Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member+
Posts: 5304
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

አሰብ እና ‘የብልጽግና ነብያት’ የቁም ቅዥት እና ‘ራእይ’

Post by Meleket » 05 Aug 2026, 03:04

Please wait, video is loading...
ለዚህ ለብልጽግናው ካድሬ ለ “ነብይ ዋቅቶሌ”፡ በአንድ Hayle Desu የተባለ ምርጥ ዜጋ የተሰጠውን ምርጡን ክርስቲያናዊ ኮሜንት እናስከትላለን!

Meleket
Member+
Posts: 5304
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አሰብ እና ‘የብልጽግና ነብያት’ የቁም ቅዥት እና ‘ራእይ’

Post by Meleket » 05 Aug 2026, 07:58

ምን ትቀባጥራለህ ካገለገልክ ለህዝቡ የባህርበር ሳይሆን የሰማይ በር አሳይ። አገልጋይ ነኝ ካልክ ለተጠራህለት አላማ ተለይ አገልጋይ የሚሰማውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ከማን እንደሰማ የሚያውቅ የሰማውን መቼና የት መናገር እንዳለበት የሚያውቅ ነው የታየውን ሁሉ አይናገርም እሺ አየህ ለህዝቡ ነገርከው ህዝቡ ምን ያድርግ? Hayle Desu


Hayle Desu እግዚአብሔር ይባርክህ!

Odie
Member+
Posts: 8771
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: አሰብ እና ‘የብልጽግና ነብያት’ የቁም ቅዥት እና ‘ራእይ’

Post by Odie » 05 Aug 2026, 08:05

ድፍረት!
መስመር የሳተና ያሳተ ትውልድ!
ፖለቲካና ሃይማኖት ደባልቆ ህዝብን manipulate ማድረግ‼️
የስው ልጅ የራሱን ምኞት በሃይማኖት ስበብ ሲያስፈፅም!!

Meleket
Member+
Posts: 5304
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አሰብ እና ‘የብልጽግና ነብያት’ የቁም ቅዥት እና ‘ራእይ’

Post by Meleket » 06 Aug 2026, 05:33

እሱ ራሱ ካልመጣ በስተቀር፡ በነ ዋቅቶሌ የሚሆን ነገር የለም ያልበት ዘመን ተሻጋሪ፡ የኛ የኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ ኤርትራዊ ምልከታ ነው፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር ዳግም አጋርተናችኋል።

Meleket wrote:
12 Aug 2018, 08:53
ርእዮት - ግርድፍ ግጥም

አንድ እናት ነበረች ልጆች የነበሯት፣
እጅግ ውብ የሆነች እንከን የማይወጣት።
ያለም ነገር ሆኖ እርጅና መጥቶ፣
ልጆች ስታሳድግ እንግልቷ በዝቶ፣
ብዙ ስቃይ አየች የማያልቅ ተወርቶ።
ግን አልሰነፈችም በማድረጓ ጥረት፣
አንድ ልጇን ዳረች መርቃ በክብረት።
ያለም ነገር ሆኖ የጤናዋ ጉዳይ፣
ለልጆቿ ስትል እሷ ስትሰቃይ፣
ከእለት ወደ እለት መሻሻል ሳያሳይ፣
ከእርጅናው ጋራ አባሰባት ስቃይ።
እንዲህ እንዲህም ሲል ያይኗን ብርሃን አጣች፣
ልጆቿ ሲያብቡ እሷ ግን ገረጣች።
ይህንን ታዝባ ባለ ትዳር ልጇ፣
እናቷን መርዳቷን አረገች ግዳጇ።
እናቷን ስትመራ በመንገዷ ሁሉ፣
ለመመረቅ ነበር እንዲያው በጥቅሉ።
እናትየዋ ግን የእናት ነገር ሆኖ፣
ልጆቿን ስትመግብ አንድ ልጇ ጨክኖ፣
አንድ ሃሳብ አመጣ አወላግዶ አጢኖ፣
ካወቅኩ ባይ ልጇ በቀረበ ‘መላ’፣
በሰላሙ ሰፈር ተንኮል እንዲያጠላ፣
እንዲህ እንዲህ አላት በነገር ፍተላ።
“ልጄ በመሆንሽ ራሴ የወለድኩሽ፣
የምልሽን ስሚ እንዲያው አትቅለስለሽ።
ይህ ያይኖችሽ ብርሃን ከኔ የወረስሽው፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ ቁርጥሽን እወቂው።
ይህን ሃቅ አጢነሽ ተንግዲህ በኋላ፣
ማንኛውም ስራሽ እኔን ማያጉላላ፣
እንዲሆን አድርጊ እኛ እንዳንጣላ!
እንዲያውም ይህ ዓይንሽ ሁሉን ምታይበት፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ እንዳሻኝ ምሆንበት፣”
ብላ እንድታስብ ያቺ ምስኪን እናት፣
አወቅኩ ባይ ልጇ በአንክሮ መከራት።
ባለትዳር ልጇ የመላች በትዕግስት፣
መረጠች ለናቷ እውነቱን ልትነግራት።
“እማማ እናታለም ወላጄ ውቢቱ፣
ይህን ሃቅ ስሚኝ እንዲያው ባዛኝቱ።
ድሮ ዓይኖች ነበሩሽ ምን ምን የመሰሉ፣
“በፌደሬሽን” ወቅት ላንቺ የተተከሉ፣
ያያቸውን ሁሉ እንዲያው ሚያማልሉ፣
እኛን በማሳደግ ውለታን የዋሉ።
የአምላክ ስራ ሆኖ ስለጠፉ አሁን፣
እንዴት ታልሚያለሽ ጌታን ለመኮነን?
ባለም አደባባይ ክሶችን መስርተሽ፣
እንዴት ልትዘልቂው ነው ፈጣሪን ሞግተሽ?
ያይንሽንስ ብርሃን እንዴት ልትመልሽ?
የተጠቃሚነት መብቱ ይገባኛል፣
የራስ ባልሆነ ዓይን እንዴትስ ይቻላል?
ይልቅ ጠባይ አርገሽ ከኔ ከልጅሽ ጋር፣
በብርሃኔ ልምራሽ እንኑር በፍቅር።
አንቺም ዋዛ አይደለሽ ብዙ ሃብቶች አሉሽ፣
ይህ የዓይኔ ብርሃን አይቀርም ሳይጠቅምሽ።
እንዲህ እንዲህ አርገን እየተጠቃቀምን፣
በፍቅር መኖር ነው ለኛ የሚበጀን።
ያለሽ አንድ አማራጭ ዓይንሽ እንዲበራ፣
እሱ ራሱ መጥቶ ተዓምር ካልሰራ፣
ሌላ መላ የለም ሚሆን በፉከራ፣
ጭቃውን አብኩቶ አይንሽን ነካክቶ፣
እሱ ካልዳበሰሽ ተሰማይ መጥቶ፣
የትም አያደርስሽ ሽለላ ቀረርቶ።

ተከባብሮ መኖር እያለ አንድ መላ፣
ተጋግዞ መኖርም እያለ አንድ መላ፣
እስቲ ዕድል አንስጠው ተንኮል ለሚያሰላ፣
አዋቂ ነኝ ለሚል ለማንም ቱልቱላ፣
ሌተቀን ለሚያልም እኛኑ ሊያባላ።
እኔና አንቺ ሁሌም ከልብ ስንፋቀር፣
እምንሰራው ሁሉ እንደሚሆን ተአምር፣
መሰሪ ዲያብሎስን እንደሚያደርግ ኩምትር፣
በምን አማርኛ ለመግለጽ ልሞክር!!!!!!!

ፍንጭ፦ ይህ ጽሑፍ ዓላማው፣ የሰው ገንዘብ ሚመኝን ክፉ መካሪ መሰሪን ለመገሰጽ ነው።

Meleket wrote:
05 Aug 2026, 03:04
Please wait, video is loading...
ለዚህ ለብልጽግናው ካድሬ ለ “ነብይ ዋቅቶሌ”፡ በአንድ Hayle Desu የተባለ ምርጥ ዜጋ የተሰጠውን ምርጡን ክርስቲያናዊ ኮሜንት እናስከትላለን!

Right
Member+
Posts: 5201
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: አሰብ እና ‘የብልጽግና ነብያት’ የቁም ቅዥት እና ‘ራእይ’

Post by Right » 06 Aug 2026, 06:49

Eritrea is a dying country. I don’t think those who called themselves Eritreans realized it how and when the tiny and the wrongly manufactured country will die. Because they are too stupid and emotionally dysfunctional to understand it.

DEMOGRAPHYic declines.

In any country around the world including as impoverished country as Uganda or a failed country like Ethiopia or first world countries like the USA & Europe - just look at the statistics of new comers or immigrants. Little Eritrea is on the top 3.

They are migrating upto 4 generations. Young and old. Let alone a new dysfunctional country even the big and powerful countries can’t survive demographic decline.

Ethiopians should shut up talking about Assab for now. Instead develop a simple and sound strategy. Close the borders, allow migration to a designated area and help them move to a 3rd country as quickly as possible as that will encourage more migration, deport all those well established Eris to a 3rd country or incentivize them to do so, don’t allow any export or import to or from Eritrea. Lock it through legislation with brutal enforcement.

Give it 20 years and revisit the policy. Period.
That will speed up the death process.

Meleket
Member+
Posts: 5304
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አሰብ እና ‘የብልጽግና ነብያት’ የቁም ቅዥት እና ‘ራእይ’

Post by Meleket » 06 Aug 2026, 08:38

በብልጽግና ወንጌል ነብያት በነ “ነብዩ ዋግቶሌ” እና መሰሎቻቸው የተታለሉና የተወናበዱ ኢትዮጵያዉያን የብልጽግና ወንጌል ኣማኞች ምን የማይሉት ነገር አለ! " ኤርትራ እየሞተች ነው፡ አሰብ ለኢጦቢያ ሲሰጥ ራእይ አይተናል ባረንቱም ኦሮምያ ነው" ይላል፡ ተመስገን የማያውቀው እና የሰው ሃብት የሚመኘው የነ ዋግቶሌ ወንጀለ ብልጥግና ምዕራፍ “ኮሪደር” ላይ። :mrgreen:
Right wrote:
06 Aug 2026, 06:49
Eritrea is a dying country. ....

Post Reply