ስለ በረራ
እኔ ስለ በረራ መከራከር አለብን ብዬ አላምንም። ምክንያቱም በመድቫል ዘመን ስለነበረ ጊዜያዊ አሰፋፈር በመከራከር ለዛሬው የፖለቲካና የአስተዳደር ጉዳይ የተሻለ መፍትሔ እናመጣለን ብዬ አልገምትም።
ከሁሉም በላይ ግን በረራ ራሷ በአርኪኦሎጂ ግኝት በተረጋገጠ አንድ የተወሰነ ቦታ ላይ የምትገኝ አይደለችም። ባሉት መላምቶች አንዳንዶች ከእንጦጦ ተራራ ጋር ያያይዟታል፤ ሌሎች ደግሞ ወደ ዛሬው ሞጆ አካባቢ ያመለክታሉ። የትኛውንም መላምት ግን፣ በረራን ከዛሬው የአዲስ አበባ ከተማ ወሰን ጋር አያገናኝም። ይህም በቀላሉ (google/AI Search) ሊጣራ የሚችል እውነታ ነው።
ስለዚህ የበረራን ጉዳይ የዛሬውን የአዲስ አበባ ወሰን፣ የከተማዋን አስተዳደር ወይም የማንነት ጥያቄ ለማስረገጥ እንደ ዋና ክርክር መጠቀም ውሃ የሚያነሳ አይደለም። የመድቫል ዘመን አሰፋፈር የዛሬዋ ከተማ የሕግ፣ የአስተዳደር ወይም የወሰን ማስረጃ ሊሆን አይችልም።
የዛሬውን ጉዳይ በዛሬው ነባራዊ እውነታ፣ በሕግ፣ በማስረጃና በሰዎች መብት ላይ ተመሥርተን መወያየትና መፍታት አለብን ብዬ አምናለሁ።
በረራ የተባለችውን የመድቫል ዘመን አሰፋፈር ከዛሬዋ አዲስ አበባ ጋር በግድ ለማገናኘት መሞከር፣ ዛሬ ለሚነሱት የሕግ እና የአስተዳደር ጥያቄዎች መፍትሔ አያመጣም። ትናንትን በማስረጃ መመርመር ጥሩ ነው፤ የዛሬን ጉዳይ ግን በዛሬው እውነታና በሕግ እንፍታው ለማለት ነው።
-
Bete Gojjam
- Member
- Posts: 1111
- Joined: 02 Nov 2019, 03:48
- Location: Guto Gida
opdo response for Berara Claim
opdo Lenjiso Birhanu Facebook