Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 44060
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አቢይ አህመድ አሊና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች

Post by Horus » 16 Jul 2026, 13:59

እኔ ሆረስ ዑይነ ብርሃን ነኝ ። ከገናናው ንጉስ አጼ ምኒልክ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔ አንድን ኢትዮጵያን የሚመራ ሰው የምለካውና ፣ የምደግፈውና የምቃወመው በማንነቱ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ነው ወይስ አይደለም? የኢትዮጵያን ግዜያዊና ዘላቂ ጥቅሞችን ይተገብራል ወይስ አይተገብርም በሚሉት መለኪያዎቼ ነው።

ስለሆነም ዛሬ እኔ በአቅሜ 30 የዚች የምወዳት አገር ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞችን ለይቼ በዚያ መሰረት አቢይ አህመድ አሊን በመደገፍ ፣ ወይንም በመንቀፍ ወይንም በመቃወም የዜግ ነት ሃላፊነቴን በመወጣት ላይ እገኛለሁ ። አቢይ አህመድ አሁን ላይ ከሞላ ጎደል ሁሉንም 30 ያገር አጀንዳዎች እየነካካቸው ነው። ሰሞኑን ያገር ምክክር ከተጀመረ አንስቶ ሕዝባችን የፖለቲካዊ ያገር ጥቅሞች ላይ አይኑን አዙሯል ።

ሐገ መንግስቱ እንዴት ይሻሻል? ፌዴሬሽኑ እንዴት ይዋቀር? የክልሎች ድንበር እንዴት ይሻሻል? የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ይቋቋሙ ወዘተ! ለምሳሌ በእኔ እምነት የኢትዮጵያ ፓርላማ ሁለት ቼምበር ወይም ባይካሜራል ቢሆን የተሻለው ነው ። ማለትም አንዱ ቼምበር የክልል ወይም ብሄረ ሰብ ጥቅሞችን የሚያስከብርና ሌላው ሕዝባዊ ቼምበሩ የዜጋዎችን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ሁለቱ ሚዛን እየጠበቁ የሚሰሩ ባይ ካሜራ ፓርላማ ቢደረግ ዘላቂ መፍትሄ ነው። የክልል ድንበሮች ቢደበዝዙ መልካም ነው። አገሪቱ በፕሬዚዳን ብትገዛ ጥሩ ነው።

ይህም ሆነ ያ አቢይ አህመድ አሊ እነዚህን 30 ያገር አጀንዳዎች ካስፈጸመ የሚቀጡትን 5 አመት ሲጨር ፕሬዚዳንት ሆኖ ሌላ ሁለት ተርሞች ቢገዛ እደግፈዋለሁ ። ኢትዮጵያ በ2045 ሁለተኛ አለም አገር ሆና ፣ ቁጥር 1 ወይም ቁጥር ሁለት ያፍሪካ ኃያል አገር እና ያፍሪካ ቀንድ ብቸኛው ንጉስ ሆና፣ የባህር ኃይሏን በቀይ ባህር የምታንፈላስስ ገናና አገር ያደረገ የዘመናችን ምኒልክ ሆኖ ላየው በጉጉት ስለምከታተለው !!!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች ..

(1)የኢትዮጵያ ባህር በር እና ባህር ኃይል ጥያቄ
(2) የህዳሴ ግድብና ሌሎች አባይ ላይ ስለሚገነቡ ግድቦች
(3) የኢትዮጵያ የውሃ ህብትና የውሃ ኃይል ጥያቄ
(4) የአረንጓዴ ኢትዮጵያና አገር አቀፍ የደን ልማት ጥያቄ
(5) ኮሪደርና የኢትዮጵያ ከተሞች ዝመና ጥያቄ
(6) የኢትዮጵያ እርሻ ዝመናና የመስኖ ልማት ጥያቄ
(7) የማዳበሪያ ፋብሪካ ግምባታ
(8) የእርሻ ትራክተር ፋብሪካ ግምባታ
(9) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
(10) የኢትዮጵያ አየር መንገድ
(11) የኢትዮጵያ ቴሌኮም
(12) የዲጂታል ኢትዮጵያ ፕሮጀችት
(13) የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ ክህሎት ፕሮጀክት
(14) የኢትዮጵያ እስፔስ ሳይንስ ምርምር ጉዳይ
(15) የኢትዮጵያ ኑክሊየር ኃይል ምርመር ጉዳይ
(16) የኢትዮጵያ እስቶክ ማርኬት ጉዳይ
(17) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮጀክት
(18) የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት
(19) የኢትዮጵያ እስታጽቲክስ ሳይንስ እድገት
(20) የኢትዮጵያ አርትና ስነጽሑፍ እድገት ጉዳይ
(21) የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ እድገት ጉዳይ
(22) የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም ኢንዱስትሪ ልማት
(23) ከአፍሪካ 1ኛ የሆነ ያገር መከላከያ
(24) አለም አቀፍ ደረጃ ያለው የትምህርት ሲስተም
(25) የዘርና ጎሳ ፌዴሬሽን መለወጥ
(26) አዲስ ሕገ መንግስት
(27) ፕሬዚዳንታዊ አገዛዝ
(28) የግል ንብረት ሕግ
(29) ዱብል ዜግነት
(30) የገጠር ኮሪደር ልማት (ዘመናዊ ገጠር)
ጁልይ 16 ቀን 2026 ዓም
ሆረስ ዐይነ ብርሃን

Horus
Senior Member+
Posts: 44060
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ አሊና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች

Post by Horus » 16 Jul 2026, 14:18

THE CITY DANCING IN THE RAIN!


Horus
Senior Member+
Posts: 44060
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ አሊና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች

Post by Horus » 16 Jul 2026, 14:35

እኔ ሓምሌን አውቃታለሁ በዘቢዳር ተራራ ላይ! ከባድ ነበር! ይህው የሃምሌ ዝናብ እንደ ጥቅምት ጸሃይ የሚወደድበት ዘመን ደረስን ! ግዜ ስንቱን ያሳያል!



Post Reply