Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7584
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

እኔ ሥራን የማዉቀዉ በወሬ ሳይሆን በተግባር ነዉ

Post by Naga Tuma » Today, 00:59

እኔ ተወልጄ ያደኩኝ እንደ ብዙሃን የኢትዮጵያ ቤተሰቦች የኣርሶ ኣደሮች እና የኣርብቶ ኣደሮች ቤተሰብ ቤት ነዉ።

ጥሮ ግሮ የሚኖር ቤተሰብ ቤት ማደግ ሥራን ከልጅነት ጀምሮ የማስተማር ጥቅም ኣለዉ።

ወደ ኋላ ተመልሼ ሳስብ ብዙ ሥራዎችን ከልጅነቴ ጀምሮ መስራቴን ኣስታዉሳለሁ።

እረኛ ነበርኩኝ።

ማገዶ ሰብሳቢ ነበርኩኝ።

ድኬ የሚባል ገፊ ነበርኩኝ።

እንጨት ፈላጭ ነበርኩኝ።

የጓሮ አጥር ማጠርን የምረዳ ነበርኩኝ።

ለኣጥር ዛፍ ጥሎ መፍለጥ እና ማጓጓዝን የምረዳ ነበርኩኝ።

ልጅ ሆኜ የእራሴን ኣልጋ ሰርቼ ተኝቼበታለሁ። ጥንካሬ ኣንሶት ብዙ ሳይቆይ ወላለቀብኝ።

ምንጭ ሄዶ ዉሃ ቀጂ ነበርኩኝ።

እህል በኣናቴ ተሸክሜ ወፍጮ ቤት ወስጄ ኣስፈጭቼ ተሸክሜ የምመለስ ነበርኩኝ።

እንደ ጥቅል ጎመን፣ ቀይስር፣ ድንች ተክዬ የምሸጥ ነበርኩኝ።

እረኛ ሆኜ ወፍ ዘራሽ ጌሾ ችግኞችን ሳገኝ ጓሮ ወስጄ ኣሳድጌ የጌሾ ቅጠል የምሸጥ ነበርኩኝ።

እረኛ ሆኜ ኣንድ ግዜ የጣዝማ ማርን ጉድጓድም ኣግኝቻለሁ።

ምስር ዘርቼ ሰብሉን ለገበያ የማቀርብ ነበርኩኝ።
ይህ ለቤተሰብ ከሚሰራዉ በተጨማሪ ማለት ነዉ።

በኣማርኛ ስሙን የማላስታዉስ ይዘን ድቅድቃ የሚባል ተባብሮ ስራን ብዙ ግዜ ኣስታዉሳለሁ።

በሬዎችን ጠምጄ መሬት ኣራሽ ነበርኩኝ።

ሰብል ሲደርስ በማጭድ ኣጭድ ነበር።

በበሬዎች እንወቃ ነበር።

ለዐቅም የደረሰ ፈረስን ጠፍሬ ገርቻለሁ።

ዶሮዎችን ኣርብቼ ዕንቁላሎችን እሸጥ ነበር።

በጎችን ኣርብቼ እሸጥ ነበር፣ ለቤተሰብ ጥቅምም ይሆኑ ነበር።

ቡና ነግጄ ነበር፣ ንግዱ ረከስ ያለ ገበያ ሄጄ ገዝቼ በተሻለ ዋጋ መሸጥ ነበር።

ሹራብ መስራትን እራሴን ኣስተምሬ ለፈለጉ እየሰራሁ እሸጥ ነበር።
ለእኔም ሹራብ እየሰራሁ እለብስ ነበር።

ከሁሉም የማልረሳዉ ሹራብ መስራትን በጣም ትንሽ ልጅ ሆኜ እራሴን ማስተማሬን ነዉ።

ኣንድ ቀን ከትምህርት ቤት እረፍት ላይ የነበሩ እህቶቼ በኪሮሽ ዳንቴል የሚሰሩ ለማገዶ ለቀማ ጫካ ሄደን ዳንቴል ሲሰሩ ትንሽ ክር ስጡኝ ብዬ ከሰጡኝ በኋላ እንጨቶች ሰብሬ ክሩን መጎንጎን ጀመርኩኝ። ዝም ብዬ ስጎነጉን ስጎነጉን ኣንድ ዐይን ወጣልኝ። ያዛን ቀን የሹራብ አሰራር ዐይን ኣይቼ የተደሰትኩኝ ደስታ መቼም ኣይረሳኝም። የማይረሳ የመጀመርያዉ ፈጠራዬ ነበር። የሹራብ አሰራር ኣንድ ዐይን እንዴት እንደሚወጣ ታወቀ ማላት መላልሶ እያወጡ ሹራብ መስራት እንዴት እንደሚቻል ታወቀ ማለት ነዉ።

ዘንባባ ገዝቼ ባርኔጣዎችን ሰርቼ እሸጥ ነበር።

እነዚህ ሁሉ ጥረቶች ከተምህርት ጋር ጎን ለጎን ነበረ። መንግስት ያዘዛቸዉ ኣልነበሩም። መንግስት የከለከላቸዉ ጥረቶች ኣልነበሩም።

የመጀመርያ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ሆኜ ለዕረፍት ቤተሰብ ጋ ስደርስ አባቴ መሬት ስያርስ ኣይቼ እረፍት ዉሰድ ብዬ ተቀብዬዉ ሳርስ ዉያለሁ።

የዛን ቀን ትዉስታዬን ከኮሌጅ ስመረቅ የጻፍኩት ኣንድ ኣርትክል ዉስጥ ኣስቀምጫለሁ። እስከዛሬ ድረስ ያ ኣርትክል ስለዛ ቀን ትዉስታ የያዘ መሆኑን ኣልተናገርኩም።

እንደዚህ ጥሮ ግሮ ኮትኩቶ ላሳደገኝ ቤተሰብ ክብሬ ዘላለማዊ ነዉ። ስለዚህ የእኔን እዚህ ደርሻለሁ ማለት በክብር የመስማት መብት ኣላቸዉ።