት የመጡትን የተሳሳተ ግምት የሚያረጋግጥ ጥቃቅን ክስተቶች ሲያጋጥማቸው፡ አስቀድመው ወዳሰቡት ድምዳሜ ሸተት ለማለት አቀላጣፊ ነበር (confirmation bias)::


አጠቃላይ ግንዛቤየ - የወያኔ ታጋዮችን በሳህል ምሽጎች እንዳያኋቸው

ሀ- በአጠቃላይ የወያኔ ታጋዮች፡ አዲሱን የቋሚ ምሽግ ዕለታዊ የውጊያ ስልትን ለመልመድ ብዙም ግዜ አልፈጀባቸውም፡ በጀግንነትም ከህግሓኤ ታጋዮች እኩል ተዋግተዋል ተሰውተዋልም።

ለ- አንዳንድ የወያኔ ሃላፊዎችና ካድሬዎች፡ በሻዕብያ ሃላፊዎች ወይ አመራሮች ይሰጥ የነበረውን የጦር ክፍሎችን የማጣመር ወይ አንድ የማድረግ ሂደትንና ዕለታዊ ኑሯቸውን በተመለከተ የሚሰጠውን ትእዛዝና ምክር ለመቀበል ችግር የነበረባቸው አሻፈረኝ የማለት ስሜት ይታይባቸው የነበሩ እንደነበሩ አስታውሳለሁ። በዋነኛነት ተራ የወያኔ ታጋይ ግን ከሻዕብያ ታጋዮች ጋር በቅጽበት ተዋህዶ መልካም የሆነን ዝምድና መስርቶ የነበረ ሆኖ ይሰማኛል።

ሐ - ከተለያዩ ድርጅቶች የተቀላቀሉ ወይ የተወሃዱ ስለነበሩ ከግዜ ጋር የመጣ የባህልና የልምድ ልዩነቶች እንደነበሩም አስታውሳለሁ። አንዳንድ ግዜ፡ በሻዕብያ ታጋዮች መካከል እንደ ቀላልና አስቂኝ ይቆጠሩ የነበሩ ቀልዶችና ተመሳሳይ ጥቃቅን ነገሮች የወያኔ ታጋዮችን የሚያስኮርፉና የሚያበሳጩ ሆነው ይገኙ ነበር።

መ - የምግብና የልብስ - ወዘተ ችግሮች ነበሩ። ስድተኛው ወረራ ወይም ቀይኰከብ ዘመቻ የተካሄደበት ወቅት እጅግ መጥፎና መራራ ሁኔታ ላይ ነው።

ሰ- አንድ ግንባር ወይ የጦር ክፍል ውስጥ ሁለት አቻ እዝ ሊኖር አይችልም። ስለሆነም፡ የወያኔ የጦር ክፍሎች በአጠቃላይ በህግሓኤ (ሻዕብያ) እዝ ስር ነው የነበሩት ። የወያኔ መሪዎች፡ ለሻዕብያ ጦር መሪዎች ምክትል ሆነው ሰርተዋል። (ይህም ማለት የወያኔ የሃይል አመራር የጋራው ጦር ሃይል ምክትል ሆኖ ይሰራል ማለት ነው . . ። ወዘተ)።

የ ህግሓኤዉ ታጋይ ገረዝግዜር ዓንደማርያም (ውጩ)ና የወያኔው ታጋይ ይስሃቅ አበራ ጉዳይ—

መጀመርያማ በቪዲዮዋ ውስጥ ያሉትን ነጥቦች እንመልከት፦

ኣቶ ይስሃቕ ኣበራ፡ የሻዕብያ አመራሮች በወያነ ታጋዮች ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸው ብዙም እንደማይተማመኑባቸው፡ የወያኔ ታጋዮችን በመጥፎ ዓይን ያዩ እንደነበር፡ የሻዕብያ አመራሮችን መጥፎዎች መሆናቸውን ለማስረዳት በሱ ማለትም በይስሃቅ አበራና በ4ኛው ብርጌድ አዛዥ ታጋይ ውጩ (የተሰዋ የሕግሓኤ የጦር ኣመራር አባል) መካከል የነበረውን ግንኙነት እንደ አብነት ጠቅሶ ያወሳል።

በቪዲዮዋ የወያኔው አንጋፋ ታጋይ፡ ይስሃቅ አበራ፡ አዛዡ የነበረውን የአራተኛ ብርጌድ መሪ ውጩን እንደ “ገልቱ” ሰው ሲያብጠለጥለው ይስተዋላል፡ የ4ኛ ብርጌድ ኮሚሳር የነበረውን ወዲ ልብሱንም “አዳፋ ወይ ቆሻሻ” በማለት ይገልጸዋል። ከዚህ አባባሉ በመነሳት አቶ ይስሃቅ በነዚህ ታጋዮች ላይ የግል ጥላቻ እንደነበረው ለመገንዘብ እንችላለን። አንድ እኔ ነኝ ያለ ሰው ወይ ሞያተኛ፡ የስራ ባለደረቦቹን ይህን በመሰለ ቃላት አይገልጻቸውም (በሳልና professional አለመሆኑን ያሳብቅበታል)። እስከ የህወሓት (ትህነግ) ሊቀመንበር ድረስ የዘለቀ ስሞታ ከነበረው ደግሞ ጉዳዩ እሱ ሊነግረን ከፈለገው በላይ ትልቅ ወይ ግዙፍ እንደነበረ መገመት ይቻላል። ከሻዕብያ ጋር በነበረበት ወቅት፡ የ1982 የይስሃቅ አበራ ዶሴ ወይ ፋይል እየተገለጠ ቢታይ ምን ዓይነት ሐቆችን ባገኘን ነበር? ለማንኛዉም ወደ ጉዳዩ እንዝለቅ።

1. በዚህች ቪዲዮ ይሁን በሌሎች ተመሳሳይ ቃለ መጠይቆች፡ የአንድ ወገንን ማለትም የወያኔን ትረካ ብቻ ነው እየሰማን ያለነው። ሌላኛው አካልስ ምን ይል ይሆን? በዚች ልዩ ጉዳይ ላይ ካተኮርን ደግሞ የይሳቅ አበራ ቴፕ የምትኖር አይመስለኝም። ውጩ ደግሞ ተሰውቷል፡ በህይወት ቢኖር ኖሮም እዚህ እንካስላንትያ ውስጥ አይገባም? ያቺ የይሳቅ አበራ መጥፎ ዶሴም የመገለጥ ግዜዋ ገና የደረሰ አይመስልም። ታድያ እንዴት አድርገን ነው የይስሃቅን አባባል ልናረጋግጠው የምንችል?

2. ይህን በመሰለ ሁኔታ ውስጥ የምንጠቀምበት የተለመደ አካሄድ አለ።

ሀ. ይሳቅ ያለውን ሊያረጋግጥልን ወይ ደግሞ ከአባባሉ ጋር ሊስማሙ ወይ ሊገጣጠሙ የሚችሉ ሐቆች ልናገኝ እንችላለንን? ይህም ማለት የተባለችዉ ቴፕ ብትገኝና አቶ ይሳቅ እንድንሰማት ይፋ ቢያደርጋት፡ በልዩ ሁኔታ የተገለጸችው ውጊያ የግምገማ ውጤትም አርካይቭ ውስጥ፡ በተለያዩ ማእዘኖች ይደረጉ የነበሩ የሬዲዮ መልእክቶችና ዲያሪዎች . . . ወዘተ ቢገኙ ግሩም ነበር። ለግዜው እነዚህ ሁሉ በእጃችን የሉም።

ለ. እንግዲያዉኑስ ቀጣዯ ስትራቴጂ፡ አቶ ይሳቅ እያለው ያለ ጉዳይ በህግሓኤ ውስጥ በተለይም በ4ኛዋ ብርጌድ ከነበረው የአስተዳደር ስርዓት ጋር ወይም ከውጩ ባህርይ ጋር ይመሳሰላልን (coherence አለዉን?) የምትል ትሆናለች።

ሐ. ቀጥለንም፡ “በ4ኛው ብርጌድ ውስጥ የነበሩ የሻምበል(ቦጦሎኒ) ኣመራሮችን ሰብስበን ብንጠይቃቸው፡ ‘ አቶ ይስሃቅ እያላቸው ያሉት ባህርያት ከውጩ ጠባዮች ጋር የሚሄዱ ናቸው” በሚል ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ ይደርሳሉን?” የሚል ጥያቄን ማንሳትም ሐቁን ለማወቅ ያግዛል።

ከሁሉ የሚገርመው፡ ብርቱ ውጊያ ውስጥ እያለ እንዴት አድርጎ ነው ቴፕ ለመቅዳት ያሰበው የሚለው እጅግ የሚገርምና የሚደንቅ ጉዳይ ነው። ለምን ቢባል ይህን በመሰለው ፋታ በማይሰጥ ውጊያ መካከል ማንኛውም የአእምሮ ክፍልህና ትኩረትህ ሁሉ አጋጥሞህ ያለውን ብርቱ ዉጊያ በምን ጥበብ ላሸንፈው ወይ ልፍታው በሚል ጥረት ውስጥ ብቻ ነው የሚያተኩረው። ቀውጢ በሆነ ውጊያ ውስጥ ሆነህ “ነገ አሌ ይለናል ብለህ በቴፕ መቅዳት” ለማመን ያስቸግረኛል፡ ሳልጠራጠረው እንድቀርም አያደርግም። በቴፕ መቅዳት በፍጹም አያስፈልገውም ነበር። ለምን ቢባል ውጩ ትእዛዙን ያስተላልፍ የነበረው በቴሌፎን አይደለም። ግልጽ በሆነ የሬዲዮ ሞገድ ነው የስራ ባለደረቦቹን የሚገኛቸውና የሚገናኛቸው የነበር። በብርጌድ ደረጃ የሚደረግ ግንኙነት በሶስት ደረጃ ይከፈላል። ውጩ ከግንባር አመራር አካል ጋር እንዲሁም ከእኩዮቹ ከብርጌድ አመራሮች ጋር የሚያገናኝ መስመር ሊኖረው የግድ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከሶስቱ ቦጦሎኒዎች (የሻምበል) አመራሮች ጋርም የሚያገናኝ መስመር ሊኖረው የግድ ነው። በተጨማሪም በሶስተኛ የመገናኛ መስመሩ ደግሞ በድፍኑ ከሁሉ የጋንታ (የመቶ) አመራሮች ጋር የሚያገናኝ መስመር ይኖረዋል። ኣብዛኛውን ግዜ ብዉጊያ ወቅት ብዙ ድምጿ ጎልቶ የሚሰማዉ ሶስተኛዋ መስመር ነች። ውጩ በተለይ ለይስሃቅ የሚያስተላልፈውን ትእዛዝ ደግሞ ሁሉም የቦጦሎኒ (የሻምበል) አመራሮችም ይሰሙታል። ብርጌዷ ውስጥ ሶስት የሻምበል አመራሮች፡ ሶስት የወያኔ ታጋዮችም እንደ ምክትል ሆነው የሚሰሩ፡ ሶስት ደግሞ ኮሚሳሮች ባጠቃላይ 9 ሰዎች መስመር ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉበት ሁኔታ ነበር። ምንም እንኳ በመስዋእትነትና በቁስለኝነት አንዳንዶቹ ቢጓደሉም፡ በዚያች ቀውጢ ሰዓት ቢያንስ ቢያንስ ሶስት የሻምበል አመራሮች መስመር ላይ ናቸው። ግጭትና አለመግባባት ሊፈጠር ይችላል፡ ያም ሆኖ ግን የበታች አካል ለበላይ አካል ሃሳቡን ብቻ ነው ሊሰጥ የሚችል እንጂ፡ ትእዛዝ ሁሌም ከላይ ወደ ታች ነው የምትፈሰው። ጦርነት ውስጥ ደግሞ እምቢ ማለት አይቻልም። እንዲህ ይሳቅ እያለን እንዳለው ዓይነት ትእዛዝን ከመቀበል ማፈንገጥ (insubordination) ከብት በማረድና ጠላ ጠምቆ በጨዋታና በፌስታ የሚፈታ ጉዳይ አይደለም። ቅጥ ባለው መልኩ ከእያንዳንዷ ውጊያ በኋላ በሚደረግ ግምገማ ነፍስወከፍ ታጋይ ይወቃቀስበታል ይወዳደስበታል ይተራረምበታልም። ውጊያ ውስጥ ትእዛዝን የማይቀበል ሰው ካለ ከመቅጽበት ነው ከውጊያ ቀጠና የምታስወግደው፡ ቀጥለህም በደንቡ ሒሳቡን ታወራርዳለህ፡ አስፈላጊ ከሆነም እስከ መረሸን የሚያስደርስ ሒሳብ ታወራርዳለህ። ታድያ ይሳቅ አበራ ማን ሆኖ ነው እንዲሁ በቀላሉ የሚተው? ስለሆነም፡ በጭራሽ ከሻዕብያ አካሄድና ባህል ጋር የማይሄድና የማይጣጣም እላይ እንደተጠቀሰውም በቴፕ መቅዳትም የማያስፈልገው ጉዳይ ነው። ኢሳቅ አበራ ምናልባት “አገር ለቆ መሄድ ለውሸት ያመቻል” እንዲሉ ከኛ እይታ ብዙ የራቀ መስሎት ሊሆን ይችላል፡ ግን እድሜ ለቴክኖሎጂ ይሀው ሰምተነውስ እየመለስንለት ነው።


በተጨማሪም፡ “ያውቃሉ” ወይም “ያስታውሳሉ” ብዬ ካልኳቸው ከ4ኛዋ ብርጌድ አባላት ጋር ተነጋግሬ ይህ አቶ ይሳቅ እያለ ያለው ጉዳይ ከውጩ የአመራር ስልትና ጠባይ ጋር በፍጹም እንደማይስማማም አነጥረው ነግረውኛል። ይሳቅ አበራን እንደሚያስታውሱት ነገር ግን እያለ ያለውን ዓይነት ትወናን ፈጽመው እንደማያስታውሱ ገልጠውልኛል። እኔም ከዚህ በላይ የአንባቢን ግዜ መቀራመትና መግደል ስለማልፈልግ ወደ ሚቀጥለው ልለፍ።

ትንሽ ስለራሴ

ኢሳቅ አበራ ነበርኩበት በሚለው ምሽግ ውስጥ ነበርኩ። የኛ ጦር ክፍል ከተለያዩ የድጋፍ ሰጪ ክፍሎች የተውጣጣ ነበር። ኢሳቕ ከጠቀሳት ኮረብታ ከ’ታባ ተከል’ እስከ ‘ደብረ-እመን’ ያሉ ምሽጎችን በደንብ አድርጌ አስታውሳቸዋለው። ከወያኔ ታጋዮች ጋርም ግሩም ከሆነ ትዝታ በስተቀር አንዳችም መጥፎ ትዝታና ገጠመኝ የለኝም። እዛ የቆዩን የ4ኛዋ ብርጌድ ታጋዮችም፣ ያን ቦታ ለረዢም ጊዜያት የተዋጉበትና የተጋተሩበት፣ በተለይም ገዢ ቦታዎችን በልዩ ጥንቃቄ የሚከታተሉ ነው የነበሩት። ለኛ ከተለያዩ ድጋፍ ሰጪ ክፍሎች ተወጣጥተን ዘመቻውን ለተቀላቀልን የሻዕብያ ታጋዮችም በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ልዩ ትኩረትና እንክብካቤ ያደርጉልን ነበር። እኛን ሲንከባከቡና ለመታደግ ሲሉ ብዙ የብርጌድ 4 ጀግና ታጋዮች ተሰውተዋል። የ4ኛዋ ብርጌድ አባላት በሙሉ ከአዛዦቻቸው እስከ ተራ ታጋዮች ድረስ ሁሉም እጅግ ምርጦች፣ ህልከኞች፣ ቀልደኞችና ኃይል ተዋጊዎችን ነው የነበሩት፣ ከወረራው ማግስትም በሰላም ሸኝተውናል።

ኢሳቅ አበራ በትረካው፡ የቦታ ስሞችን አደነጋግሯል። ይህ ግን ከግዜ ብዛት የተፈጠረ ሊሆን ይችላል። እጅግ የገረመችኝ ግን “ሕሽክብ የተባለ ቦታ፡ ‘የወያኔ ሬዲዮ ጣቢያ’ የነበረባት” ብሎ የተናገራት ነች። ድንቄም። መጀመሪያ ቦታው ‘ሕሽኽብ” አይደልም ስሙ። ይህ ብቻም አይደለም፡ በዚህ ግዜ ‘የወያኔ ሬዲዮ ጣቢያ’ ብሎ ነገር አልነበረም። ነገር ግን፡ ወያኔ በኤርትራ ታጋዮች የሬዲዮ ጣቢያ ማለትም “በሰፊው የኤርትራ ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ’ የአየር የሞገድ ግዜ ለወያኔዎች ተሰጥቷቸው፡ ፕሮግራሞቻቸውን ያስተላልፉ ነበር። (ቦታውም ‘ጥሩቕሩቕ’ በተባለው ተራራ አካባቢ በሚገኝ፡ “ላዕላይ ዓራግ” በተባለ ሰርጥ ስፍራ ነው)።

ሌላኛው ትዝብቴ ደግሞ እየገለጸው ያለው ጥቃት የተፈጸመት ስፍራ የ’ታባ ተከል’ ግራ ክንፍ ነው ሲል ቆይቶ፡ እንደገና ደግሞ ስለ “ታባ ወዲ ፈንቅል” ያወራል። በዚያ ግንባር ውስጥ ከስድስተኛው ወረራ ማለትም ከቀይኮከብ ወረራ በፊት አንድ ሁለገብ ጥቃት ተፈጽሞ ነበር። በወረራው መካከልም ጠላት የፈጸማቸውን ጥቃቶች ወደ ጎን ትተን ሌሎች ሁለት የመልሶ ማጥቃት እርምጃዎች ተደርገው ነበር። ኢሳቅ እያወራ ያለው ከነዚህ መካከል ስለየትኛው እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ያም ሆነ ይህ ከ4ኛው ብርጌድ አመራሮች ጋር ብቻ ነው ሊሆን የሚችል እንጂ፡ ኢሳቅ ብቻውን ያዘዘው ቀጠና (sector) አልነበረም።

ስለ ውጩና ወዲ ልብሱ በጥቂቱ

እነዚህ ሁለት የ4ኛዋ ብርጌድ አመራሮች፣ በታጋዮች ዘንድ እጅግ ተወዳጆች፣ ቀልደኞች ተግባቢዎችና ሩኅሩኆች መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ገልጸውልኛል። በህግሓኤ ውስጥም በዚህ ጠባያቸው ነው የሚታወቁት። ሁለቱም ኣዛዦች የሚታወቁት ለበታቾቻቸው የሰራዊት አዛዦች ይሰጡ በነበረው የስራ ነጻነት ነው። ሁለቱም አመራሮች ከበታቾቻቸው ማለትም ሁኔታዎችን በቅርበት ከሚከታተሉ የሻምበል አመራሮች የሚያገኙትን ሃሳብ የመቀበል ባህሪ እንደነበራቸው በዚያን ግዜ የሻምበል መሪ የነበረ አንድ ነባር ታጋይ ገልጾልኛል።


በመጨረሻም፦ በወያነ ሰራዊት የሻንበል አመራር የነበረው ይስሃቕ ኣበራ፡ የበላይ ኣዛዡ የሆነው የውጩን ትእዛዝ አልቀበልም ብሎ ከበርካታ ሰዓታት በኋላ በገዛ ራሱ ፕሮግራምና ስልት ስራዉን እንዳከናወነ የገለጸው አባባል ራሱን ለመካብና ጨቅላዊ ወይ ልጅነታዊ ዝንባሌውን ገሓድ ከማድረግ ባሻገር፡ አንዳችም እውነታ ያለው አይመስልም። ውትድርና ወይ ወታደር ቤት ውስጥ ያ ብዙ የለፈለፈበት ዲሞክራሲ ቦታ የለውም፡ አይሰራምም። ወታደርና ውትድርና ራሱን የቻል የአስተዳደር ሕጎች (code of conduct) አሉት። ጉዳዩ ግን ወያኔ ሲፈጠር ጀምሮ
ሻዕብያ የትግራይ ነጻነትን የማይቀበል የቡርጅዋ ድርጅት ነው

ከሚል ሰንኮፍ ወይ ተልካሻ አመለካከቱ የተነሳ እንጂ በሻዕብያና በወያኔ መካከል በየዕለቱ በሚደረገው ግንኙነትና የስራ አተገባበርና አመራር ይህ ነው የሚባል ልዩነት ስለነበረ አይደለም። ከሂስና ግለሂስ ጀምሮ፡ ወያነ ውስጣዊ ችግሮቹንና ግጭቶቹን ይፈታበት የነበረው ጥበብ ከሻዕብያ የኮረጀው ጥበብ ነው። የሻዕብያ ታጋዮች “እናንተ አዛዦቻችን ብትሆኑ ይሻለናል” ይሉን ነበር ይላል ወያኔው ኣይተ ይስሃቅ አበራ።
“ገራሚ” ብየ ብቻ ልለፈው እንጂ!

ክብር ለሰማእታቶቻችን

ሓምለ 2019


አነጋጋሪዋ ቪዲዮ፡



ጀግናው ሜጀር ጀነራል ገብረዝግሄር ዓንደማርያም [ውጩ] ማን ነው? ውጩ ተሰውቷል ነገር ግን ታሪኩ ህያዉ ነው፣ ለአብነት አሰብን ነጻ ባወጣ ማግስት ለህዝብ ያስተላለፈውን መልእክት ማድመጥ ይቻላል። የሕወሓት (ትህነግ) መሳፍንቶች እውነተኛ የኤርትራዉያንን ታሪክ ሊፍቁና ሊደመስሱ አይችሉም።

ብርሃነ ሃብተማርያም

Eritrea- Personal Interview With Late Maj. General Ghebregziabhier Andemariam (Wuchu), About his Childhood And His Life As A Fighter:



ERi TV Late Maj General Gebregziabher Andemariam (Wuchu) - seminar on the Great Denkalia-Assab Front 1991:





Eritreas war to Freedom in 1988, Nadow ez:



ሜጀር ጀነራል ገብረዝግሄር ዓንደማርያም: ህግሓኤ/ህሰሓኤ ኦፕረሺን ፈንቅል በሚል መጠሪያ ሰምሃርንና ምጽዋን ነጻ ባደረገው ውጊያ ወቅት የተናገረው አጭር ታሪካዊ ጥቅስን የኋላኋላ በተግባር በጀግንነት ተርጉሞታል።



አንዳንድ የሻዕብያ ተወዳጅ ሙዚቃዎች

1. "ብናይ ደርጊ ፈኸራ ንድሕሪት ነይትምለስ ሰውራ ኤርትራ" ብሙዚቃውን ድምጻውን ስነ-ጥበባውን ሓርበኛ ተኽለ ክፍለማርያም:



2. "ሓርበኛ" በድምጻዊ መልኣከ ኣብርሃም በትግሉ ዘመን የነበረች ሙዚቃን ዳግም እንደዘፈናት:



3. "ተሃንዳዲ ሓይሊ መን ከማይ በሃሊ" ብሙዚቃውን ድምጻውን ስነ-ጥበባውን ሓርበኛ ተኽለ ክፍለማርያም:



Zmeselo ኃወይ ንስኻ

ኢኻ!



Post Reply